አዴፓትክክለኛውንመንገድያዘ – ስለሽ ደስታ

1 min read

ላለፉትሃያሰባትዓመታትየኢዴፓአቋምናአካሄድየተልፈሰፈሰናእራሱንአዋርዶመላውየአማራዉንሕዝብያዋረደ፥ለችግር፥ለመከራ፥ለስቃይ፥ልስደት፥ለእስራትናለሞትየዳረገቡድንእንደነበርየትናንትትዝታችንነው።ሆኖም ግን ላለፉት አሥራ አራት ወራት በነበረው የለውጥ ጭላንጭል ተከትሎ መለስተኛና እራስን ለመሆንእያደረገ የነበረውን የትግል አካሄድ የአማራ በዋናነትም የኢትዮጵን ትንሳኤ ለሚደረገው የትግል እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪና  ጥሩ ጅምር እንደሆነ እያስየዋልን ባለንበት በአሁኑ ወቅት ሰሞኑን በባህር ዳርና በእዲስ አበባ ተከሰተ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት ተብየው ድራማን በተመለከተ ህወሃት በአዴፓ ላይ ያወጣዉን ቅጥ ያጣ፥ እርስ በራሱ የሚቃረንና መሰረተቢስ ክስ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ያሳዘነ ብሎም ያስቆጣ መግልጫ ነው።

በመሆኑም ይህንየወያኔመግለጫአስመልክቶየአዴፓማእከላይኮሚቴ በዛሬው እለት ባወጣው የመልስ መግለጫ የህወሃት ፥ መሰሪነትን፥ ፀረ ኢትዮጵያዊነትንና አጠቃላይ ቁመነዋን ያጋለጠና በትክክል ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ህልውናና መብት እንደሚቆመ ያረጋገጠበት መግለጫ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ የአዴፓ መግለጫ የአማራውን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስደሰተና አልኝታ ድርጅት አለኝ ብሎ ተስፋ እንዲሰንቅና እንዲኩራራ አድርጎታል።

መላውየአማራሕዝብምሆነአጠቃላይየኢትዮጵያሕዝብአዴፓን አሁንበያዘውና ባለውቁመናይበልጥተጠናክሮናእንድወጥሆኖእንዲቀጥል የሁሉም አማራ ሕዝብ ድጋፍ ይሻል። በመሆኑም፥ ኋላ ቀርና ከፋፋይ የሆነውን ጎጠኝነትን፥ እርስ በርስ መጠላለፍን፥ ቂመኝነትንና ራስ ወዳድነትን ሳይበግረው በአማራነቱ ተደራጅቶና እንድ ሆኖ ለመታገል ቁርጠኝነቱንና አጋርነቱን ማረጋገጥ መቻል ይኖርበታል። አዴፓም የመላው አማራ ማህበረሰብ ሙሉ ድጋፍ ማግኘት ይችል ዘንድ፦

1)       በውስጡ ያሉትን እንዳንድ የአማራዉን ጥቅምና ፍላጎት ማሟላት የተሳናቸው፥ ለሆዳቸው ያደሩ፥ ከወያኔ ጋር ግንኙነት በማድረግ የአማራዉን ህልውና የሚፈታተኑና ጥቅመኞችን ለእንዴና ለመጨረሻ መንግሎ መጣል ይጠበቅበታል።

2)   ብቃትናችሎታያላቸዉንወጣቶችበአመራርነት ማስገባት

3)  ከታች ጀምሮ ያሉትን አባላት አንድ ወጥ የሆነ ድርጅታዊ ቁመና እንዲኖራቸው፥ ለድርጅቱ ቀናኢ አመለካከትና ጥራት እንዲኖራቸው የእርማት እንቅስቃሴ በማድረግ ድርጅቱን ሪስትራክቸር ማድረግ።

4)ከአሁን ቀደም በዶ/ር አምባቸው ተጀምሮ የነበረዉን በመላው የአማራ ክልል ሕዝባዊ ውይይቶችን አጠናክሮ መቀጠል።

       በመጨረሻምአዴፓዛሬባወጣችሁትመግለጫመንነታችሁንናለእማራሕዝብተቆርቋሪነታችሁንበግልፅየሚያመለክት መግለጫ በማውጣታችሁና እውነተኛ የሕዝብ ልጆች መሆናችሁን ያስመሰከራችሁበት በመሆኑ የአማራው ሕዝብ ከልብ የተደሰተ ከመሆኑም ባሻገር ከጎናችህ በመቆም አቅማችን በፈቀደና በምንችለው መጠን ለመደገፍ ቁርጠኝነታችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳልን።

ፈጣሪኢትዮጵያንይባርክ !

ሞትለዘረኞችናለገንጣዮች!!

ስለሽ ደስታ

3 Comments

 1. ௐௐௐ እነ”ኢያጎ”ን አፈላልጉን!!!ௐௐௐ
  ௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐௐ
  አራቱ አርበኞችን እኒያ የገደሉት፤
  ፋሺሽቶቹ ናቸው
  በደም የወደሉት።
  ወገንን በሴራ ወዳጅ ተጠግተው፤
  የኛን ሰው ገድለዋል፣
  በግፍ ቀን አድብተው።
  በሸፍጥ ነው የወጉን፤
  እነ”ኢያጎ”ን ያየ ዛሬ አፈላልጉን።
  ክህደትና ሴራው፤
  ተውጠንጥኖ ባልባሌ፤
  በወዳጅ-ጠላት ሥም፣
  ላኩት ከመቀሌ።
  ችግር ተነጋግረን እንደምንፈታበት፤
  ተቀምጠን በሰላም ስንወያይበት።
  በድንገት”ኢያጎ”ን ሳናውቀው እንደነበር፤
  ሸፍጠኛው ማን ይሆን
  ሁሉም ሰው ይበርበር።
  እሱ ነው አጋዳይ ለፋሺሽት-ወያኔ፤
  መረጃ አመላላሽ በግድያው ያኔ።
  አሉባልታዎቹ አንድ በአንድ ወጥተው፤
  ወሬኛው ይጣራ በድምብ ተለይተው።
  እናም በእርግጠኛ ገዳዩን ሕዝብ ያውቃል፤
  ሦስተኛው እጅ ይያዝ አንድ መረጃ ይበቃል።
  እንመርምር ወሬውን እናጣራ ሁሉን፤
  ግርግር ፈጥረው ነው
  እኛን የገደሉን።
  አዎ እነ”ኢያጎ”ፍፁም ካልተያዙ፤
  የሚፈጥሩት ክፋት ፣
  ብዙ ነው መዘዙ።
  ፋሺሽቱ-ወያኔን
  ገዳይና አጋዳይ፤
  ይነገር በይፋ:-
  ሕዝቡ በደምብ እንዲያይ።
  የወንጀሎቹ ምንጭ አልፋና ኦሜጋ፤
  መጀመር አለበት
  በ”ኢያጎ” ፍለጋ።
  ነብስ አይካካስም በሚታይ ቁሳቁስ፤
  ደም ባይከፈልም
  ይቀራል ወይ ሃቁስ።
  ስለዚህ አንርሳ ለግፉ መጨረሻ፤
  አራት ባንዳ አያጠፋም
  ለደም ማካካሻ።
  ከእስር ቤት ተቀምጦ ሁሉን የሚያጋድል;
  እኛ ስንሞትለት ይቆጥራል እንደድል::
  እናም በሸፍጥ እኛን በድብቅ ያስወጉን፤
  እነ”ኢያጎ”ናቸው ለፍትህ አፈላልጉን።
  ௐௐௐ…

 2. የክልሉ ህዝብ መሬት ላይ ወርዶ ችግሩን የሚፈታ እንጅ መግለጫ የማዉጣት፣ የመደራደር፣ የመተቃቀፍ፣ ቃላትን እየቀያየሩ መጠቀምና ህዝብን ማዘናጋት…………. አዴፓ ከጅምሩ በህዝብ ሞትና መስዋእትነት ከወያኔ መንጋጋ ተላቆ እንኳን ከተላላኪነቱ መዉጣቱን ማረጋገጥ አልቻለም የትናንትና ስህተቶቹን አሁንም እየደገመ ነዉ፡፡ ለዚህም ማሳያዉ ባለፉት 30 አመታት የድርጅቱ አባል ስለሆኑ ብቻ ስልጣን ላይ የወጡት አመራሮች አሁንም ስልጣን ላይ ናቸዉ መመዘኛዉም ያዉ ነዉ ( ማን ይመቸኛል)፡፡ ለማኛዉም አዴፓ ከማይድን በሽታዎቹ አንዱ የአቅም ማነስ ነዉ!!!!!!!!!!!!!!፡ ይሄንንም ለማሻሻል ዝግጁ አይደለም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.