ሕወሓት ተደምራለች ግስጋሴ ወደ አራት ኪሎ!? – አብርሃ ደስታ

1 min read
4

የሰሞኑን የፖለቲካ ሽር ጉድ ላየ የኦዴፓ/ኦህዴድ እና የሕወሓት ነገር ፍቅር አያረጅም የሚለውን የምኒልክ ወስናቸውን ዘፈን የሚያስታውሳቸው አሉ። የመቀሌው ጉባዔ የእነ አብይ ዝምታ ብዙ ትርጉም አለው። በአንድ ወቅት ጌታቸው ረዳ ክንውን አትንኩት ሁዋላ መመለስ ያስቸግራል አይነት ንግግር አድርጎ ነበር። እና አብርሃ ደስታ የአረና ሊቀመንበር እንደሚለው ሕወሓት ተደምራለች።ያው ክንውን ዳግም ጎትተው አምጥተዋል። መጨረሻውን እናያለን።ለሁሉም የአብርሃም ጽሑፍ ያንብቡት ሼር ያድርጉት

ባልተያያዘ ዜና ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተደምራለች። “እንድንደመር አዲስ አበባ ስንመጣ እንዳታስረን” የሚል ልምና አቅርበዋል። የማይታሰሩ ከሆነ … አሁን (ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ) ማንም የህወሓት ካድሬ ዐብይን እንዳይሳደብ ተነግሮታል። “መሽረፈት” የሚል ቃል ዳግም ላንሰማው ነው። “ዐብይ ናይና” የሚሉበት አጋጣሚም እየፈለጉ ነው። ድሮም ላለመታሰር ነበር ይህን ሁሉ ማንገራገር። “መብሰሉ ላይቀር ማገዶ ፈጀ” አለ ያገሬ ሰው! የህወሓት ሰላዮች! በሉ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ! እናንተ ከመጣችሁ ብዙ ነገር ተበላሽቷል -መቀለ። ከተማችን ወደ ድሮ ሰላማዊ ህይወቷ ትመለሳለች!