ሙትም ይወቀሳል! – በላይነህ አባተ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ሙት አይወቀስም የሚሉት አባባል፣
የስንቱ ከሀዲ ወንጀል ሽፋን ሆኗል፡፡

እንኳንስ  በኮቢ እንኳን በሰው ልሳን፣
በቅዱስ መጻሕፍት ሙትም ይወቀሳል፡፡

በለስን የበሉት አዳምና ሄዋን፣
በኦሪት በሐዲስ ዛሬም ተወቅሰዋል፡፡

አቤልን የበላው ቃየል አረመኔው፣
ድህረ-ምጣትም ሲወቀስ ኗሪ ነው፡፡

ክርስቶስን ስሞ አሳልፎ ሰጪው፣
የጥንቱ ብአዴን ይሁዳ ከሀዲው፣
እስከ ዓለም ፍጣሜ ሲረገም ኗሪ ነው፡፡

የመሲህ ከሳሹ ከንቱው ፈሪሳዊው፣
በሐሰት ፈራጁ ጲላጦስ ካንጋሮው፣
መጣፍ ለዘላለም በጥኑ እሚወቅሰው፣
ነፍሱን ሲኦል ልኮ የተቀበረ ነው፡፡

ግዛቱን እርስቱን በሆዱ የሸጠው፣
ሕዝቡን በግርፋት በባሩድ ያስቆላው፣
ቅርሱን እያሳዬ ዝርፍ ያስደረገው፣
ጣናን እምቦጭ ዘርቶ ምጥጥ ያስደረገው፣
የመጣፉን ግዮን ለሌሎች የሰጠው፣
ተዋህዶ ቋንጃን ሊሰብር የዶለተው፣
እሬሳው ብአዴን በቁሙ የሞተው፣
ተመቃብር ገብቶም ቁሞም ተወቃሽ ነው፡፡

የብአዴን ዘመድ ጓደኛ ያላችሁ፣
ቆሞም ሙት ነውና እግዚአብሔር ያጥናችሁ፡፡

ሙት አይወቀስም እየተረታችሁ፣
ለከሀዲው ሁሉ ተገን የሆናችሁ፣
በክርስቶስ ፋንታ ለይሁዳ ቆማችሁ፡፡

በመጣፉ ታመንክ በእውነት በእግዚአብሔር፣
ይሁዳን ተሆነ ሙትም ይወቀሳል፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መስከረም ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.