ኢዜማ ፕሮግራሙን ለመቐለ ነዋሪዎች አስተዋወቀ

1 min read

 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የፓርቲውን ፕሮግራም ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች አስተዋወቀ።

የውይይቱን መድረክ የከፈቱት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዱዓለም አራጌ ለፓርቲው አመራሮች ለተደረገላቸው አቀባበል የክልሉን መንግስትና የመቐለ ከተማ ነዋሪዎችን አመስግነዋል።

የፓርቲውን ፕሮግራም ያስተዋወቁት አቶ ሀብታሙ ኪታባ በበኩላቸው ኢዜማ በፌዴራላዊ ስርዓት ግንባታ ያልተማከለ የአስተዳደር ስርዓትን በመከተል ያምናል ብለዋል።

ህገመንግስቱ ከግለሰብ መብት ይልቅ ለቡድን መብት ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ የዜጎችን ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሊሻሻል እንደሚገባው የኢዜማ እምነት ነው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ጥያቄዎቹም በኢዜማ አመራሮች መልስና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.