ሀገር ወዳዱን አቶ ነዓምን ዘለቀን ተውት!!! – ወንድወሰን ተክሉ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ሰሞኑን በአቶ ነዓምን ዘለቀና ወገኖቻችን መካከል የቃላት ጦርነት የተከፈተ በሚመስል መልኩ ከየአቅጣጫው ቃላት ሲወነጫጨፍ እያየን ነው፡፡

በአቶ ነዓምን በኩል ከኢሳት ለሁለት መሰንጠቅ ማግስት ሲሰነዘሩ ባሉ ሀሳቦች ላይ ሙሉ በሙሉ እማልስማማ ሆኖ ሳለ በተለይም ሰሞኑን ከባህር ዳሩ አደጋ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የአማራን ህዝብ ከመንግስት ጋር እንዲቆም ያቀረበውን ጥሪና ስለ አብን የገለጸውን አቋሙን ሙሉ በሙሉ ባልቀበልም አቶ ነዓምን ዘለቀን ዛሬ ላይ እኛ የአማራ ልጆች በይፋ ልንጋፈጠውና የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ልንከፍትበት ይገባል ብዬ አላምንም፡፡

ሲጀመር ሰውዬውን በጸረ አማራነት ልንፈርጀው እንደማንችልና እንደማይገባንም ካለኝ ትውውቅ አኳያ ብቻ ሳይሆን አቶ ነዓምን ከሚያራምደው አቋምና ፖለቲካዊ ታማኝነቱ አንጻር ልናገር እችላለሁ፡፡

ለምሳሌ ያህል ከሁለት ዓመት በፊት የ12ዓመቱ ታዳጊ ህጻን ዮሴፍ በተሰዋበት የወሎ ወልዲያ በዓለ ጥምቀት ጭፍጨፋ ወቅት አቶ ነዓምን በዋና ጸሃፊነት ሲያገለግል የነበረው የአግ7 አንድ ጸረ አማራ የሆነ መግለጫን እንዳወጣ መጀመሪያ #DawitSolomon ደውሎ እንዳሳሰበኝ እኔም ወዲያውኑ ለአቶ ነዓምን እና ለአቶ አበበ ቦጋለ በመደወል ምን አይነት መግለጫ ነው ድርጅቱ የሚያወጣው በማለት ጥያቄ ሳቀርብ ከሁለቱም የአግ7 አመራር ያገኘሁት መልስ ማን አማራ ጠል ሆኖ በአማራ Phobia የፊጢኝ ተጠፍንጎ እንደታሰረ ለማወቅ ኢምንት አልፈጀብኝም፡፡

አቶ ነዓምን በዋና ጸሃፊነት የሚመራው አግ7 በወልዲያው ጭፍጨፋ (ከ15በላይ ንጹሃን የአማራ ልጆች ያለቁበት ነው)ላይ ባወጣው መግለጫ ስህተተኝነትን ያለአንዳች ውጣ ውረድ «ስህተት ነው» በማለት የገለጸለኝ ሲሆን በዚህም ሳይገታ ማብራሪያ በመስጠት ነገሩን ለማስተካከል እንደጣረ እማንዘነጋው ሀቅ ነው፡፡

ነገር ግን የአግ7 ቃለ አቀባይ የነበረው የአቶ አበበ ቦጋለ መልስ ግን የተገላቢጦሽ አማራ ጠል የሆነ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የአበበ ቦጋለን ስም ከጠቀስኩ አይቀር ባለፈው አመት ሀምሌና ነሀሴ 2018 ላይ በአንድ ወዳጄ አቅራቢነት ለትንሳኤ ራዲዮ መጣጥፍና ዜና እንዳቀርብ በተደረገበት ወቅት በመተከል ህጻን አበጥር ወርቅ በጦር ቀስት በተወጋበትና ብልቱ በተሰለበበት ጥቃት ያቀረብኩትን ዘገባዬን የትንሳኤ ራዲዮ ሳያስተላልፍ ይቅረና ለምን ብዬ ስጠይቅ የራዲዮ ጣቢያውን አለቃ አበበ ቦጋለን አነጋግር ተብዬ ደውዬለት ሳነጋግረው ቃል በቃል የነገረኝ «ወንድወሰን ያቀረብከው ዘገባ የአማራን ብሄርተኝነት የሚያነሳሳና አሁን እየተነሳሳ ያለውንም ብሄርተኝነት የሚመግብ ግብዓት ስለሆነ አግጄዋለሁ» በማለት በአማራው ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚዲያ መግለጽ አይገባም ብሎ ያገደብኝ ሰው ሲሆን የእኔም ለትንሳኤ ተሳትፎ እዚያው ላይ እንዲበጠስ የቻለበትን ክስተት ልጠቅስ እወዳለሁ፡፡

ወደ አቶ ነዓምን ስመለስ ለእኔ ሰውዬው ከድርጅት ታማኝነት ይልቅ ለህዝብና ለሀገር ታማኝነት እራሱን ያስገዛ ፖለቲከኛ እንደሆነ ነው እምረዳው፡፡ እንዴት ብትሉኝ ይህው ስብእናው ነው እኔን እና አቶ ነዓምንን በአካል ሳንገናኝ ግን በተመሳሳይ ሀገራዊ ዓላማና ቅኝት ዙሪያ ስንጓዝ ልንተዋወቅ ያበቃንና በዚህ ትውውቅ ሂደት ከድርጅት ድርጅት አንዴ መድህን ኢህአፓ እና መሰል ከሆኑትና ከቅንጅት መፈጠር በፊት በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ወያኔን በመታገል ጉልህ ሚና ሲያደርጉ ከነበሩት ድርጅቶች ጋር ተጠግቶ ለመታገል ሲሞክር ነው እማውቀው፡፡

አቶ ነዓምን በእውነተኛ የትግል መንፈስ ተሞልቶ ለሀገሩና ለወገኑ እውነተኛ ትግል ለመታገል ያልምና ከድርጅቶች ጋር ሲቀላቀል ድርጅቶቹ እሚናገሩትና በተግባር እሚያደርጉት ለየቅል እየሆነበት ድርጅቶቹን ጥሎ እየወጣ ከድርጅት ወደ ድርጅት ሲንከራተት የነበረ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ይህም ሀገር ወዳድና ትግል ወዳድነቱ ነው እዚህ ኬኒያ ካለሁት ከእኔና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመገናኘትና ብሎም በርካታ ፖለቲካዊ ስራዎችን ለመስራት በጽኑ ሲጥር የነበረው፡፡

ይህ እንቅስቃሴው ግምቦት 7 ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ሲሆን በኢሳት ምስረታም ሲያደርግ የነበረውን ጉልህ የመሪነትን ሚና ሁላችሁም ስለምታውቁት ሳልደግመው አልፈዋለሁ፡፡ ለምሳሌ ያህልም ኢሳት ሙሉ በሙሉ ለሁለት ከመሰንጠቁ በፊት በአቶ አበበ ቦጋለና በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ በኢሳት አባላት ላይ የተከፈተውን Pre-emptiveየፕሮፖጋንዳ ዘመቻን በፊት ለፊት ወጥቶ የኢሳት ጋዜጠኞችን በመከላከል ሁለቱን አጥቂዎች በይፋ የተቸ ሲሆን (በእርግጥ መልሶም ይቅርታ መጠየቁንም አውቃለሁ) መጨረሻም ከአግ7 ሊለቅ የቻለው በጎንደር የሰፈሩ የድርጅቱ የቀድሞ ታጣቂ አባላት ህልውና ጉዳይ አስጨንቆት እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦልናል፡፡

በእነዚህ ወገኖቻችን ስቃይ ኃላፊነቱን የለቀቀውና ከላይ በወፍ በረር አገላለጽ ያስቀመጥኩትና በቅርበትም የማውቀውን አቶ ነዓምን ዘለቀን አማራ ጠል ነው ብለን ከመተቸት ይልቅ ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያዊ አንድነትን አራማጅና ለዚህም አላማው ታማኝ የሆነ ነው ብለን ልንረዳው ይቻለናል፡፡

እንደምናስታውሰው ሁሉ እነዚሁ ወገኖቻችን ማለትም አቶ ነዓምን ህልውናቸው ያስጨነቀውና ከድርጅቱ ለመሰናበት ያበቃው ወገኖቻችን ናቸው መጨረሻ ላይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ባህርዳር ላይ አትሰበሰብም በማለት ሲያግዱት ያየነውና የአቶ ነዓምንን ስጋት ልንረዳለት ይቻለናል፡፡

ይህን ካልኩ በኃላ በአቶ ነዓምን በኩልም እየተስተጋቡ ካሉት ሰሞነኛ አቋሞች ውስጥ አብዛኛዎቹን በፍጹም እማልጋራና እማልቀበላቸው መሆኑንም መጥቀሱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ለምሳሌ ያህል አቶ ነዓምን ኢሳት ለሁለት ተከፍሎ በእነ ኤርሚያስ ለገሰ የሚመራው ኢትዮ360ሚዲያ ከተቋቋመ በኃላ በእነዚህ ልጆች ላይ ሲያራምድ የነበረውን አቋምና በቅርቡ ደግሞ በባህርዳር በተከሰተው አደጋ መላው የአማራ ህዝብ ከመንግስት ጋር ቆሞ ህልውናውን እንዲታደግ ሲል ያቀረበውን ተማጽኖአዊ መልእክቶቹን በሙሉ With do all respect የማልቀበልና ብሎም የምቃወመው ሲሆን ከሁለት ቀናት በፊት ባሰራጨው የእልህ፤ቁጭትና የንዴት መልእክቱ ላይ ስለፋሺስት ድርጅቶች ባብራራው አረፍተ ነገር ላይ የአብን ስም ባካተተበት መልእክቶቹ ፈጽሞ ድጋፍ እንደሌለኝ መግለጽ ይኖርብኛል፡፡

ይህ በአቶ ነዓምን ዘለቀ አቋምና በእኔ አቋም መካከል ያለው የአቋም ልዩነት ግን ፈጽሞ አቶ ነዓምንን እንዳወግዘውና ባላተገባ ክብረ ነክ የስድብ ውርጅብኝ እንድተቸው ያላስቻለኝ ምክንያት የአቶ ነዓምን ተግባርና እንቅስቃሴ ለድርጅታዊ ጥቅምና ግለሰብዓዊ ጥቅም ብሎ ጸረ አማራ አቋም ይዞ ሳይሆን ለሀገር ህልውና ይበጃል ብሎ ስላመነ እንደሆነ ስለምረዳ ነው፡፡

ሲጀመር አቶ ነዓምን አማራ ጠልና ጸረ አማራ ሆኖ የአማራን መደራጀት የሚቃወምና የሚያወግዝ ሰው አይደለም፡፡ በእሱ አረዳድ ለሀገር ይጠቅማል ብሎ የማነበትን ህብረብሄራዊ አወቃቀርና አደረጃጀትን ብዙዎቻችን ስናምንበት እንደነበረው ማለት ነው ዛሬም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚያምን ሲሆን ይህንንም እምነቱን በይፋ በሚገልጽበት ወቅት ሀሳቡን በሀሳብ Challenge አድርገን መጣል ሲገባን ቅዋሜያችንን ወደ ግለስብእና ደረጃ በማውረድ የ Character assassination አይነት ባለው ይዘት አቶ ነዓምንን በማንነቱ መውቀስ፤መተቸትና ብሎም ማንጓጠጥ ተገቢ ሆኖ ስላላየሁት ነው ሀገር ወዳዱን አቶ ነዓምን ዘለቀን እንተወው የሚለውን ይህንን መልእክቴን ላስተላልፍ የወደድኩት፡፡

ዛሬ የአማራ ህዝብ ወዳጆቹን የሚበትንበት ሁኔታ ላይ ሳይሆን ያለው በሩቅና በቅርብ ያሉትን ገለልተኛ መሳይና በዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቀው በርቀት እያዩት ያሉትን ወገኖቹን ድጋፍ የሚሻበት አደገኛና ወሳኝ ምእራፍ ላይ ባለንበት ሁኔታ የፕሮፖጋንዳ ፍላጻችንን በሙሉ ወደ አንድ የለየለት ጸረ አማራ ኃይል ላይ ማነጣጠር ይኖርብናል እንጂ ኃይላችንን ማባከንና ብሎም አላስፈላጊ የሆነ የ Confrontation ግንባር በየቦታው መክፈት አይገባንምና አቶ ነዓምን ዘለቀን ተወት እናድርገው ስል ጽሁፌን እደመድማለሁ፡፡

13 Responses to ሀገር ወዳዱን አቶ ነዓምን ዘለቀን ተውት!!! – ወንድወሰን ተክሉ

 1. How comes somebody who dances with OLF extremists get the morality to condemn ABN? Sorry Neamin Zelelke for the fatal mistake you are committing. How comes you call Amharas to collaborate with the government of Abiy which practices ethnic cleansing against these innocent and hardworking Ethiopians? Why do you think Amhara intellectuals and business people are jailed in mass without the due process of the country`s law?. Why do you think the Amhara state is under the control of oromo army?

  There is one propaganda that Berhanu the puppet and his traitor collaborators are parroting: ABN caused commotion during his political rally in Bahirdar. This is a lie, in fact a white lie. What happened was that his former comrades-in-arms-former arbegnoch G7 soldiers-came to the scene of the meeting to demonstrate against the betrayal of their former boss. Instead of facing the situation, the timid Berhanu Nega fled from the meeting hall.

  The one million dollar question, however, is, why the poor, innocent, hardworking, and God-fearing Amhara people have so many enemies, left and right, including TPLF, OLF, all so-called liberation fronts created in the image of TPLF and OLF, shabia, white senile lobbyists such as herman cohen etc?

  meseret
  July 8, 2019 at 9:48 pm
  Reply

 2. “ሀገር ወዳዱን አቶ ነዓምን ዘለቀን ተውት!!!” – ወንድወሰን ተክሉ

  አቶ ወንድወሰን ሻቢያ ወዳዱን ማለትህ ነው?

  nahom
  July 8, 2019 at 10:17 pm
  Reply

 3. ዛሬ የአማራ ህዝብ ወዳጆቹን የሚበትንበት ሁኔታ ላይ ሳይሆን ያለው በሩቅና በቅርብ ያሉትን ገለልተኛ መሳይና በዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቀው በርቀት እያዩት ያሉትን ወገኖቹን ድጋፍ የሚሻበት አደገኛና ወሳኝ ምእራፍ ላይ ባለንበት ሁኔታ የፕሮፖጋንዳ ፍላጻችንን በሙሉ ወደ አንድ የለየለት ጸረ አማራ ኃይል ላይ ማነጣጠር ይኖርብናል እንጂ ኃይላችንን ማባከንና ብሎም አላስፈላጊ የሆነ የ Confrontation ግንባር በየቦታው መክፈት አይገባንምና አቶ ነዓምን ዘለቀን ተወት እናድርገው ስል ጽሁፌን እደመድማለሁ፡፡

  1. Who is this “anti-Amhara” enemy anyway? In my opinion, it is none other than the gangsters who have high-jacked and swallowed ABN and thereby swayed its focus to extremist “confrontational politics”.

  2. Okay, let’s assue Amharas are united, what does it mean and then do what? Attack Tigrai, or Oromia or Benishangul? Attack the Federal Government and assume power? Declare independent Amhara State? or what…? Honestly, not clear to me. You may not like to believe it, but eventually you will have to settle down to structured party politics and a “one-man, one vote” democratic governance. As the saying goes, “collective thinking is like digging a mass grave”. Vive la Differance!

  Kedir Setete
  July 9, 2019 at 7:39 am
  Reply

  • የአማራ አንድነት የሚያመክነው ለ50 አመታት በአማራ ላይ ፀረ ህዝብ የሆነውን ዘመቻ ለማምከን ነው:: ይህ ሊገባህ አይችልም አማራ ስላልሆንክ:: የአማራ አንድነት ለኢትዮጵያም አስተማማኝ ሰላምን ያረጋግጣል:: አማራ ሲገነጠል ወይንም ከሀዲ የሀገር አውዳሚ ስራ ሲመራ እይታወቅም:: በራሱ የሚመመጣ ጥቃት ለመመከት አንድነቱ እጅግ ይፈለጋል:: እንዳንተ አይነቶቹ አማራ ጠሎችን ያስደነግጥ ይሆናል :: ነገር ግን አማራን የሚወዱ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ብዙ ተስፋ አላቸው::

   ደመቀ
   July 9, 2019 at 8:51 am
   Reply

   • I am not against Amhara unity. I cannot be! In fact I do not even know if the Amara people are divided. However, if you get a bit sober and think, whichever way you look at it, whatever “unity” you are talking about, eventually you will have to settle down to structured party politics and a “one-man, one vote” democratic governance. Anything other than that is “ye’man bet tefto, ye’man libeji, ye’awre mewleja yihonal enji”. If you mean that is your goal, oops, I withdraw my case!

    “እንዳንተ አይነቶቹ አማራ ጠሎችን ያስደነግጥ ይሆናል”.
    who was using this “አማራ ጠሎችን”? Ow, got it, ABN leaders! Please this is what extremists normally use to suppress views other than their group. Examples are abundant, OLF, EPRDF (members), Meison, Ehapa e.t.c

    Kedir Setete
    July 9, 2019 at 4:29 pm
    Reply

  • The “anti-Amhara” enemy group consists of TPLF, OPDO/OLF and all so called libration fronts created in the image of TPLF.

   If you have a common sense, you have to acknowledge the anti-Amhara propaganda and ethnic cleansing unleashed against Amharic speaking people during the TPLF regime and continued by abiy`s opdo “kegna” government.

   The drama of the so called “cue” led by our hero General Asaminew is part of this anti-Amhara campaign.

   However, despite the hardships, we will prevail.

   Meseret
   July 9, 2019 at 12:31 pm
   Reply

   • “The “anti-Amhara” enemy group consists of TPLF, OPDO/OLF and all so called libration fronts created in the image of TPLF.”

    So what is your strategy to deal with all these enemies? Finish what the General started? Come’on, be sober and think – eventually you will have to settle down to structured party politics and a “one-man, one vote” democratic governance. So should your “enemies”, they have no choice as well. Agul elih, ke’metefafat besteker minm ayametam. If that is what you want, it is your choice.

    I advise you to watch some of the Youtube videos of Daniel Tessema (Zamunda). Amhara at the moment needs more of him.

    Kedir Setete
    July 9, 2019 at 4:51 pm
    Reply

 4. ወንድሜ መልካም ፅሁፍ ነው:: በዚህ ወቅት ከአማራ አብራክ የተፈጠረ ኢትዮጵያዊ አ ብ ን የመቃወም የሞራል ቁመና የለውም::
  ያለመደገፍ ይቻላል ሆኖም መቃወም በአማራ ላይ ለ27 አመታት ያነጣጠረ ጦርነት የለም ብሎ መካድ ነው:: አብን የወለደው በአማራ ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ነው::የአማራ ጠላቶች አብንና አዴፓን ለማጋጨት የማይቆፍሩት ጉድጏድ የለም:: አማራ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አንድነቱ እያደገ ነው:: የዐማራ ጠላት ትናትንም ዛሬም ህውሀት ነው::

  ደመቀ
  July 9, 2019 at 8:03 am
  Reply

 5. አማራ የሆነ ሆሉ ከክልሉ ውጪ የሚኖሩትን አማራ ማሰልጠንና ማስታጠቅ ግዜው የሚጠይቀው አገብጋቢ ጉዳይ ነው። ከታጠቁ አትሊሰት ከሚደርስባቸው ጥቃት እየተከላከሉ ይምታሉ።

  ASTO
  July 9, 2019 at 3:15 pm
  Reply

 6. ዛሬ ብስል ከግርዱ የለየበት ነው። አማራው ለዘመናት በደምና አጥንቱ ባቆማት ሃገር፣ በባንዳና ወራሪዎች ጣምራ ጦር ለ 28 አመታት የቁምስቅሉን አይቷል። ይኽንን ሃቅ ይክድ የነበረና፣ አማራ፟፟፟’ጥሉ ግንቦት 7 ሹም የነበረው፣ ነአምን፣ ከአማራ በተሰብ የሚወለድ፣ መልቲ ነው።
  እርሱ ብሎ አብንን ተች? አብን የተፈተኑ ፣ ብርቅዬ ያማራ ልጆች ናቸው። ገና አመት ሳይሞላቸው፣ ህዝብ ያቀፋቸው አናብስት ናቸው። ተወደደም ተጠላም፣ ያማራው የሞት የሽረት ትግል ገና መጀመሩ ነው።

  messay Dejene
  July 9, 2019 at 6:01 pm
  Reply

 7. It is a sad day for Ethiopia. Most Ethiopians including Amharas are started thinking like Woyane. Ethiopians were against woyane because woyanes were thinking about only their ethnicity. Amharas never been amharas other than Ethiopians. I could not see any difference between TPLF and ABN or OLF and TPLF. They all are narrow ethnic based political entities and for their survival they advocate how their ethnicity were subdued and targeted by an enemy and if there is no one by creating a virtual enemy. Their ultimate goal is to grab power and seat in a palace and doing what Hailesislassie, Mengistu or Meles does once again. If it walks like a duck, quacks like a duck then it must be a duck. All they are doing is creating a narrative that their people are suppressed by some group and creating and instilling fear that a monster is out there to prey on their people.The gullible follower will buy this cheap idea and leads the population to be like Somalia, Yemen and Syria. In my humble opinion, our survival depends on the existence of a nation called Ethiopia.

  Yohannes Temesgen
  July 10, 2019 at 4:12 am
  Reply

 8. አበበ ቦጋለን ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ የአማራ ጠላት አልከዉ -ነአምን ንቅናቄዉ ያወጣዉን መግለጫ ላንተ ትክክል አይደለም ማለቱ ብልግናዉን ነዉ እንጂ ትክክለኛነቱን አያሳይም! ትክክል አይደለም ብሎ መከራከር የሚችለዉ እዛዉ ድርጅቱ ዉስጥ ነዉ እንጂ አንዴ በስምምነት የወጣ መግለጫን ትክክል አይደለም ብሎ ፓብሊክሊ መናገር ነዉር ነዉ። ደግሞም መግለጫዉ ምኑ ላይ ነዉ ጸረ አማራ የሆነዉ? የአማራ አክራሪዎች ሁሉን ነገር ውስጥ እንደ ዝንብ ጥልቅ ማለት ስለምትወዱ ነዉ እንጂ! ዝም ብለህ ዘላበድክ እንጂ ሁለቱንም በቅርብ የምታዉቃቸዉ አይመስለኝም- ደሞ ከመቼ ወዲህ ነዉ ነአምን የግንቦት ሰባት ጸሀፊ ሆኖ የሚያዉቀዉ- እኔ ሰምቼም አላዉቅም- የግንቦት ሰባት ጸሃፊ ሲጀመር ጀምሮ አንዳርጋቸዉ ነዉ- እሱ ሲታሰር ግንቦት ሰባት ጸሀፊ የሚል ስም የያዘ መሪ አልነበረዉም- ንቅናቄዉ የመጨረሻ ጉባኤዉን ሲያደርግ ባደረገዉ ምርጫ የስክረታሪ ዘርፍ ሃላፊ ነበረዉ መልኳንንት አበጀ የሚባል ግን ጠፍቶ ኢትዮጵያ ገባ- ከሱ በኋላ አንዳርጋቸዉ ነዉ ተፈትቶ እንደገና ሴክረታሪ የሆነዉ- የንቅናቄዉ ሊ/መንበር ብርሃኑ ሲሆን እሱ በሌለበት ንቅናቄዉን የሚመራዉ ኤፍሬም ማዴቦ ነበር- ነአምንና አበበ ቦጋለ ሁለቱም በፖለቲካዉ ዘርፍ ስር ነበሩ- ንቅናቄዉ እስኪከስም ድረስ የፖለቲካዉ ዘርፍ መሪ ኤፍሬም ነበር

  Kebede Ketema
  July 12, 2019 at 2:41 pm
  Reply

 9. Some three years ago I stated that G7 leadership and ESAT were heading to a slippery slope. Now they are at the bottom of the cliff bleeding waiting for of Dr Abiy’s OPDO/OLF ambulance to rescue them. At that time I commented that G7 leadership were suffering from the hung over of Amara domination syndrome.

  Inferiority complex ridden Efrem Madebo showed it vividly in his video recorded speech in Australia, in which he said that Amaras want to revitalize their hegemony. Look how mean he was to ESAT news readers and journalists who had declined to fit into OPDO/OLF rule!

  Timid, time tested opportunist Brhanu Nega too, openly demonstrated his Amara hatred by refusing to approach Amara activists and organizations while forming the useless and aborted so called “Ethiopian National Movement”, composed of some of the most extreme fronts that never got tired of branding Amaras as their number one enemy.

  Naamin Zeleqe, whom I saw and listened to in person while he was addressing a gathering in my home town. I watched him walking out from the meeting about 5 times to smoke. That gave me a hint of the type of leaders G7 had. Then, during question and answers, after his boastful presentation about the achievements of G7, I found him acting like the bullying freshman boys of my university life. I din’t think he was useful to G7 as much as he is not and will not be to the cause of Amaras.

  Samma
  July 17, 2019 at 1:12 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.