በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተጀመረው ዘመቻና  የ ኤል ቲቪ ነውረኛ ዉንጀላ – ከአበበ ጉልማ

1 min read

በኢትዮጵያ  የሚተላለፈው LTV World የተሰኘው ቴለቪዥን ሰሞኑን የኦሮሞ መብት ተከራካሪ ነኝ ከሚሉት አቶ ግርማ ጉተማ ጋር ባደረገው ቃለመጥይቅ በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተደረገ ስም ማጥፋትና በአደባባይ የተደረገ ዉንጀላ ነበር። LTV World በዮቲዩብ Sep 18, 2019  ባሰራጨው ቃለመጠይቁ (7፡18 አካባቢ ያለውን ያዳምጡ) ወጣቷን ገጣሚ ያላለችዉን ብላለች በማለትና፣ በኢትዮጵያ ቀርቶ በሌላዉም አለም ነዉር የሆነን የብልግና ቃል በአደባባይ በመጠቀም፣ ስሟን ለማጥፋትና፣ የኦሮሞን ህዝብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት ተጠቅሞበታል፡፡ ጋዜጠኛዋም ይሁን LTV ምንም ይቅርታ አልጠየቁም፡፡

ጠያቂዋና LTV የኢትዮጵያን ህዝብና ገጣሚ ህሊና ደሳለኝን በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል።   በአገራችን ለሚደርሰው ጥፋት OMN, LTV እንዲሁም እየቀረቡ ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ መርዘኛና ዘረኛ መልዕክት የሚያስተላልፉ ግለሰቦች፣ እንደ ጃዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ እና ግርማ ጉተማ፣ ጸጋየ አራርሳ፣ ዶ/ር እዝቄል ጋቢሳ ያሉ በህግ ሊጠየቁ ይገባል።  ይህ ዘመቻ ኢትዮጵያን በማበጣበጥና እርስ በርስ በማዋጋት፣ ኢትዮጵያን ለዉጭ ጠላት አሳልፎ ለመስጠት ነው፡፡

መንግስት የዉጭ አገር ፓስፖርት ይዘዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየመሩ ያሉትን ግለሰቦችና ድርጅቶች በትዕግስት መመልከቱ ወይም በአደባባይ በይፋ አለማዉገዙ የሚዘራዉን ከፋፍይ ትርክት የሚደግፍ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡   እነዚህን ግለሰቦችና ድርጅቶች ወደፍርድ እንዲቀርቡ ህዝቡ ሊጠይቅ ይገባል፡፡

3 Comments

 1. ይገርማል። አክቲቪዝም ፓለትከኛ መሆን አይደለም ይላል እንዴ? For practical reason let us see the definition of the word “Activism” – It is advocacy, militancy, involvement, fanatic etc.. ይህ ባህሪ የአንድን የፓለቲከኛ ገጸ ባህሪ አያሳይም ማለት ድመትን በውሃ ለመንከር እንደ መሞከር ነው። ግን ትላንት የገጠመኝ ነገር ከዚህ ውይይት ጋር አብሮ ይሄዳልና ልጥቀሰው። ስድስት ሆነን ምሳ እየበላን አንደኛው ስለ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሰላማዊ ሰልፍ አንስቶ ይለፈልፋል። ሌላኛው አይ ክርስቲያን የሆነ ፓለቲካ መግባት የለበትም ይላል። ይህ ሰው እብድ ነው? መጽሃፍ ቅዱሱ ከዳር እስከ ጫፍ ፓለቲካ አይደለ እንዴ? አላስችል አለኝ። አርፈን የቀረበውን እንብላ አለዚያ እኔ መውጣቴ ነው ስል ሁሉም ጭጭ አለ እና ተወርቶ ወደማያልቀው የእግር ኳስ ጉዳይ ገቡ። የሚያሳዝነው ኳስ በእግሩ ነክቶ የማያውቀው ሁሉ ያለቅጥ ቲፎዞ ሆኖ ሲወራጭ ማየት አይ ጉድ ያሰኛል። ወደ ቃለ መጠይቁ ሃሳብ ልመለስ፡
  ቄሮና የመንጋ አስተሳሰብ – እንኳን ቄሮ ቀርቶ የዓለምን ካርታ ያስቀየሩ፤ ሃገርን የወረሩና የከፈሉ ሃገሮች ሳይቀሩ የመንጋ አስተሳሰብ አራማጆች ነበሩ። ሩሲያ በኮሚኒዝም ስር፤ ጃፓን በንጉሳቸው ሥር፤ ጀርመን በናዚ መሪነት። ፓለቲካና የጅምላ እርምጃ ተለያየተው አያውቁም። የቄሮን ዋጋ መክፈል ዓሊ የሚል ማንም የለም። ችግሩ ሁሉም ለእኛ ብቻ በማለት በጅምላ ፍርድ በአዲስ አበባ የኮንዶሚኒዪም ዕጣ የደረሳቸውን እንዳይገቡ መከልከል፤ ሰውን ዘቅዝቆ መስቀል ባጠቃላይ የብቀላ ፓለቲካ መያዙ ነው። በመሰረቱ ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ “አንዲት ሴት” ገጣሚ ማለቷ አድሎአዊነቷን ያሳያል። ስም አላት። ግን የዚህ የዘር ፓለቲካ ሁሉን ሰው ጠፍሮ ስለያዘው በጋዜጠኛ ስራዋ እንኳን ገለልተኛ መሆን አልቻለችም። እውነታው የኦሮሞ ህዝብ ሃገሩን የሚወድ፤ ተርቦ የማያውቅ፤ ያለውን የሚያካፍል ለመሆኑ አበረነው የኖርን እናውቃለን። ተጻፈ የሚባለው የታሪክ መጽሃፍም ሆነ ሌላ ምነው ሁሉን አጥለቅልቀው ኦሮሞዎቹ ግብጽ ደርሰው በሆነ ዛሬ ያለው ችግራችን ሁሉም ባይሆን ግማሹ በተቃለለ ነበር። ግጥሙ የኦሮሞን ህዝብ አይሳደብም። አያሳንስም። የአጼዎቹ ዘመንም ናፋቂ አይደለም። ግን ቀን ያነሳው ፓለቲካ በዘሩ ተገን ለማድረግ በሰው ላይ አቧራና ጥላሸት መቀባት ስላለበት ግጥሙን እንደ አንድ ስነጽሁፍ ወስዶ ከማየት ይልቅ ቀንጥሰው እየቀጠሉ ለኦሮሞ ህዝብ የተቆረቆሩ በመምሰል በቴሌቪዝን ላይ መወስለቱ በሃገሪቱ ላይ መከራ ያመጣል እንጂ ለማንም አይጠቅምም። ወደ 60 ዓመት የሚጠጋው አንድ የግጥም መዝጊያ እንዲህ ይላል።
  እስቲ አዋቂዎቹ እናንተ ንገሩኝ
  እኔን ያስጨነቀው ኢትዮጵያዊው ማን ነው? (ምንጭ ኢብሳ ጉተማ ፡ ኢትዮጵያዊው ማን ነው?)
  አቶ ግርማም ነገሮችን ረጋ በማለት ቢረዳ የተሻለ ነው እላለሁ። ፓለቲካ እንደ አውሎ ነፋስ ነው። የማይሸከመው የለም። የሚያኖርበትን ግን መገመት ይከብዳል። የትላንት አለቆቻችንን አወዳደቅ ትምህርት ይሁነን። ሰላም ለሃገራችን እና ለህዝቧ ይሁን!

 2. ለምንድ ነው ሰዉ ግራ የሚጋባው?እባብ ጭንቅላቱ ካልተፈረከሰ ፈፅሞ አይሞትም ብለን ስንቴ ተናግረን ነበር???…እንዳይገርማችሁ አንገቱ ተቆርጦ የራሱን ጅራት ሳይቀር የሚበላ አንዴ ነክሶ በመርዙ የሚገድል ነው። የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪና የተንኮሉን ዘር የተከለው ወቸገል ዜናዊ እንደሆነ ብዙ መረጃዎች ለአደባባይ ቀርበዋል፤ እጅግ የሚያሳዝነው በተገደሉት የትግል ጓዶቻችን ደም አምሥት ቢሊዮን ብር ዘርፏል፣ቢባልም ጉዳዩ ለሕግ ይቀርባል ተብሎ የውሃ ሽታ ሆኗል።
  አሁን ደግሞ ለሃያ ሰባት ዓመታት ለፋሺሽት ወያኔ በአሽከርነት ተላላኪ ሆነው ሲያገለግሉ በጋዜጠኛነትና በቅጥር ባንዳነት ከሚያገለግሉት መካከል LTV የተባለ የቴሌቭዢን ድርጅት በሽምቅ አፃፋዊ-ቅስቀሳዎችን እያደረጉ መሆኑን በመረጃነት ይህን ተመልክታችሁ ለሌላውም እንድታካፍሉ እየጠየቅኩ ለመዝናኛ ይህችን ግጥም ተቃመሷት፣መረር ያለች ብትሆንም።
  የአርዴሞች ሰላዮች።  
  ጉጅሌን “አርዴሞ”ስንላቸው እኛ፤
  ምክንያቶች አሉን ይሄው ነው አንደኛ።
  “ሺሻ”ብሎ ነገር
  ኢትዮጵያ አስመጥተው፤
  ወጣቱን አስፈጁት
  ትምቧሆ አግተው።
  ልጃገረዶችም “አሪማጥ” እንዲሆኑ 
  ጫቱን አመንዥገው፣
  በሺሻ ሲቦኑ፤
  በጫት አቃቃማቸው
  ቀሩ እንደዘመኑ።
  ወጣቱ ግን ነቄ
  ሆነና አስቀድሞ፤
  አጋታቸው ዕፁን
  ትምባሆ ለቃቅሞ።
  ልጆቻቸው ይልመዱ
  አሉና ሰጧቸው፤
  እኛን እንዳነደዱን
  እነሱን ይፍጃቸው።
  ሁሉንም አይደለም 
  አውቀው የሚያደርጉትን፤ 
  በፍፁም አንምርም
  ዛሬ ያስገደሉትን።
  በሚመረው ቅጣት
  ለጋንጃ አባት ዳርገን፤
  የባሰ እንቀጣለን
  እንዲገዛ አድርገን።
  የማን ልጅ ፈራርሶ፣
  የማንስ ይቀራል፤
  ደም-ዕምባ እስክታለቅስ፣ 
  ሞት ውስጥህ ይኖራል።
  እስኪ የድሃን ልጅ
  ቅደሙ ገዳዮች፤
  እናውቃችኋለን የአርዴሞ ሰላዮች።
  ከደደቢት በረሐ 
  ይዞት-የመጣው ሠይጣን፤
  አስመስክሮለታል
  ነፃ እንደሚያወጣን።
  የምናየው ሁሉ
  የሰዶም ተግባራት፤
  የ”ሌጌዎን” ናቸው
  እዩት በማጣራት።
  ለሰሚ የሚከብዱ የሚሰቀጥጡ፤
  ሰው ገድለው በቁሙ ናቸው የሚመጡ።
  እነዚህን ሁሉ
  አርክሶ ያመጣቸው፤
  የፋሺሽቱ-ወያኔ
  እርሱ ነው መሪያቸው።
  እናም አታጓቱት
  በባለሥልጣን ሰበብ፤
  ወቸገል-ዜናዊ በሕዝብ ፈት ተረግሞ
  አፅሙ ችሉት ይቅረብ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.