የአማራና የሱማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በባህር ዳር ተካሄደ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የህዝብ ለህዝብ መድረኩ የተጀመረው በቅርቡ ለተሰውት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው፡፡

በመድረኩ ከአማራ ክልል የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የሀይማት አባቶች በሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር ከተመራውና 100 አባላት ከሉት የክልሉ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ላቀ አያሌው የካራማራን ታሪክ በማንሳት ሁለቱ ህዝቦች ለአገራዊ ሉዓላዊነትና ለፍትህ የከፈሉትን መስዋትነት ዘክረዋል፡፡

“የዛሬው ግንኙነት በአገሪቱ ለዘመናት የተሻገሩ የአንድነት እንቅፋቶችን በጋራ ታግሎ ለመጣል የተደረገ በመሆኑ ትርጉሙ ላቅ ያለ ነው” ብለዋል አቶ ላቀ፡፡

 

የአማራ ህዝብ በተሳሳተ የጨቋኝነት ትርክት አግላይ ፖሊሲዎች ሲጫኑበትና በርካታ ችግሮች ሲገጥሙት መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ይህንን በመታገል ሂደትም የሱማሌ ህዝብና መንግስት ለአማራ ህዝብና መንግስት ያደረጉት አስተዋጽዖ ጉልህ መሆኑን አቶ ላቀ አውስተዋል፡፡

በጅግጅጋ በርካታ የአማራ ክልል ተወላጆች የሚገኙ እንደመሆኑ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ተጠብቆ እየሰሩ እንዲኖሩ የክልሉ መንግስት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማና አካባቢው በተፈጠረው ግጭት 7 ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለው የነበረ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አምስቱን ክልሉ መልሶ በማስገንባት ወደ ስራ ማስገባቱ ተገልጿል፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር ስለአብሮነትና አንድነት ያላቸው አቋም በአማራ ክልል ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቅሷል፡፡

በውይይቱ የሁለቱን ህዝቦች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስሮች የሚዳስሱ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

ጥናታዊ ጽሑፎቹ በዋናነት ሁለቱ ህዝቦች ለአገር ሉዓላዊነትና ነፃነት የከፈሉትን ዋጋ እንዲሁም የሚጋሯቸውን የአብሮነት እሴቶች የሚያጎሉ ናቸው ተብሏል፡፡

ሪፖርተር፦ ራሔል ፍሬው

5 Responses to የአማራና የሱማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በባህር ዳር ተካሄደ

 1. የአማራ እና የሱማሌ ሕዝብ አንድነቱ፤ህብረቱ፤ተሳስቦ መረዳዳቱ፤መዋደድ እና መፋቀሩ ከጥንቱ ጀምሮ የነበረ መሆኑን፤ሌላው ቀርቶ በድግስ እንኳን ክርስቲያን አማራው ድግስ ደግሶ ሲያርድ በእኩል ደረጃ ለእስልምና አማኝ ሱማሌ ሕዝቦች በእስልምና አማኞች ታርዶና ተዘጋጂቶ በየቦታቸው በመሆን በጋራ ደስታቸውን የሚገለጥበት እንድሁም የእስልምና አማኝ የሱማሌ ሕዝብ ሲደግስም በተመሳሳይ መልኩ ይደረግ እንደነበር ታሪክ እና የኢትዮጵያ ምድር ትመሰርክራለች፡፡ “ህወሐት” ወይም ወያኔ በሚባል ዱር አዳሪ ሺፍታ የነበረውን ታሪክ እና አወንታ በመካድ እና በመሻር፤የኢትዮጵያን ምድር ክልል በሚል አጊል ፈሊጥ ሸንሽኖ እና ሰነጣጥቆ፤ ህዝቦቿንም በዝረ እና በጎሳ ሆድ እና ጀርባ በማድረግ ትዳር እንዲፈርስ፤ንብረት እንዲወድም ድህነት እንዲገን ለዘመናት የረጨውን መርዝ ለማክሰም በአሁኑ የተደረገው የአማራ እና የሱማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ በባህርዳር ከተማ የነበረውን ታሪክ እና አዎንታ እድሳት ነውና ምላሹም ጂጂጋም እንዲካሄድ፡ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎችም ይኸው ተግባር ቢከናዎን ወሰን የማይገኝለት ፍቅር እና መዋደድን ይመሰርታል ብየ አምናለሁ፡፡ሐገራችን ኢትዮጵያን መልካም ስራችሁን ይባርክ፡፡

  Avatar for solomon Belay

  solomon Belay
  July 21, 2019 at 1:48 pm
  Reply

 2. More Mustefes for Ethiopia – a human being and world class thinker.
  I have a slight fear that he may be overqualified/misfit in a country where hate-mongering has become the norm rather than the exception. I take solace on the other hand that the “silent majority”, regardless of ethnic background, are with him – peaceful and forward looking. I hope to see Mustefe with a portfolio at the Federal cabinet, including the top job. Inshallah!

  Avatar for Kedir Setete

  Kedir Setete
  July 22, 2019 at 9:59 am
  Reply

 3. አንተ ምጡቅ ሰው ሙስጠፌ መሀመድ፡ ፈጣሪ አብዝቶ ጥበብን እውቀትን ይግለጥልህ እድሜና ጤና ይስጥህ
  ከክፉዎች አይን ያውጣህ፡፡ በዚሁ ቀጥል የሀገራችን አለኝታ ነህ፡፡ ከፈጣሪ በታችን ያለችሁ ተስፋዎቻችን አንተና እንዳንተ የሚስቡ ናቸው፡፡ አንተንና መሰሎች ፈጣሪ ያብዛልንና፡፡

  Avatar for ethiopiazelalem

  ethiopiazelalem
  July 24, 2019 at 6:26 am
  Reply

 4. Muster should replace the liar and fake PM Ahmed.

  Avatar for Meseret

  Meseret
  July 24, 2019 at 8:11 am
  Reply

 5. አንተ ምጡቅ ሰው ሙስጠፌ መሀመድ፡ ፈጣሪ አብዝቶ ጥበብን እውቀትን ይግለጥልህ እድሜና ጤና ይስጥህ
  ከክፉዎች አይን ያውጣህ፡፡ በዚሁ ቀጥል የሀገራችን አለኝታ ነህ፡፡ ከፈጣሪ በታችን ያለችሁ ተስፋዎቻችን አንተና እንዳንተ የሚስቡ ናቸው፡፡ አንተንና መሰሎች ፈጣሪ ያብዛልንና፡፡

  Avatar for Termama

  Termama
  July 25, 2019 at 1:38 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.