መንግሥት የሰላማዊ ሰልፉን አዘጋጆች እጅ መጠምዘዙን ያቁም !!

1 min read

መንግሥት ሕግ እና ስርዓትን ማስከበር ባለማቻሉ ዜጎች በብሄር ማንነታቸው፣በሀይማኖት ልዩነት ሲፈናቀንምሉ፣ሲገደሉ የዕምነት ተቁዋማት በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ሲቃጠሉ በለውጥ እና ለውጥ ተቃዋሚዎች ትርክት ብዙ ጉዳት ደርሱዋል። የመንግሥት ጉልበት ሕዝብን እና አገርን በሚያሸብሩ ላይ ሳይሆን በተቃራኒው መሆኑ በተጨባጭ እየታየ ነው ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቁዋም ለመንግሥት ያቀረበችው ጥሪን ምላሽ ነፍጉዋል።በስርዓቱ ባለስልጣናት እና አክራሪ ሀይል ከጀርባ የተደገፈው ወገን በተቃራኒው የፈለገውን አድርጉዋል።የቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫ በሕዝብ ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥቱ መገናኛ ብዙሃን ከአንዴም ሁለት ጊዜ እንዲታፈን ሆኑዋል።ይህ የመንግሥት የንቀት እርምጃ በተዘዋዋሪ ለአጥፊዎች የልብ ልብ መስጠቱን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ለማሳወቅ ልጅም አስተዳደር ደብዳቤ መጻፋቸውን ተከትሎ የተደረጁ ሀይሎች ቆንጨራ እና ዱላ ይዘው አደባባይ ወጥተው ሁለት ክርስቲያኖችን ገድለው በትንሹ ስድስት አቁስለዋል። ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል ሞክረው በክርስትያኑ እና በቀረውም ነዋሪ ርብርብ ለጊዜው ተርፉዋል።

በኢትዮጵያ የሽብር ሀይል ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ በመንግሥት መዋቅር ጭምር እየተጠቀመ ሕዝብን በሀይማኖትብእና በብሄር ለማጫረስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርግ ውል በሚል ጥሪ ሲቀርብ ቆይቷል። መንግሥት ይህን አልሰማም።ዛሬ የመከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹሙ ለመንግስት ልሳን ቀርበው ኢትዮጵያ ውስጥ አይ ኤስ ያሰለጠናቸውን ይዘናል።ተጨማሪ ለመያዝ እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል። እነዚህ እነማን ናቸው? በአደባባይ ሕዝብን በሀይማኖት ለማጫረስ ፣አገር ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ወገኖች መንግስት ጉያ ውስጥ ይፕተደበቁ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ መንግስት ናቸው በሚባልበት አገር የተያዙት እነማን ናቸው? ግልጽ መልስ ያስፈልጋል።

የመስከረም 4/2012 የተጠራውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ እይደረሰ ያለውን በደል ግድያና አካል ማጉደል፣በሀይማኖት ተቁዋማት ላይ ቤተ ክርስቲያንን እና የያዘችውን ታሪካዊ ቅርስ ማቃጠል በተመለከተ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማክሸፍ ህገ ወጥ ጫና በአስተባባሪዎቹ ላይ እየተካሄደ ነው።

በሰላማዊ ሰልፍ ጠሪዎች ላይ በተለያዩ መንገዶች ከሚደርሱ የቀጥታ እና ከእጅ አዙር ከደህንነት ማስፈራሪያ አልፎ ከአስተባባሪዎቹ አንዱዋ ትላንት በአዲስ አበባ ፖሊስ ታስራ ተለቃለች ። ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ሀሳባቸውን በአደባባይ እንዳይገልጹ፣የአማኞቹ አንድነት እና ሰላማዊ ሆኖ ገፍቶ በዚህ ደረጃ መውጣትን ቤተ ክርስቲያን አትፈርስም ሲሉ የነበሩ ባለሥልጣናትን ሊያስፈራ አይገባም ነበር። ይህ መሰሉ ማስፈራራት እና እጅ ጥምዘዛ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን የኖረ የኢህአዴግ በሽታ ነው። ዛሬም ተረኛ ነን ያሉት ኦዴፓዎች እየደገሙት ነው።የማያዋጣ የአፈና መንገድ መሆኑን ግን ማወቁ ይጠቅማል።

አቶ መለስ ዜናዊ ምርጫ 97ን ካጭበረበሩ እና የሕዝብ ድምጽ ከዘረፉ በሁዋላ በጊዜው የነበረውን ቅንጅት የጠራውን የሶስት ቀን ከቤት ያለ መውጣት አድማ ለማስቀረት ብዙ ርቀት ሔደዋል።ከጸሐይ በታች እንወያያለን በሚል ከማስፈራራቱ በሁዋላ በዲፕሎማቶች ጣልቃ ገብነት አድማውን አሰርዘዋል።የተባለው ከጸሐይ በታች ውይይት የውሃ ሽታ ሆኖ ራሳቸው ቀርተው እነ በረከትን ልከው የይስሙላው ውይይት ሰኞ ተጀምሮ ረቡን ከሸፈ። ድምጼ ይከበር ያሉትን ጨፍጭፈው በዓለም አቀፉ ጫና ይጠቅመኛል ብለው ያቋቁዋሙት አጣሪ ኮሚሽንን በአብላጫ ድምጽ መንግሥት ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የወሰደውን ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ለማጋለጥ የሞከሩትን ቤተ መንግሥት ጠርተው ጎራዴው በእጃችን ነው ያለው ሲሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል። ጥቂት እውነተኞች ሪፖርቱን ይዘው ወጡ።ወንጀሉ ተጋለጠ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ብጹአን አባቶችን የመንግሥት ጥበቃ ተነፍጉዋት ሁከተኜች እና አሸባሪዎች ያቃጠሉትን አንሰራም ሲሉ ተቃውመዋል። ጭራሽ ሀላፊነቱን ያልተወጣው መንግስታቸው መውቀስ አስቆጥቷቸዋል። የሲኖዶሱ መግለጫ የታፈነው እሳቸው በሚቆጣጠሩት አስተዳደር ስር ባሉ መገናኛ ብዙሃን ነው።

የስልክ አስተባባሪዎች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጠሩት ከጀርባ በደህንነት ማስፈራሪያ አንሰርዝም ያሉትን ሰልፍ ለማስቀረት ነው። ይህ ቢሆን በህገ ወጥ መንገድ በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥፋት ያደረሰውን ሀይል ከማበረታታት ያለፈ ትርጉም የለውም። መንግሥት የጸጥታ ስራውን በአግባቡ አለማስጠበቅ እና የደህንነት ስጋት አለ ብሎ ሰልፉን ማሰረዝ አሁንም ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ ሀይል መኖሩን ያሳያል።ይህ ደግሞ የመንግሥትን አቅመቢስነት ካልሆነ ጥንካሬን አያሳይም።

በህገ መንግስቱ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ መብት ነው። የመስከረም 4/2012 ሰላማዊ ሰልፍ የሕዝብን ሞራል የሚነካ፣የዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚጎዳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ዜጎች ጥያቄ በጠየቁ ቁጥር በአደባባይ ሕዝብ የሚያሸብሩትን የታገሱ መሪዎች “ፖለቲካ ውስጣችሁ” ገባ በሚል ጭንብል ለማፈን መሞከር ጉዳቱ የከፋ ነው። የሀኪሞችን እና መምህራንን የደሞዝ ጥያቄ ከመፈንቅለ መንግሥት ጋር ለማያያዝ የሞከረው የዶ/ር አብይ አስተዳደር ለፖሊሶሽምች ስልጣን ላይ ከወጣ በሁዋላ እንኳን በሁዋላ ሁለት ጊዜ ደሞዝ ጨምሩዋል። ለፖሊሶች ደሞዝ መጨመርን የሚቃውም የለም።አቅም የላቸውም ተብሎ የሚታሰቡ ሀኪሞች እና መምህራን ሲጠይቁ ግን ጉዳዩን በመፈንቅለ መንግሥት ስም ለማሸማቀቅ መሞከር አፈና ነው የቤተ ክርስቲያኑዋን ሰላማዊ ሰልፍ አክራሪዎች ሰሞኑን ሲያደርጉት የነበረውን ጭቃ መለጠፍ እና ህገ ወጥ ጥሪ መንግሥት ሊያስቆመው ሲገባ ያንን ሽፋን አድርጎ ጫና መፍጠሩ ተቀባይነት የለውም።

የአገር ሰላም እና አንድነት የሚረጋገጠው ዜጎች በማንነት እና በሀይማኖታቸው ሳቢያ ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመባቸው መቀጠሉ ነው። ዜጎች የፈለጉትን የማምለክ፣የፈለጉት ቦታ የመኖር መብታቸውን አደጋ ላይ ከምንም ጊዜ በላይ የጣለ ስርዓት በተለያዩ ተልካሻ ምክንያቶች ሽፋን ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴን ለማፈን መሞከር ትርጉም አልባ ጫና ነው።

የመንግሥት ጥንካሬ ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ እንጂ በሰላም እና ደህንነት ሽፋን የዜጎችን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ማፈን ሊሆን አይገባም እና የመስከረም 4/2012 ሰላማዊ ሰልፍ ጠሪዎችን ማሸበር እና እጅ ለመጠምዘዝ መሞከር ይቁም እንላለን።

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!

ህብር ራዲኦ