አቡን ሆይ! አብ የሚሆኑ መቼ ነው? – በላይነህ አባተ

1 min read

 

ቁርጥ እንደ ሥምዎ፤ በአብ እንደሳለው ግዕዙ፣
እባክዎን አቡን ሆይ! ልጅ ጠባቂ አባት ይሁኑ!

ለሰላሳ ዓመት በትዝብት፤ እንደ ዘገበው ታሪኩ፣
እንኳንስ ተግተው በግዎን፤ ተርጉም ቀበሮ ሊያድኑ፤
ቤተ-ክርስትያን ስትነድም፤ ውህ ሲረጩ አልታዩ፡፡

ጳጳስ ሆይ!

እንደ ማገዶ ስትነድ፤ ቤተ-ክርስትያን ተቃጥላ፣
ተሸራሹና ቁጪ አሉ፤ እንደ እሳት ሟቂ ተምድጃ!

ምን ያህል ሆድን ቢመርጡ፤ ምን ያህል መኖር ቢመኙ፤
ዓለም ተገርሞ ጉድ እስቲል፤ ሥጋዎን ተነፍስ ወደዱ?

በሐዋርያት መንገድ ሳይሄዱ፤ የሐዋርያት ሥራ ሳይሰሩ፣
ማርቆስ ገብርኤል ገሪማ፤ ጳውሎስ ማቲያስ መባሉ፣
ከርስን ተመሙላት በቀር፤ ለነፍስ ምን ይሆን ጥቅሙ?

አቡን ሆይ!

መንኩሰ ሞተን ዘንግተው፤ ተዓለም እጅጉን ተጣብቀው፣
የፍፃሜው ቀን ሲመጣ፤ መግቢያ ሥፍራዎ ወዴት ነው?

አሥር ሕግጋት አውልቀው፤ የይህ አድግ ደንብ አጥልቀው፣
በጨለማ ውስጥ መጓዝን፤ የሚያቋርጡት መቼ ነው?

የልማት ስብከት አቁመው፤ የጳውሎስን ገድል አንብበው፣
ተብፅኦ ቅዱስ ወ ጴጥሮስ፤ ግብር የሚማሩ መቼ ነው?

ተቤተክሲያኗ ተጣብቀው፤ ቋንጃ ሰባሪን ድል ነስተው፣
ተአብዮት ስብከት ተላቀው፤ ምዕመናንን አዳምጠው፣
እንደ ሰባዎች ሰማእታት! አብ እሚሆኑት መቼ ነው?

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መስከረም ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

1 Comment

  1. የወያኔ ካድሬ ብለህ ያልተሳደብካቸዉ ይመስል አሁን ደግሞ አቡን ብጱዕ አባት ወነፍስ አድን ትላቸዉ ጀመር? ያንተን ስድብ ይረሳሉ ብለህ ትገምታለህ? ኦሮሞን እንዲጨፈለቁልህ ፈልገህ ነዉ አይደል? አይሠራም አርፈህ ተቀመጥ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.