በቀለ ገርባ የሾህ አክሊሉን ደፍቶ ራሱ እሳት ጭሮ ባቀጣጠለው ሰደድ እሳት ምኑም ሳይቀር ተቃጠለና ደቀቀ! – በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

1 min read

2012 ዓመተ ምሕረት ተአምር አሳየን! ኅሊና የምትባል የመስከረምን ወፍ የመሰለች ቆንጆ ወጣት፣ በቀለ ገርባ የሚባል የወህኒ ቤት አክሊል አእምሮውን የደፈጠጠበት አምሮተኛና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓቢይ አህመድ በአንድ መድረክ ላይ ተገኛኙ፤ በቀለ ገርባ የሾህ አክሊሉን ደፍቶ ራሱ እሳት ጭሮ ባቀጣጠለው ሰደድ እሳት ምኑም ሳይቀር ተቃጠለና ደቀቀ!

ኅሊና በቀዘቀዙ ቃላት የአእምሮውንና የመንፈስዋን ኃይልና ምጥቀት መገንዘብ ለሚችል ሁሉ አሳየች፤ ዓቢይ አህመድ ሳይተነፍስ በታዛቢነት ተቀምጦ ነበር፤ የተቃጠለውን እያየ አዘነ፤ በኅሊና ቃላት ውበት፣ ምጥቀትና የተስፋ ጽንስ ውስጡ የረካ ይመስላል፤

በቀለ ገርባ ከኅሊና ግጥም የመረጣቸው ቃላት ታች ታቹን የሚያይ ሰው የሚያጋጥሙ ናቸው፤

በቀለ ገርባ በእሾህ አክሊሉ ስር የረበረበው መደላድል ለመሸከሚያ እንጂ ለማበጠሪያ አይረዳም፤ ያለፉት የአምባ ገነን ሥርዓቶች ተመልሰው እንዲመጡ በፍርሃት መልኩ ጠንካራ ፍላጎት ያለው በበቀለ ገርባ ውስጥ ነው፤ የጥንቱን ሥርዓት ለመመለስ የሚለው የበቀለ ገርባ ጩኸት ሀሳበ-ቢስ ነው፤ የጃንሆይን ነው? የደርግን ነው? የወያኔን ነው? ምናልባት ከቃሊቲ ለማንገሥ ታስቦ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አይጥላትም፤ ሰውም አያሳጣትም፤ በቀለ ገርባን ፊት ለፊት ገጥሞ የሚቃወመውና በዝርር ከትግሉ ሜዳ የሚያስወጣው ቱባ ኦሮሞ የሆነው ታየ እሳት ለብሶ፣ እሳት ጎርሶ ብቅ አለበትና የኦሮሞን ሰውነትና ኢትዮጵያዊነት በቁመቱ ልክ አሳየው!!

መስፍን ወልደ ማርያም
መስከረም 2012

8 Comments

 1. Ante yecerecesk shimagile! Zim bileh beqereh idimeh atinorim????? Ahun man yisemahina new yemitiqebaxirew? Inkuwan Oromoo, yantedegafiwochim ketefuh zemen alefe. Zim bileh lahacihin xireg. Hey! Man neh yan cerq aqebilew. Kotetam Oromoo fobist!!!!

 2. You talk/write like a walking deaድ man- zombie! ደግሞ ምሁር ነኝ ሊል ይፈልጋል! ይህ የአሮጊቶች ሁለተኛ ቡና መጠጫ እንጂ የምሁር መነጋገሪያ ጽሁፍ ነው??

  • አባ ካላ እውቀትም እውነትም የለህም። ሃሳቡን መሞገት አልቻልክም። ስድቡ የአንተን ትንሽነት ያሳብቃል።አባትህን ሰድበህ አዋርደህ ደብድበህ የምትኩራራ ከሆነ የአእምሮ ችግር አለብህ።ስድብ በጣም ቀላል ነው በተለይ ለባለጌ።አንተን መሳደቡ በአንተ ደረጃ መዝቀጥ ይሆናል።.ስለዚህ ሌላ ስድብ ከንተው እንስማ ቀጥል። ዛሬ አባትህን የሰደብክ ነገ እናትህን ትሳደባለህ።ይህ የትኛውም ብሔር ባሕል አይደለም።የአንተ ብቻ ነው።ልብ ግዛ።

 3. አንድ ጊዜ አንድ ሰው በሌላው ላይ ተናደደ እና የሚለው ጠፋበት። ትንሽ አስብ አደረገና “አንተ ክርታስ አፍ” እኔን ነው እንደዚህ የምትለኝ ሲል ሌላው ቀብል አርጎ እንዴ ክርታስ አፍ አለው እንዴ ቢለው ዝም በል አንተ ቀፎ አፍ በማለቱ ሶስተኛው ቀበል አርጎ አዎን ከክርታሱ የቀፎው ስድብ ይሻላል። ማር ባይኖርበት የሚሰሩ ንቦች ይኖሩበታል እና በማለት ሁላችንም አሳቀን።
  የሃገራችን ፓለቲካ የስድብ ፓለቲካ ሆኖአል። ሃሳብን መሞገት ቀርቶ ሃሳቢውን ማሳደድ ይመቸናል። አይ ጊዜ። አይ የዘር ሰልፍ ፓለቲካ። እንዲህ ነው ፊደል መቁጠር።
  በየድህረ ገጽ፤ ስፍር ቁጥር በሌላው የዪቱብ ቢዲዎ፤ ሲበላና ሲጠጣ ሰው የሚነታረክበት ይህ ወስላታው የሃበሻ ፓለቲካ የስንቶችን ህይወት እስረኛ አደረገ። የስንቱን ቤት አፈረሰ፤ የስንቱን የነጻነት ጮራ ጨለማ አለበሰው። አሁን ማን ይሙት ፕሮፌሰር መስፍን ይሰደባሉ? ሌላው ቢቀር በአዛውንትነታቸው አይከበሩም? በየምክንያቱ በምዕራቡ ዓለም ተመሽገው የሚገኙ የድሮ ፓለቲካ ትራፊዎችና የዘር ጥመኞች ከሩቅ ሆነው እሳት እየጫሩ የሰው የሳር ጎጆ በሃገር ቤት ሲቃጠል ማየትና መስማት እፎይታቸው ነው። አሁን ማን ይሙት በወለጋ ደምብዶሎ ውስጥ እየተሰራ ያለው ግፍ ሰውን እንቅልፍ ያተኛል? ሰው በራፉ ላይ በሚስቱና በልጆቹ መካከል በጥይት ደብድቦ መግደል የነጻነት ምልክት ነው? የነጻነት ትግል የሚባለው አራሽ ገበሬን ከእርሻው አፈናቅሎ ሥፍራው ተራበ ብሎ ለመንግሥትና ለዓለም ኡኡ ማለት ነው።
  ከላይ ፕሮፌሰሩ አሉት ተብሎ የተጻፈው እውነት ነው። አቶ በቀለ ገርባ የእሾህ አክሊል መጫናቸውን አላወኩም። ቢጭኑ ግን ጥሩ ነበር። የሃገሪቱና የህዝቦች ችግር ይገባቸው ነበር። ከወያኔ ጋር ለምሳ የተቀመጡት በእውነት ለኦሮሞ ህዝብ ተጨንቀው ከሆነ የሚያሳዝን ነው:: ወያኔ በአቶ ስዬ አብርሃ አንደበት ” እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛ ይናገራል” እስኪሉ ድረስ ህዝባችንን ያስጨነቀ የጉድ መንግሥት ነው። ታዲያ የአቶ በቀለ ዙረው ከወያኔ ጋር ቂጥ መግጠም ምን ይባላል። ለእኔ እብደት ነው። በሌላ መልኩ ገጣሚ ህሊና ያላትን እይታ በማካፈሏ ቃላቶቿን እየመነዘሩ አንዳንዱ ለራሱ የፓለቲካ ጡሩር ሲያረገው ሌላው ደግሞ አጥፊ እሳት ለኩሶ እሷንና መሰሎቿን ለማጋየት እየሰራ እንደሆነ እናያለን። ታሪካችን ከትላንት ጀመረ፤ የጋራ ታሪክ የለንም፤ ኦሮሚያ የምትባል ሃገር መገንባት እንሻለን እያሉ በለንደንና በሌላም አካባቢዎች ሲያቅራሩ የነበሩ እብዶች ናቸው አሁን ሃገር ገብተው ሰውን የሚያተራምሱት። እኛ እንዲህ በሃሳብና በግብግብ ስንቧደስ ግብጽ ልክ ኢራን በሳውዲ የነዳጅ ማውጫ ላይ እንዳደረሰችው ጥቃት በአባይ ግድብ ላይ ጥቃት ለማድረስ የማወናበጃና የማስመሰያ ስልቶችን ነድፋ የእኛኑ ሰዎች በማስታጠቅ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። አንድ ቀን በዜና ማሰራጫም ግብጽ የአባይ ግድብን መታች መባሉ አይቀሬ ነው። ለተሳዳቢ ፓለቲከኞች የፓለቲካ ነጭ ለባሾች የምለው ቢሆን ፓለቲካውን ተውት ኳስ መጫወት ልመዱ። ክብደት ይቀንሳል፤ ከያዛቹሁ የማይለቅ የፓለቲካ ስካርም ታርፋላችሁ። እንዴት የሰው ልጅ ዘመኑን ሁሉ ፓለቲካ ሲያላምጥ ይኖራል። ኤጭ አይ ሃገር … ፍሬ ቢስ ሁሉ

 4. አዕምሯቸው በንፍጥ የተሞላ፣ አስተሳሰባቸው ከገማው ሽንት ቤት እንደተደፋ ጥንብ ቆሻሻ የሚከረፋው የእነ በቀለ ገሪባ፣ ህዝቅኤል ገቢሳ፣ ጁሃራውያን፣ ኦነጋውያን/ሸኔዎች፣ የትምህርትን እሴት ገደል የሚከቱ ሃሳበ ድውያን ከመሆን ይሰውረን!!!

  ሰውን ትምህርት ሲያበላሽ እነርሱን አየሁ።

 5. ፕሮፌሰር መስፍን ቃላት ሳያባክኑ ለእዚህ ከንቱ በራሱ የማይተማመን በቀለ ገርባ ! እውነተኛ ኦሮሞዎች ገርባም እይደሉም:: ከመሬት የሚያላትም ፅሁፍ ነው ያቀረቡት :: ቃለ ህይወት ያሰማልኝ:: አንድ ምርጥ የ17 አመት ልጅ ገጣሚን በሀሳብ ሞመገት የማይችል በቀለ ገርባ:: ለእነዚህ ፅንፈኞች ያሳዝኑኛል:: ዛሬ ስልጣን እጃችን ገብቷል በሚል ጮቤ እየረገጡ የሚይዙትን አሳጥቷቸዋል:: ኢትዮጵያዊነት ዛሬም ወደፊትም አሸናፊ ይሆናል:: bunch of losers

 6. ያንተ ኢትዮጵያዊነትን አየን ለመቶ ሃምሳ አመታት፥ የዐማራ የበላይነትን እንጂ እኩልት እኩልነትን የሚቀበበል አለመሆኑንም አየን፥ አሁን የእኩልነት ጭላንጭል ስናይ ደግሞ ለናንተ አማሮች እኩልነት የበታችነት መስሎ ታያች ሁና ቡራ ከረዩ ማለት ጀመራች ሁ። መገንዘብ ያለባች ሁ ግን ካሁን ቦኃላ ተመልሶ ላይመጣ ያከተመለት ስርዓት መሆኑን ነው። ካሁን ቦኃላ እናንተ ለዓለም የሚታበረክቱት ነገር ታሪክን ወደ ኃላ መጎተት ነዉ። ጣሳ ጭንቅላት ነዉ ያላችሁት።

 7. እናንተ የኦሮሞ አክራሪዎች ተረጋጉ::

  ሰውየው ይህንን የፃፈው ሆን ብሎ አማራን ለማሳጣት እንደሆነ ጠፍቷችሁ አይደለም እንዲሁ ለአማራ ያላችሁን ጭፍን ጥላቻ ለማሳየት ፈልጋችሁ እንጂ::
  አቦይ መስፍን ወ/ማርያም አንዴ አማራ የለም ሌላጊዜ በመንግስት ደረጃ መወከል የለበትም እያለ የተቻለውን ያህል አማራን ሲጎዳ የኖረ ፀረ፡አማራ ይሁዳ ነው። ይህ ወንጀለኛ ሽማግሌ ከ60ዎቹ የጃንሆይ ባለስልጣናት ማስገደል ጀምሮ(ክቡር ፀሃፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድን ጨምሮ)አማራ ላይ ብዙ በደል ፈፅሟል።

  እናንተን ለማስደሰትና አማራን ለማናደድ ስለበላይ ዘለቀ አንዴት እንደዋሸ ከመቸው ረሳችሁት? ስለዚህ ተረጋጉ አቦይ መስፍን ወ/ማርያም የናንተ ወዳጅ እንጂ ጠላታችሁ አይደለም።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.