“ሕገ መንግስቱ ሲጸድቅ እኔ ሐሳብ ሰጥቼበታለሁ፣ ህዝብ ተወያይቶበታል” አቶ በቀለ ገርባ

1 min read
8

በርካታ የኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞችና ልሂቃን ጉዟቸውን ወደ መቀሌ በማድረግ፣ በዚያም፣ በተለይም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሕግ መንግስትና ፌዴራል አወቃቀር ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው።

ከአንድ ሳምንት በፊት ዶር ሕዝቄል ጋቢሳ ፣ እርሳቸው “ሕብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም” የሚሉት ግን በብዙዎች ዘንድ የጎሳ ፌዴራሊዝም ተብሎእ የሚጠራው የአሁኑ የፌዴራል አወቃቀር እንዲቀየር የሚፈለጉ አካላትን፣  በኢትዮጵያ አሃዳዊ ስርዓት እንዲመጣ የሚፈልጉ ናቸው በማለት፣ አሁን ያለውን የፌዴራል አወቃቀር መቃወም ፌዴራሊም እንደመቃወም አድርገው ለማቅረብ የሞከሩ ሲሆን፣  ወደ አሃዳዊ ስርዓት ከዚህ በኋላ መመለስ የማይቻል ነገር እንደሆነ ግለጸው ነበር።

በወቅቱ የአረና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ አሃዳዊ ስርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቅ የፖለቲካ ቡድን እንደማያውቁ ገልጸው፣ ፌዴራሊዝም የሚቃወም በሌለበት ሁኔታ ስለ አሃዳዊ ስርዓት ማውራት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ በመጠየቅ ፣ ጉዳዩ የአሃዳዊ ስርዓት ጋር ሳይሆን ፣ ፌዴራሊም እንዳለ ሆነ፣ ግን የትኛው አይነት ፌዴራሊዝም የሚለው ላይ እንደሆነ ለማመላከት ሞክረዋል።

በዚህ ሳምንት ደግሞ ሌላው የኦሮሞ ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባም በመቀሌ ተገኝተው፣ አሁን ያለው ሕግ መንግስት ፌዴራል አወቃቀር ምንም ችግር እንደሌለበት፣ እንደው ችግሩ ያለው ፌዴራሊዝሙ በትክክል ካለመተግበሩ የተነሳ እንደሆነም በመግለጽ፣ “በአገሪቷ ላለው የጎሳ ግጭትና መፈናቅሎች ሕገ መንግስቱና ምክንያቱ ፌዴራል አወቃቀሩ ነው” የሚለውን አስተያየት እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።

ሕግ መንግስቱ ሕዝብ ያልመከረበት ፣ በጉልበት በሕዝብ ላይ በወቅቱ ስልጣን በእበጡት በሕወሃትና ኦነግ/ኦህዴድ ፖለቲከኞች በሕዝቡ ላይ የተጫነ እንደሆነ ብዙዎች የሚናገሩት ነው። ሆኖም አቶ በቀለ በህያል የተጫነ ነው በሚለው አይስማሙ። ” እኔ ሐሳብ ሰጥቼበታለሁ.. ህዝብ ተወያይቶበት ያጸደቀው ህግ መንግስት ነው” ሲሉ አሁን ያለውን ሕግ መንግስትና አወቃቀር መቀየሩ ላይ እንደማይሰማሙ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ በቀለ ገርባ የኢትዮጵያ መንግሥት ክልላዊ መንግሥት ለመመሥረት የቀረቡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ወደ ኃይል ከማዘንበል እንዲቆጠብ አሳሰቡ። «ወደ ኃይል ከማዘንበል እና ጦር ከማዝመት» ይልቅ የዜጎችን ጥያቄ በጊዜ መመለስ አስፈላጊ ነው» ብለዋል።