ውልክፋ አትደገፍ! – በላይነህ አባተ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ያድነኛል ብለህ ተወዠቦ ተዶፍ፣
ወይራ ሆይ ተመከር ውልክፋ አትደገፍ፡፡

 

ተወይራ ዋንዛ ሥር ውልክፋን ሲፈጥረው፣
በእምብርክኩ እሚሄድ ልፍስፍስ አርጎ ነው፡፡

 

በልግን ተመርኩዞ ራስ ቀና ቢያደርግ፣
እውነት አይምሰልህ ቀጥ ብሎ እሚሄድ፣
ውልክፋ አጎንባሽ ነው ወዲያው እሚል እርፉቅ፡፡

 

እንደ ልጅ አጫዋች ወፌ ቆመች ብትል፣
ውልክፋ ልምሻ ነው ቀጥ ማለት የማይችል፡፡

 

ወስደው የተከሉት ውልክፋን ተዛፍ ሥር፣
ዙሪያ ተጠምጥሞ ወይራን አንቆ እንዲያስር፡፡

 

ውልክፋን አጥንቶ ለማወቅ አመሉን፣
በሰላሳ ዓመት ላይ ስንት ይጨመርልን?

 

ውልክፋ ቀጥ ይላል እያለ እሚሰብከው፣
እድር እቁብተኛው ሰርዶ ወይ ጠሮ ነው፡፡

 

የውልክፋ ዘመድ ጓደኛ ያለው ተክል፣
እንኳን ሊመፃደቅ ሊኮራ ሊጎርር፣
ባፍረት ተሸማቆ ሊደበቅ ይገባል!

 

የሚያኮራ ታሪክ ወይም ፍሬ የለው፣
እንዴት በውልክፋ ይወዛገባል ሰው?

 

ውልክፋ ተብትቦ ቀይዶ ባይዘው፣
ብሳናና በለስ ወይራን ባልደፈረው!

 

ወይራ ሆይ ስለዚህ ተመከር እባክህ፣
አሸክቱ ቁጥቋጦው ዳግም እንዳይወርህ፣
ውልክፋ አትደገፍ ቀጥ በል ራሥህ!

 

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

 

One Response to ውልክፋ አትደገፍ! – በላይነህ አባተ

 1. Egypt follows the Shariya law. Egypt reached a level much better than Ethiopia in all aspects because the whole country of Egypt follows the Shariya law .

  It would have been very wise for the betterment of all Ethiopians, if all of Ethiopia starts following the Shariya law now.

  Currently in Ethiopia the Shariya law is applicable only to married Muslim Ethiopians, if the Shariya law applied to all Ethiopians in the country except listing married Muslim Ethiopians the only people who are allowed to benefit from the Shariya law , then all Ethiopians would have been better off.

  All Ethiopians should be allowed to rip the benefit of following the Shariya law not only married Muslim Ethiopians. Ethiopia would have been a much better country than it is now if Shariya law was followed by all.

  M. A. H.
  July 12, 2019 at 7:31 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.