የሕብር ሬዲዮ ነሐሴ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በትግራይ አዲስ የለውጥ ተስፋ አለ ወይስ ወሬ ነው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ እውን ከሕወሓተ የተለየ አጀንዳ ነው የሚያራምዱት? የኤርትራስ ወታደራዊ ዝግጅት ለማን ነው ? በጉዳዩ ላየ የተደረገ ሰፋ ያለ ውይይት ? (ያደምጡት)

በሽብር የተጠረጠረው  ጋዜጠኛ ምሥጋናው እህት ጋር የተደረገ አጭር ቆይታ

መቋጫ ያልተገኘለት የወጣት ኢትዮጵያኖች ወደ ሞት ጉዞ (ልዩ ዝግጅት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ በዓለም አቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ

ዶ/ር አብይ እና ሕወሓት እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

ኦብነግ  የመገንጠል አቋሙን እንዳልቀየረ  አስታወቀ

የሀይማኖት አባቶች የቤተ ክርስቲያን ውድመት እንዲቆም አስጠነቀቁ

ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም   ለከሃዲዎች እና ለሰላዬች  ትእግስት  የሌላቸው መሪ ተባሉ

በሽብር የተጠረጠረው የኢትዮጲስ ጋዜጠኛ ቤተሰብ ክሱ አስደንግጦናል አሉ

አዲስ አበባ አጣብቂን ውስጥ መውደቁዋ ተገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል

 

One Response to የሕብር ሬዲዮ ነሐሴ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

 1. አዝማሪና ታሪክ፦
  በተግባር ሲታይ አዝማሪነት ማለት ዋሽቶ መብላት ማለት ነው።ይህም የመጣው ከጥንት ከጠዋቱ ከከተማ አመሰራረት ባህሪ ጋር የተያያዘ ነው።በጥንት ጊዜ ከተሞች ሲመሰረቱ በመጀመሪያ በሰራዊት ሰፈርነትና ለወታደር መኖሪያነት በመሆን ነው።
  ቀጥሎም አዝማሪዎችና ሴትኛዳሪዎች ለማዝናናትና መተዳደሪያ ፍለጋ ወታደሩን ተከትለው ይገባሉ።
  በዚህ አይነት ከተመሰረቱት ሰፈሮችና ከተሞች አንዷ ጎንደር ናት።
  ጎንደር የሚለው ስያሜዋን ሳታገኝ ጥንት በጌምድር ከመባሏም በፊት አካባቢው የሚኖሩት ቤጃዎች(በጌዎች)ና ቅማንቶች ነበሩ።ኋላ ላይ ደግሞ በዚያን ጊዜ ተገልለው እንዲኖሩ የተደረጉ ፍላሾችና ባለጆች ተወስደው እዚያ እንዲሰፍሩ ተደረጉ። እያደርም አካባቢውን ከቱርክና ግብጽ ለመከላከል ሲባል የተወሰኑ የነገስታት ልጆች ሰራዊታቸውን ይዘው በመስፈራቸውን ተከትሎ ማህበረሰቡ ባጠቃላይ አማርኛ ተናጋሪ ሆነ። አዝማሪቤትና ሴትኛዳሪነትም በአካባቢው እየተበራከተ መጣ።
  እንግዲህ ይህ የአዝማሪ ሙያ በባህሪው እውነቱን ውሸት ውሸቱን እውነት በማለት፡ፈሪውን ደፋር፡ድሃውን ሃብታም፡ሴቱን ወንድ፡ጨካኙን ጀግና— በማለት ዋሽቶ የመብላት ስራ ነው።ይህም ባህሪና ተግባር በአካባቢው ማህበረሰብ ላይም ተመሳሳይ ስነልቦና መፍጠሩ በስፋት ከብዙ ዘመን በኋላም ይታያል።
  የዚህ ስነልቦና ውጤትም ያስከተለው ችግር እውነተኛ ታሪክን ወደጎን እስከማለትና ተረትና ፈጠራን እስከማምለክ የደረሰ ሆኗል። ሰርቶ ከማሳየትና በስራ ከመኖር ይልቅ በሴራና በተንኮል ልቆ መገኘትን እንደክብር ማየት ዋና መገለጫ እየሆነ መጥቷል።
  ለምሳሌ ያክል፦ ጎንደርን በሚመለከት የሚዜሙና የሚነገሩ ትርክቶች ጽብዛኛው ወይም ሁሉም ማለት ይቻላል ፈጠራና ድርሰት፡የአዝማሪ ተረትና የሴራ ፖለቲከኞች ትርክት ነው።ፈጠራውን ትተን እውነቱ ስንመለከት-
  -ጎንደር ከተማን የመሰረቷት ከሌላ ቦታ የመጡ መሳፍንቶች ናቸው
  -የፋሲልን ቤተመንግስት የሰሩት ካቶሊኮች ናቸው
  -ጎንደርን ሲገዙ የኖሩት ሁሉም የሌላ ቦታ ሰዎች ሲሆኑ ለምሳሌ በመጀመሪያ ከ100 አመታት በላይ የመሃል አገር የነገስታት ልጆች ፡ ቀጥሎም ከ100 አመታት በላይ የየጁ ኦሮሞዎች ናቸው።ይህ ግን ለአዝማሪ ስለማይመችና የእለት እንጀራን ስለሚያሳጣ አይነገርም።
  -ቴዎድሮስ ፋሲል ቤተመንግስትን በእግራቸው ረግጠውት አያውቁም፡በተደጋጋሚ ጊዜ ስልጣኑን ለወደዳችሁት ስጡት እኔ እንደሁ እንደ— እየዘረፍኩ መብላት አያቅተኝም በማለት ይዝቱ ነበር፡ሴትና ሸክም አስጠቂዎች ናቸው ይሉ የነበረና ወደ ሩቅ ቦታ ሲሄዱ ሚስታቸውን ተዋበችን ዋሻ ውስጥ ደብቀው ይሄዱ ነበር፡እኔን ፈጣሪ የላከኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ልቀጣ ነው ይሉ ነበር፡በሚሰሩት ግፍና ጭካኔ በተደጋጋሚ በጸጸት ምርር ብለው ያለቅሱና ወዲይኣው እንባቸው ሳይደርቅ ጭካኔአቸውን ይጀምሩ ነበር፡ህጻናትና ሴቶችን በሳር ቤት አጉረው አቃጥለዋል፡አንድ ምስኪን ገበሬ በመድፍ ፊት እንዲቆም አድርገው በመድፍ የረሸኑ በታሪክ ብቸኛው ሰው ናቸው፡እግርና እጅ ጎንድሸው ወደ ገደል ይወረውሩ ነበር፡በመጨረሻም ቤተሰቦቻቸውን የሚያስጠጋቸው ጠፍቶ በስደትና በየመንገዱ ወድቀው ባክነው ቀርተዋል።
  -ቴዎድሮስ በችግር ምክንያት ያደጉት በየሰዉ ቤት ሲንከራተቱ፡ከፍ ሲሉም በአሽከርነት በየ መሳፍንቱ ቤት ሲያገለግሉ የኖሩበመጨረሻም መሯቸው በየጫካውና በየዱሩ ሲንከራተቱ ብዙ ያሳለፉ በመሆናቸው ለጭካኔ ባህሪያቸው ከፍተኛውን አስተዋጾ ያደረገው ይሄው ያለቤተሰብ በችግር ማደጋቸው ነው።
  በዚያን ጊዜ የነበረች አንድ ሴት ቢቸግራት-
  “አንድግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
  ለብልቦ ለብልቦ አቃጥሎ ፈጃችሁ “
  በማለት አንግራጉራለች።
  -እቴጌ ጣይቱ የየጁ ኦሮሞ የልጅልጅ ናቸው
  —–
  እንግዲይ ይህ ሁሉ ሃቅ ለአዝማሪ ምኑም ሳይሆን በተቃራኒው ጨካኝነትንና ግፈኝነትን እንደጀግንነት በመቁጠር – ሰው የሚፈጀውና የህዝብ እልቂትን የአገር ወዳድነት መገለጫ በማመሰል ግፍንና ጭካኔን በማበረታታት፡ጎጠኝነትንና ትምክህተኝነትን ኢትዮጵያዊነት በማስመሰል፡እውነተኛ ታሪካችንን መማሪያ መሆኑ ቀርቶ በተረትና ፈጠራ በመተካት— ትውልድን ወዳልተገባ ባህሪና ማንነት እየገፋ ከትክክለኛ ኢትዮጵያዊነት ስነልቦና ሳይደርስ በጅምር የቀረ ማህበረሰብ አድርጎት ይገኛል።
  ከእስክስታው ጩሀትና እሽኮለሌው ውጪ ቴዎድሮስን ያለስራቸው በማግነን በእሳቸው ስም ራስን ለማጽናናትና የፈጠራ ማንነት ለገንባት በሚደርአገው ፈጠራ ውስጥ በጣም የሚያስገርመው ፡ በዚያን እንኳን ከለር ፎቶ ቀርቶ ራሱ ፎቶ ባልነበረበት ወቅት የተነሳ ፎቶ በማስመሰል፡በችግርና በመከራ ያደጉትን ቴዎድሮስን የሆሊውድ ፈረምጅ ከዚያም አልፎ መልአክ አስመስሎ በኮምፒውተር በመሳል ፡የኮምፒውተር ጸጉር በመቀባት ያልነበረና የሌለ በስራፈቶች የእጅ ስራ እውነተኛውን ጥቁር አበሻነታቸውን አጥፍተው ድርሰት አድርገዋቸዋል።ፎቷቸውን በተመለከተ ግን በጥንት ዘመን የተነሱትና የልጃቸውንና የልጅልጆቻቸውን መልክ ማየት በቂ ይሆናል።በታሪክ ጸሃፊዎች መሰረት ከሄድን ደግሞ ቴዎድሮስ ከሌላው አበሻ ሁሉ በተለየ ሁኔታ ጥቁርና አይናቸው አነስ አነስ ያሉ ናቸው።ጸጉራቸው እንደማንኛውም የዚያ ዘመን ሽፍታ ነበር፡እሳቸው በችግር ያደጉ መሆናቸው ሳይረሳ—-
  እንደዚያ ቢሆንማ- ደርግ የጨፈጨፈው የአገር ባለውለታ፡የተማረ ወጣት፡መጡቅ ምሁራንና የጦር መኮንኖች— ወዘተ እልቂት ለአገር ሲባል የተደረገ— ወያኔ የጨረሰችውና ያመከነችው ትውልድ ህገመንግስቱን ከጥቃት ለመከላከልና ህዝብን ከሽብርተኝነት ለመጠበቅ የተደረገ ስለሆነ መጭውም በሀገርና በህዝብ ስም ህዝብና አገር መውደም ፡ትውልድ መደምሰስ ይኖርበታል ማለት ነው።
  ኢትዮጵያዊነት የነጻነትና የአንድነት እውነተኛ ማንነት እንጂ የጎጠኝነትና ትምክህተኝነት ፡የግፍና ጭካኔ መገለጫ አይደለም።
  ከአዝማሪ ተረትና ከሴራ ትርክት ይልቅ እውነተኛ ታሪካችን ማንነታችን ነው።
  ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም!

  Avatar for Abbayneh

  Abbayneh
  August 13, 2019 at 4:27 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.