መንጋ ያለመሆን ከብረት – መስከረም አበራ

1 min read

የማደንቀው ፀሃፊ፣ገጣሚ እና አሳቢ(ይችን እኔ የጨመርኩለት ማዕረግ ነች) አገኘሁ አሰግድ(Agegnehu Asegid) ባፈው ሰሞን “ሰጎች” በሚል ርዕስ ጥፍጥ ያለች ጦማር ከትቦ ነበር፡፡ጦማሯን በህዝብ ጥያቄ መልሶ ቢፖስታት ደስ ባለኝ! በዚህ ጦማር መንጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተለመደው አስማት አገላለፁ ቁጭ አድርጎት ነበር፡፡ አጌን አሳቢ የምለው ለዚህ ነው! እኛ በተለምዶ የምንቀባበለውን ሃሳብ ስጋ አልብሶት ፣የሆነውን በሆነው ልክ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ይዞ ከተፍ ይላል-ትንሹ አዳም ረታ!
ሰጎች” የሚለው አባባል ራሱ መንጋ የሰውነትም የበግነትም ማንነት የያዘ ነው ሲል “ሰው” እና “በግ” ከሚለው ቃል የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ፊደል ወስዶ የፈጠረው እንደሆነ አብራርቷል፡፡

አጌ “ሰጎች” ሲል በውብ አገላለጥ የገለፀው የመንጋነት ፀባይ በርካታ ቢሆንም በጣም የማይረሳኝ “ሰጎች ለእረኛቸው ሃሳብ እስከመታረድ ይሄዳሉ እርሱ ግን እርዱም ፍርዱም አይደርሰውም ሩቅ ሆኖ የሚታረድም የሚታሰርም ተተኪ ሰግ መሰብሰብ ነው” ያለው ነገር ነው፡፡”

ለማንኛውም አጌ እንዳለው መንጋ ማለት እረኛው እንደፈለገ የሚያደርገው ሰውም በግም አይነት ተፈጥሮ ያለው ነው፡፡መንጋነት ጭንቅላትን ለማከራየት የመፍቀድ፣ራስን ዝቅ እረኛን ከፍ አድርጎ የማየት እሳቤ ነው፡፡ይህ ሰው ሆኖ መፈጠር የሸለመንንን የታላቅነት ፀጋ ካለመረዳት ራስን የመናቅ ጎስቋላ አስተሳሰብ ከእሳቤ ድህነት እንጅ ከዘር ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ ለዚህ ምስክሩ በሃገራችን ዳርቻ በሁሉም ጥጋጥግ የመንጋነት ዝንባሌ እና ሪኮርድ መመዝገቡ ነው፡፡

ከሰሜን ጫፍ ተነስትን ብንጀምር አረመኔው ጌታቸው አሰፋ እኔ ነኝ ብለው ቲሸርት ለመብሰው ጎዳና ላይ ወጥተው ፎቶ ሲነሱ የነበሩ ሰዎች፣ጥናት ሊያደርጉ የሄዱ ባለሙያዎችን በድንጋይ ናዳ የገደሉ ሌሎች፣ቡራዩ ላይ ሰው ያረዱ ቢጤዎቻቸው፣ሻሰመኔ ላይ ሰው ዘቅዝቀው የሰቀሉ ዘግናኞች፣ወደ ደቡብ ስንወርድ ሃገረሰላም ላይ ሆስፒታል የገቡ የ85 አመት አዛውንት ከሆስፒታል አውጥተው ከነአስታማሚ ልጃቸው በድንጋይ በዱላ ቀጥቅጠው የገደሉ ለወሬ የማይመቹ አረመኔዎች ሁሉ መንጋዎች ናቸው፡፡

በዚህ ሁሉ መንጋነት ውስጥ ዘረኝነት እንዳለ ባይካድም፤መንጋነትን የሚፈጥረው ግን ዘረኝነት ብቻ አይደለም-ለዘረኝነት መንገድ የሚጠርገው አለማወቅ እንጅ፡፡ አለማወቅ ዘረኝነትን ፀንሳ ጨካኝነትን ትወልዳለች፡፡ ይህ ተጠራቅሞ መንጋን መሰብሰብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ብልጥ እረኛ ደግሞ በፉጨቱ ብቻ እስከመታረድ/ማረድ በራሳቸው የጨከኑ፣ለምን እታረዳለሁ/አርዳለሁ? እረኛየስ እውነት የሚያምንበት የትግል ዓላማ ካለው ለምን ከፊት ሆኖ አይመራኝም?ለምን ያን ያህል ሩቅ ቦታ ቆሞ ያሰማራኛል? የማይሉ መንጋ ሰጎችን ይሰበስባል፡፡

የመንጋ እና የታጋይ ልዩነቱ ግልፅ ነው፡፡ታጋይ መሪ ሲኖረው መንጋ እረኛ ይኖረዋል፡፡ታጋይ መሪው ሲስት እስከመገሰፅ እና ወደመስመር ወደማስገባት ድረስ የሚሄድ የራሱ ነፍስ እና ስጋ ያለው ሲሆን መንጋ ግን እረኛው ካአፉ ቃል እስኪወጣ ጠብቆ ወደገደልም ቢሆን ለመሄድ ዝግጁ ነው፡፡ከሰሞኑ እረኛ ነኝ ባይ “ውሻ ተብለሃል ድመት ተብለሃል” ብሎ የመንዳት አባዜው ባቀበለው መጠን የብጥብጥ ድቤ ሲመታ መልስ ያለማግኘቱ ነገር በሃገራችን የመንጋነት እሳቤ እየተመናመነ እንደሄደ ተስፋ ሰጥቶኛል በበኩሌ፡፡

በተጨማሪ የአዲስ አበባ ባለደራ ኮሚቴ ከሰሞኑ መግለጫ እሰጣለሁ ሲል እኔን ጨምሮ ለወትሮው የትግል አላማው ደጋፊ የሆንን ወዳጆቼ “ምን የሚባል መግለጫ ነው?”፣ “ባላደራው እስከ መግለጫ መስጠት የሚያደርስ መሪነት በዚህ ሁኔታውስጥ ሊኖረው ይገባል ወይ?” የሚል ሃሳብ ቆም ብለን ከማሰብ እስከ መቃወም ድረስ ሄደን ነበር፡፡

ባላደራው ልክ ነው የሚሉ ወዳጆቻችንንም ሃሳብ ስናደምጥ ቆይተናል፡፡ አንድ ወዳጄ እንደውም ‘ይሄ ባላደራችን በመንገድ ሲያልፍ ያማረ ሰገነት ድንገት ካየ እንኳን እዚች ላይ ነበር መግለጫ መስጠት’ ሳይል ይቀራል ብለሽ ነው” ሲል በጋራ የምንደግፈውን የባላደራ ምክርቤት ላይ ቀልዶ አስቆኛል፡፡የባላደራው ተከታዮች መንጋ እንዳልሆንን ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ባደረግነው ውይይት ተረድቻለሁ፡፡መንጋ ባለመሆናችን መሪው የባላደራ ኮሚቴም ካላስፈላጊ አካሄድ ተመልሷል፡፡

#መንጋነት_በመመናመኑ_አዲሱ_ዓመት_ብሩህ_ነው

11 Comments

 1. “………ጥናት ሊያደርጉ የሄዱ ባለሙያዎችን በድንጋይ ናዳ የገደሉ ሌሎች……..”

  Yet,…….yet…..yet?????????!!!!!!!

  Lib inibel midre adro qariya/kermo xija hula. Yenesu sihon botawum ayixeqesim. Inesu menga ayideluma. Gojam wusxi new lexinaat yehedutin be nidet bedingayi wogrew yegedeluachew. Yihe new ingidi yehabesha meselxenina lelawun maselxen. Ayi nefxenyaanaa shintoochuu!!!!!!!????????

  • ሌባ ተይዞ ድላ ይጠየቃል በሚል ፈሊጥ ያደገን ህብረተሰብ ለህግ ተገዥ እንዲሆን መሻት ፍየልን የስንዴ ማሳ ውስጥ ለቆ ለምን አዝመራዬ ተበላ ብሎ እንደማልቀስ ነው። መሰረቱ የተናጋ ትውልድ ነው። አንድ ጊዜ በአንድ ሥፍራ አንድ የአዲስ አበባ ልጅ ስሙን ካልተሳሳትኩ ዳንኤል የሚባል በወያኔ የጥላቻ ወጥመድ ይጠለፋል። ልጅ ተጫዋችና በጣም ቀልጣፋ ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ሰው ጥቃት ማድረስ ለወያኔ ቅጥረኞችም ሃበሳ ስለሚሆን በደቦ ወደ 6 ሰዎች ሁነው ወጣ ባለ (ልብ በሉ ይህ የባእድ ሃገር ነው) ውስደው በመደብደብ ጥርሱን ሁሉ አወላልቀው ሞተ ብለው ትተውት ይመለሳሉ። ያ ሰው ተርፎ የሆነውን ሁሉ ሲያጫውተን ትዝ ይለኛል። አሁን በህይወት ካለ መናገር ይችላል። ታሪኩ እውነት ነው። የደቦ ድላ እና ግድያ ፈጻሚው ወያኔ ብቻ አይደለም። ኦሮሞውም አምሮበት ሰውን ዘቅዝቆ እስከ መስቀል ደርሷል። አማራው ለምርምር በመንደሩ ጉራ ያሉትን ምሁራን ያለምንም መረጃ ቀጥቅጦ ገሏል። ችግሩ የምድሪቱ እንጂ በዘር ብቻ የሚመነጭ አይደለም። ነገር የተበላሽው የምንታወቅበትን የዘርና የጎሳ ፓለቲካ የቋንቋ ጥላቻ አቃምሰን የሌሎች መጨቆኛ ብልሃትና የግል ትርፍ ማስገቢያ ካደረግነው ወዲህ ነው። የራሴን መብት ተገፈፍኩ ብሎ እንደ ቁራ ሁሌ እያደነቆረን ተመልሶ እሱ ጨቋኝ እና አሳዳጅ ይሆናል። አይ ፓለቲካ… ባፍንጫዬ ይውጣ!
   የህዝባችን ሃበሳ የበለጠ የምናደማው እኛው ነን። ጎራ ለይተን አመልካች እጣታችን ቀስረን እነርሱና እኛ ስንባባል ዓለም ጥሎን ፈረጠጠ። መታወቂያችን ስደት፤ ረሃብ፤ ጦርነት፤ ግጭት፤ ይባስ ብሎ ለተራድኦ ሃገር ውስጥ የገቡ የውጭ ዜጎችን ሃገር በቀል ሰዎችን አድኖ እንደ እንስሳ በጥይት የሚገል ሰው ያለበት ሃገር ናት። ገዳዪ አስገዳዪ ማን እንደሆን አይታወቅም። ለጊዜው ሆይ ሆይ ይባልና ሌላ ወሬ ተክቶት ይረሳል። የሰው ህይወት የረከሰባት ሃገር የሃበሻይቱ ምድር ብቻ ናት። የደቦ ፓለቲካው የሥራ ቢሆን ኑሮ እስከ ዛሬ ድረስ የት በደረስን ነበር። ግን አእምሮአችን የሚሰላው፤ እጃችን የሚፍታታው ሰው ያዘው ጥለፈው ለማለት ብቻ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ በህክምናው ዘርፍ፤ በትምህርቱ ዘርፍ በወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከላት፤ በንግድ ወዘተ… የሚታየው ግፍ ሰማይ የደረሰ ነው። ሂጅ ባክሽ አትጩሂብኝ እግርሽን ከፍተሽ ሰተሽ ምን ያስጮህሻል ይላል አዋላጅ ተብየው። እሱ በዚያው መንገድ እንዳልወጣ ሁሉ። የስነምግባር ጉድለት፤ በተማሪዎች ላይ መምህራንና ተማሪዎች በሴቶች ላይ የሚፈጽሙት ግፍ ይህ ነው ብሎ ለመስፈር መለኪያ አይገኝለትም። ብቻ ነገሩ ሁሉ አስረሽ ምቺው ነው። ሰክሮ ማሽከርከርና መሽከርከር፤ ሰውን በቀጠሮ ማጉላላት፤ በዘርና በጎሳ አድሎ መፈጸም የእለት እለት የውስልትና ስልቶች ናቸው። ታዲያ እማ መንጋ ያለመሆን ክበረት ከራስ ነው የሚጀምር። ግን እኮ ምድሪቱ የተከለለቸው በመንጋ አስተሳሰብ ነው? ከዛ አስተሳሰብ እና እይታ ለመውጣት ራስን መለወጥና ከዘር የጸዳ እይታ እንዲኖር ግድ ይላል። እስከዛው በሰብብ አስባቡ ስንገዳደል ለመኖር የሌላውን ቤት እሳት ስንለኩስ ጀንበር ወጥታ ወደማደሪያዋ ወይም ተመልሳ እስክትመጣ (ለነገሩ ማደሪያ የላትም)ትገባለች። ተሳዳቢና የውሸት ዜና ቀናባሪ በበዛበት አለም ላይ ጭራሽ እውነት ነው ብሎ አንድን ነገር ማመን አስቸጋሪ ነው። በከተማ መልኩሶ መቀመጥም አይቻል ክርፋቱ መከራ ነው። ገዳሙም ታርሷል። የት ይገባል? አታድርስ ነው።

 2. መስከረም፤ እንዳሻሽ ተራርቢ። የጠፋሁ እንዳይመስልሽ። ትችትሽ፥ ቅን፤ ኣስተማሪ፤ ዝርጠጣ የሌለበት፤ ስድብ ያላዘለ፤ ምስጋናውም ሆነ ቁጣው፥ በውል የታወቀ ይሁን። ችሎታሽን የምታሳዪው በማንቋሸሽ ኣይሁን።

 3. I have a great respect for Meskereme Abera, but I want her to listen to the following link from Eskender why Baladera Mikere Bet needs to give press release, and it was reasonable decision. https://www.youtube.com/watch?v=GXxPLY8vTm0
  The so called Kesse Belay and his followers are obviously backed by Abeye Ahmed OPDO and Mencha Man and other Oromo extremist groups. The place where they gave the press release itself tells you who is backing them, and also one of the guys with a black ‘KEMISE’ said it loudly by banging the table in front of him “Addis Ababa is the capital city of Ormya”
  It is obvious what Kesse Belay and his group are one way of the tool by the OPDO Abeye Ahmede for the mission of disintegrating the country and it is clear what they are doing in the name of religion is a dangerous politics to divide people just like what they did in the name of language, so we all have to wake up and fight it back in what ever form we can and the action of Baladera Mikere Bete is Very Very Very Correct. Actually we need to organize our struggle in a higher level to fight back for our birthright freedom.

  God Blesses Ethiopia and the People of Ethiopia!!!

 4. መስክዬ እጅሽ ይባረክ እንደተለመደው በድንቅ አጻጻፍሽ ሁሌም ልቤን ትገዥዋለሽ:
  እውነት ለማይዋጥላቸው መራራ መሆኑ ሀቅ ነው: በርቺ የኔ ቆንጆ:
  እግዚአብሔር እንዳንቺ ያሉትን ያብዛልን: ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር አሜን!!!

 5. የኢትዮፒየያ ተቆርቃሪዎች ኢትዮጲያን እያጠፋችሓት መሆኑን አለመረዳታችሁ ከእንስሳ ያልተሸለ አስተሳሰብ ላይ መሆናችሁን በግልጽ የሚያሳይ ነው፤፤

 6. ይህች ጢባር ዘረኛ ምንድነው የምትቀባጥረው ???

  ትግራይ እህል እንዳይደርስ የሚከለክለው የገገማ መንጋ ምነው አላነሳች ?????

  ምነው የኔን እምነት ካልተከተላችሁ የኔን ቋንቋ ካላወራችሁ እያሉ ሰልፍ የሚወጣው ስልጣኔ የራቀውን የእንስሳት መንጋ ለምን ዘለለችው?????

  ምነው የጠራሁ አትዮጵያዊ እኔ ነኝ የሚለውን ና የሚኮፈሰውን የትምክህት መንጋንስ አንዴት ዘነጋችው ????

  አዲስ አበባ ኦሮሞ አይገባም ብሎ ድንጋይ የወረወረውን ልኩን ያላወቀውን የሠፋሪ መንጋንስ የት አደረሰችው ??

 7. ይህች ሴት ሁሌ የአማራ ሲሆን ጭፍን ደጋፊ የኦሮሞ ሲሆን ጭፍን ተቃዋሚ ናት ፡፡ የጅምላ ደጋፊና የጅምላ ተቃዋሚ ይህች የሰሜኖች የመንጋ አባል ናት ፡፡

  መንጋጋዋ ይውለቅ !!!!!

 8. የመስከረም አበራ የፖለቲካ ድርሰቶች የሚገርሙ ናቸው ፡፡ የአልጋ ላይ ፍቅር ብትፅፍበት እንዴት ባማረባት፡፡ የሷ ና የብጤዎቿ ዘረኝነት ጫፍ የረገጠ ና ሌላው አማራ ላልሆኑት ያላት ጥላቻ የምታሳዝን ሰው ያደርጋታል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.