የጠየቅነው ጥያቄ እስከሚመለስ የሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት ይቀጥላል (ማህበረ ቅዱሣን)

1 min read

በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ችግር እስከሚቆም እና መንግሥትም ጥያቄያችንን ሳይሸራርፍ በትክክል እስከሚመልስልን ድረስ በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃችንን እንቀጥላለን።
የአገራችን ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የገጠመንን ችግር አሳሳቢነት በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃችንን እንቀጥላለን ያለው መግለጫው ኮሚቴው ከመንግሥት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ማድረጉን ገልጦ የተጀመረው ከዳር ሳይደርስ እንደማይቆም መሥዋዕትነት ለመቀበል መዘጋጀቱንም አስገንዝቧል።

መስከረም 4 ቀን ሊካሔድ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ መልስ ከጠሰጠበት የኦሮምያ ቤተክህነት መቋቋም ጥያቄ ጋር እንደማይያያዝ በጋዜጣዊ መግለጫው የተነገረ ሲሆን ሰልፍ የመጥራቱ ዋና ምክንያት በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት እንዲያሰቆም መንግሥትን ብንጠይቅ መፍትሔ በማጣታችን ከወር በፊት ጀምሮ ቀጠሮ የተያዘለት እንጂ ከኦሮምያ ቤተ ክህነት ጥያቄ ጋር እንደማይገናኝ በመግለጫው ተገልጧል።

ስለ ሰላማዊ ሰልፉ አስፈላጊነት ፣ዓላማው ምን እንደሆነ እና ከሰልፉ የምንጠብቀውን ውጤት በተመለከተ ዓርብ መስከረም ሁለት ቀን 2011 ዓ፣ም ዝርዝር መግለጫ የሚሰፅ መሆኑን የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጠው ሰልፍ ማድረግ የክርስቲያን መገለጫ ባይሆንም ሸልፍ ለመጣት የተገደድነው አማራጭ በማጣት መሆኑን አስገንዝቧል።

የአብያተ ክርስቲያን መቃጠልእና መዘረፍ ፣የምእመናን መታረድ፣መሰደድ እና ንብረታቸው መዘረፍ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት በመሔዱ ሰላማ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ አስተባባሪ ኮሚቴው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

1 Comment

  1. mahibrekidusan leboch mindegnoch; yalekakisalu tikimachew endakerbachew

    freeloaders, MK==mahibrekidysan yesim kidus ye …rikus

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.