ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ዳሬ ሰላም ገብቷል

Filed under: ስፖርት |

ቡድኑ ዳሬ ሰላም ሲደርስ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ እና ሌሎች አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም አዛምን 1ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

ነሃሴ 18 የመልሱ ጨዋታ ዳሬ ሰላም ላይ ከአዛም ጋር የሚያደርገው ፋሲል ከነማ ለጨዋታው በአዲስ አበባና ባህርዳር ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በዚህ ጨዋታ ላይ ቡድኑ ባህርዳር ላይ ያደረገውን ጨዋታ አሸናፊ ያደረገውን ግብ ያስቆጠረው በዛብህ መለዮ በመልሱ በጉዳት ምክንያት ጨዋታ አይሰለፍም፡፡

በሌላ በኩል በባለፈው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ የወጣው ግብ ጠባቂው ሚካኤል ሳማኪ ከጉዳቱ በማገገሙ ተሰላፊ ይሆናል ተብሏል፡፡

@AmharaSport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.