ሰኔ 15 በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ ጉዳዮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ

1 min read

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈተዋል፡፡

ከተጠረጣሪዎች መካከል በነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 57ቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል።

እነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን በተመለከተ ደግሞ ችሎቱ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ትናንት በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 13ኛ ወንጀል ችሎት ለሦስተኛ ጊዜ ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን ከተጠርጣዎች መካከልም ከወንጀሉ ነፃ የተባሉ 57 ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡

በዚህ መዝገብ 218 ተጠርጣሪዎች የተያዙ ቢሆንም ቀደም ሲል 103ቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ መለቃቀቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ኢዜአ