የህወሓት ማ/ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው መግለጫ 7 ዉሳኔዎች

1 min read
7

1 – በጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተፈፀመው ግዲያ ከሀሳብ እስከ ተግባር በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የነበራቸው ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ሀይሎች በሀገራዊ ገለልተኛ ወገን በፍጥነት እንዲጣራ፡ የፀጥታና ደህንነት ተቋማትና አመራሮች በዚህ ተንኮል የነበራቸው ተሳትፎ ሆነ ሀላፊነታቸው አለመወጣታቸው የተፈፀመው ጥፋት ተጠያቂ እንዲሆኑ፡ ይህ የማጣራት ሂደት በአካሄዱ እና ዉጤቱ በየጊዜው ለኢትዮጵያ ህዝቦች ግልፅ እንዲደረግ የህወሓት ማ/ኮ ይጠይቃል።

2 – በዚህ ወቅት ሀገር እየበተነ ያለው ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበው የትምክህት ሀይል ነው። ይህ ሀይል ዕድል አግኝቶ እንደፈለገው እንዲሆን እያደረገ ያለው አዴፓ ነው። ስለዚህ አዴፓ በሶስተኛ አካል ማሳበብ ትቶ፡ ዉስጡን በጥልቀት እንዲፈትሽና እንዲገመግም፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ይቅርታ እንዲጠይቅ፡ ካልሆነ ግን ህወሓት ከአዴፓ ጋ መስራት እንደማይችል።

3 – ኢህአዴግ እንደ ግንባር ሆነ እንደ መንግስት በቀጣዩ ዓመት መደረግ ስላለበት ሀገራዊ ምርጫ ያለው ቁርጥ ያለ አቋም እንዲያሳዉቅ ማ/ኮ ህወሃት ይጠይቃል።

4 – ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ እና የሀገር ሉአላዊነት ከማንኛዉም አደጋ ለመከላከል እና ለመጠበቅ ሀላፊነቱ የተሰጣችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምታደርጉት ትግል ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አጠገባችሁ እንደሆኑ እንገልፃለን።

5 – ህወሓት እንደ አንድ ህገ-መንግስታዊ እና ፌደራላዊ ሀይል፡ ሀገራችን ከወቅታዊ እና ቀጣይ አደጋዎች ለማዳን ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ህገ-መንግስታዊ እና ፌደራላዊ ሀይሎች ጋ ሰፊ መድረክ ፈጥሮ ለመታገል እና በፍጥነት ወደ ተግባር ለመሸጋገር የህወሓት ማ/ኮ ወስኗል።

6 – በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እየተነሱ ያሉት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ ይገባል። ከዚህ ዉጪ የህዝብ ጥያቄ በሀይል ወይም በሌላ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ፍፁም ተቀባይነት የለዉም።

7 – የፌደራል መንግስት በዚህ ሀገር አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ህግ እና ህግ ልዕልነት እንዲከበር፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት እንዲረጋገጥ፣ ህገ-መንግስት እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ እንዲተገበር የህወሓት ማ/ኮ አሁንም በድጋሚ ያሳስባል።

ሌላ ትልቅ ነጥብ ከህወሓት መግለጫ፡
ህወሓት ከአማራ ህዝብ ጎን በመሆን ፀረ-ትምክህትና ገዢ ሀይሎች ትግል በማድረግ መስዋእት የከፈለ ድርጅት ነው። በዚህም ህወሓት ለአማራ ህዝብ ትምክህተኛ የሚል ድርጅት አይደለም።

(Haphtom Berhe እንደ ተረጎመው)