በአፋር ዳሎል የጠፋቸው እስራኤላዊት ተማሪ ህይወቷ አልፎ ተገኘች

1 min read

በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ ለጉብኝት ከሄዱ እስራኤላውያን ተማሪዎች መካከል ተነጥላ ጠፍታ የነበረችው እስራኤላዊት ወጣት ዛሬ ጠዋት ሞታ ተገኘች።
አያ ናማና የተሰኘችው ወጣት አስክሬን ዛሬ ከሰዓት ወደ አምቡላንስ መወሰዱን አንድ የአፋር ክልል ባለስልጣን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፍ የቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ አህመድ አብዱልቃድር እስራኤላዊቷ መጥፋቷ ከታወቀበት ከትላንት ጀምሮ ሊሊቱን ሙሉ ፍለጋ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸዋል።
ለሊቱን ሙሉ ሲደረግ በነበረው ፍለጋ የክልሉ መንግስት ኃላፊዎች፣ የበረሃሌ ወረዳ ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደዚሁም የአካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን አስረድተዋል። የወጣቱ አስክሬን በአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ጠዋት መገኘቱንም አክለዋል።

Entführung Touristen Äthiopien (picture-alliance/dpa)
“ሬሳው ዛሬ ጠዋት ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው የተገኘው። እዚያ አካባቢ ጸሀይ በጠዋት ስለምትወጣ የአካባቢ ነዋሪዎች ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ነው [ለፍለጋ የወጡት]። ከመቶ በላይ ሰው ነው ዛሬ ለፍለጋ የተሰማራው። ‘ድሮን’ም ነበር። እነዚያ ሰዎች እስከ ሶስት ሰዓት እየፈለጉ ነበር። ወደ መመለሻው ሳይሆን ወደ ፊት፣ ወደ አንድ ኪሎ ሜትር ሄዳ ነው የተገኘችው። ሬሳዋ እዚያ ነው የተገኘው። እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ እዚያው ነበሩ ከዚያ በኋላ ሬሳው የሚነሳበት መሳሪያ መጥቶ፣ አንስተው በአምቡላንስ ወደ መቀለ ነው የላክነው። አውሮፕላን በአቅራቢያው እዚያ ስለሆነ ነው” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
እስራዊላዊቷ ወጣት ሞታ የተገኘችበት ዳሎል የተሰኘው ቦታ ከባህር ጠለል በታች 116 ሜትር የሚወርድ ሞቃታማ ቦታ ነው። በአካባቢው ባለው እስከ 50 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሚደርሰው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ወደ

DW Amharic

https://www.zehabesha.com/israeli-missing-in-ethiopia-student-from-technion-goes-missing-during-hike-in-ethiopian-desert/

1 Comment

  1. News by Ethiopian Review claims that up to 3000 Oromo Students are sent to what it described as “concentration camps” in Afar Region, arid region in the Eastern part of Ethiopia, after they were detained in a round up.

    The news source also published a picture of shaved young Ethiopians crowded in queue.

    On the contrary, other sources in government administrative structure do have a totally different narrative. Addis Ababa City website reports that over 3500 homeless youth in Addis Ababa are mobilized for skills training to be moved to Addis Raey training center in Afar region.

    According to Addis Ababa City report, it seems that the skills training is a cooperative project between Addis Ababa City Administration Labor and Social Affairs Bureau, EFDR Metals and Engineering corporation and Elshaday charity organization. The report makes no mention of the ethnicity of the street children.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.