“በትግራይ ውስጥ የጥላቻ ገበያው ድርቷል”ኤኤፍ ፒ – ህብር ራዲኦ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ሰሞኑን የፓለቲካ ትኩሳቱ ወደ ተጋጋመበት የትግራይ ክልል ያመራው የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት (አዣንስ ፍራንስ) ዘጋቢ እሳዛኝ ፣አስገራምእና አሳሳቢ ያላቸው ትዝብቱን አስፍሯል።

ፍቅር ሲቀዘቅዝ?:-
ለወትሮው አድናቂዎቹን በፍቅር ዘፈኖቹ ያዝናና እና ጮቤ ያስረግጥ የነበረው የሬጌ ሙዚቃ ስታይል አቀንቃኙ አርቲስት ሰለሞን ይኩኑ አምላክ ባልተለመደ ሁኔታ እና ቅጽበት በትግራይ የፓለቲካ ልሂቃኖች የሚቀነቀነው “የጸረ ዶ/ር አብይ አሕመድ አስተዳደር ዘመቻን ለመደገፍ እና የትግራይ አንድነትን ለማግዘፍ በሚል” በጊታሩ ክሮችእና በድምጹ አማካኝነት ሲቀሰቅስ ተስተውለሏል፣ የጥላቻ ዘመቻውንም በይፋ ተቀለቀሏል።

ምነው በዚያ በመረዋ ድምጽህ አማካኝነት ለተዋቂነት ያበቃህን የ ፍቅር ዘፈንህን እንዲህ እርም አልከው? ለሚለው ጥያቄ አርቲስት ሰለሞን ሲመልስ”ምን ታደርገዋለህ ዛሬ በአገሪቱ በሚታየው የፓለቲካ ችግር ሳቢያ ሁሉም ፓለቲከኛ እና አቀንቃኝ(አክቲቭስት) ሆኗል፣ እኔም እንደዛው”በማለት መልሷል።

የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ “ተገፍተናል” የሚል እሮሮ እና ቅሬታ የሚያሰሙት የትግራይ ፓለቱከኞች በተለይ ሰሞኑን በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ ከተሞች ውስጥ የተከሰተውን የክልል እና የፌደራል አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያን ለፓለቲካ ተልእኳቸው ሲጠቀሙበት መሰንበታቸውን የታዘበው የ ኤ ኤፍ ፒ ጋዜጠኛው”ከሰኔ 15ቱ ግድያ በሁዋላ የአብዛኛው የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች እለታዊ የመወያያ እርሳቸው ጸረ አብይ አሕመድ አቋምን ማንሸራሸር ብቻ ይመስላል”ብሏል።

ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ሲጀግን:-
በሀያ ሰባት አመቱ የህዋት/ኢሕአዲግ ዘመን ስልጣናቸውን በመጠቀም ሙስና ፈጽመዋል፣የዚጎችን ሰብአዊ መብትን ጥሰዋል በሚል ውንጀላ የቀረበባቸው አንዳንድ ከፍተኛ የህዋት /ኢሕአዲግ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም። አንዳንዶቹም ለፈጸሙት ጥፋት ከችሎት እንዲቀርቡ መጥሪያ(ዋራንት) ተቆርጦላቸዋል።
ከእነዚህ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች መካከል በቀንደኛነት የሚፈልጉት፣በዶ/ር አብይ አስተዳደር ከስልጣን የተባረሩት እና ከአንዴም ሁለቴ የፍርድ ቤት መጥሪያ
(ዋረንት) የቀረበባቸው ነገር ግን “አልተገኙም” የተባሉት የቀድሞው የመረጃ እና የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ የት እንዳሉ በውል ባይታወቅም አንደ መቀሌ ከተማ የጨርቃጨርቅ ልብሶች ነጋዴዋ ዛይድ መለስ ገለጻ”በአሁኑ ወቅት የመቀሌ ገበያን በአንድ እግሩ ያቆመው ‘እኔም ጌታቸው ነኝ’የሚለው የአቶ ጌታቸው አሰፋ ስም እና ምስል ያለበት ካኒተራ(ቲሸርት)ነው” ብላለች። ዛይድ አስተያየተቷንም ስትቀጥል “የ አቶ ጌታቸው አሰፋ ምስል ያለበት ካኔቴራን በርካታ የትግራይ ልጆች እየገዙት ይገኛሉ፣መልእክቱም አቶ ጌታቸው ጀግና በመሆናቸው ጌታቸውን ለዶ/ር አብይ አሕመድ አስተዳደር አሳልፈን አንሰጥም የማለት ያህል ነው” ብላለች።

የእግር ኳስ ጨዋታ ድሮ ቀር:-

ድሮ ድሮ የ እግር ኳስ ጨዋታ ለመልካም ጤንነት፣ለወዳጅነት፣ለእኩልነት እና ለፍቅር መግለጫነት ነበር።አሁን ግን እግር ኳሱም በፓለቲካው ተጠልፎ ወደ ስታዲዬም የሚተሙት አብዛኞቹ ደጋፊዎች ቢሆኑም ስታዲዬሞችን የፍልሚያ ወረዳቸው ያደረጉ ፓለቲከኞችም አልታጡም።
ባለፈው እሁድ የአመቱ የኢትዬጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዬና የሆነው የመቀሌ 70እንደ ርታ ክለብም የዚሁ የጥላቻ ፓለቲካው ሰለባ መሆኑ አልቀረለትም። ክለብ አዲስ አበባ ላይ አድርጎት በነበረው ግጥሚያ የሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፖስተር በተቃራኒ ደጋፊዎች መውረዱ፣አብዛኞቹ የመቀሌው እንደርታ ክለብ ደጋፊዎች በሄዱባቸው ስታዲዬሞች”እኔም ጌታቸው ነኝ”ከሚለው ቲሸርት መልበስን አንስቶ ኢ-ስፖርታዊ የሆኑ ድርጊቶችን ሲሰሩ ተስተውለዋል። በተቃውሞዎች ሳቢያ የፕሪሜር ሊጉ ለሳምንታት መቋረጡ አይዘነጋም።” በሰሞኑ ግጥሚያ ላይም ህዋት የመቀሌ 70 እንደ ርታ ደጋፊዎችን ለክልላዊ የፓለቲካ ገበያው(አጀንዳው) ማማሟቂያነት ተጠቅሞባቸዋል” ሲል ጋዜጠኛውም ታዝቧል።

ስለ ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ ምን ይባላል? :-

በአብዛኛው የህዋት ፓለቲከኞች ዘንድ ዶ/ር አብይ አሕመድ መልካም ስም የላቸውም።አብዛኞቹ ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ “ገፍተውናል፣ለጠላቶቻችንም አሳልፈው ሰጥተውናል” ሲሉ ይወቀሷቸዋል።

በቅርቡ አ/አበባ ከተማ ውስጥ የተገደሉት የቀድሞው የመከላከያ ኤታማዦሩ ጄ/ል ሰአረ መኮንን እና የቅርብ ጓደኛቸው ጄ/ል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነስርአታቸው መቀሌ ውስጥ በተከናወነበት ወቅት በስፍራው የነበሩ አብዛኞቹ ቀባሪዎች የጥላቻ ስሜታቸውን በግላጭ ሲያሰሙ ተስተውለዋል ።ከተደመጡት የለቀስተኞች ቅሬታዎች መካከል” ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ ከሐዲ ናቸው”የሚል ጎልቶ ተሰምቷል።
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር እና ጸሐፊ የሆኑት ነብዩ ሳህለ ሚካኤል በትግራይ ውስጥ ክርር ያለ የጸረ ፌደራል መንግስት እንቅስቃሴዎች እንደሚታይ የታዘቡ ሱሆኑ “ትግራይ ውስጥ የጭንቀት ድባቡ ከፍተኛ ነው፣በጫናዎች ስርም ነን “ብለዋል።
ትግራይን የመገንጠል ህልም:-

ሁሉም ነገር ፓለቲካዊ መንፈስ እና አየር በሚነፍስባት የትግራይ ክልል መናገሻ ከተማ በሆነችው መቀሌ ውስጥ ትግራይ ብትገነጠል እንደሚሻል የሚያቀነቅኑ በርካታ መሆናቸውን የሚናገሩት የከተማዋ ነዋሪ እና የቀድሞ ዲፕሎማቱ ወንድሙ አሳምነው” ትግራዬች በአሁን ሰዓት ስለ መገንጠል ያላቸው ፍላጎት ከ ልክ ያለፈ ይመስላል። አንዳንዶቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች በሚገርም ሁኔት የኢትዬጵያ አካል ስለ መሆናቸው እና ያለመሆናቸው ሳይቀር ይጠይቃሉ ፣ይጠያየቃሉ ።ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋነት አለው” በማለት ዲፕሎማቱ አሳምነው ትዝብታቸውን ፣የዳበረ ምክራቸውን እና ተግሳጻቸውን ለጋዜጠኛው አካፍለውታል።

3 Responses to “በትግራይ ውስጥ የጥላቻ ገበያው ድርቷል”ኤኤፍ ፒ – ህብር ራዲኦ

 1. Chuhetachinin Qemoone!!!

  The feeling is mutual.

  Chuhetachinin Qemoone
  July 10, 2019 at 2:27 pm
  Reply

 2. NOWHERE IN THE CONSTITUTION IS THERE A CLAUSE PERMITTING THE REFORMED TPLF TO TAKE TIGRAYANS ANCESTRAL LANDS FROM US.

  WE WANT ABAY WOLDU BACK !!!

  ARTICLE 39 OR ARTICLE 100000000039 DID NOT PERMIT THE NEW REFORMED TPLF / REFORMED TIGRAY REGION’S GOVERNMENT TO TAKE TIGRAY FARMERS ANCESTRAL FARM LANDS.

  ” Detained Tigrayan youth land blow on TPLF ”

  Expropriations in places such as Gambella, in Oromia around highly contested Addis Ababa, and the far south, have caused outrage after violent displacements, imprisonments, and beatings.

  Now, it’s Tigray’s turn to suffer unrest due to land tensions—which is just the latest of the region’s challenges.

  SENAIT
  July 10, 2019 at 3:53 pm
  Reply

 3. I would be more glad if I were read the former Diplomats analysis. Does the writer has any intention to post it?

  Thank you,

  Jemal Ababiya
  July 11, 2019 at 2:42 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.