” ታፍነናል፣ ታከለ ኡማ ይውረዱ!!!” ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ – ህብር ራዲኦ

1 min read
4

የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኘው የባልድራስ ሰብሳቢ፣የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኢትዬጵያ ወደ ዘመነ ህዋት አገዛዝ እንዳታዘነብል ስጋቱን ገለጸ ፣ለዲያስፖራው ማህበረሰብም ጥሪውን አቀረበ።

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ አ/አ ውስጥ ጌዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የባላአደራው ም/ቤት ሰብሳቢ እስክንድር ” የህዋት አገዛዝ ከተገረሰሰ ከአንድ አመት በሁዋላ ኢትዬጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ማጎሪያ አገር ሆናለች” ሲል ሰሞኑን በጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች ላይ የተከፈተው የወከባ እና የጅምላ እስራትን አብራርቷል።

“በአሁኑ ወቅት በጭቆና ቀንበር ውስጥ እንገኛለን” ያለው የመብት ተሟጋቹ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ” በሀገራችን ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እንዳንሰበሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናረግ ማእቀብ ተጥሎብናል።ከዚህ አኳያ በውጪ የምትገኙ ወግኖቻችን ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ላይ ስለምትገኙ ጩኸታችንን አስተጋቡልን” በማለት ለዲያስፖራው ማህበረሰብ የድረሱልን ጥሪውን አቅርቧል።

ከስብሰባው ቦታ የወጡ የምስል እና የድምጽ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የባልድራስ አባላት ለመገናኛ ብዙሃናት ሊሰጡት የነበረውን መግለጫ በጩኸት እና በመገፈታተር ለማወክ የሞከሩ፣ኢህአዲግ ያጸደቀውን ባንዲራ በማውለብለብ “እኛ የማንም ድጋፍ አይደለንም ፣እኛ የኢትዬጵያ ህዝብ ወኪሎች ነን።” በማለት ረብሻ ሲቀሰቅሱ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ ወጣቶች ተስተውለዋል። የጋዜጣዊ መግለጫም በከፊል እየተካሂደ ሳለ በሁከት ቀስቃሾቹ ወጣቶች ሳቢያ እና በፖሊስ ጣልቃ ገብነት መግለጫው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ምንም እንኳን ወጣቶቹ የማንኛውንም የፖለቲካ አጀንዳ እንደማያራግቡ በቃላት ቢገልጹም ከሁከት ፈጣሪዎቹ ወጣጦች መካከል አንዱ የውክልና ጊዜያቸው በሰኔ 30,2011 ዓም ያለቀው የአ/አበባ መስተዳድር ም/ል ከንቲባ የሆኑት ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን በችግኝ ተከላ ላይ ሳለ የሚያሳየው የምስል ማስረጃ ወጣቶቹ ከኢንጂነሩ ጋር የቀረበ ግንኙነት ሳይኖራቸው እና በስሜት ሳይገፋፉ እንዳልቀረ ብዙዎች ይገምታሉ።
የባልድራስ ሰብሳቢ የሆነው እስክንድር ነጋ በበኩሉ “ኢ/ር ታከለ ኡማ ማንነታቸው አሁን በግልጽ ታውቋል፣ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመተባበር ከባህርዳሩ እና ከአ/አ ችግር ጋር በማያያዝ ሰላማዊ ዜጎችን ሰሞኑን አሳፍሰዋል።ከዚህ አኳያ ታከለ ኡማ ያለቀው ስልጣናቸውን አስረክበው ቦታውን ለተተኪው ባስቸኳይ ይልቀቁ” ሲል አቋሙን ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል እና ለጋዜጠኞች መብት የሚታገለው(ሲፒጂ)በእየ ፊናቸው ባወጡት መግለጫ ባለፈው አንድ አመት በመልካም የሰብአዊ መብት አያያዝ ጅማሮ ላይ የነበረችው ኢትዬጵያ ቀደም ሲል ወደምትታወቅበት ጋዜጠኞችን አቀንቃኞችን፣ፓለቲከኞችን በደፈናው በጸረ ሽብር ህግ ሽፋን ወደ እስር ቤት የመወርወሩ ባህሪዋ እንድትመለስ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።