ይቅርታ ማለትን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሪ ብልህ ነው (በታምሩገዳ)

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር በእጃችን ነው (ባለጊዜዎች ነን)በማለት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የምናደርጋቸው፣የምንናገራቸው፣የምንጽፋቸው …ወዘተ ነገሮች ይዋል ይደር እንጂ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉናል ፣ሲያስከፍፈሉንም ይስተዋላሉ ።

ከላይ ለተገለጸው አባባል ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑን ሰሞኑን ለሁለተኛ ዙር የምረጡኝ ዘመቻ የጀመሩት የካናዳ ጠ/ሚ/ር ጀስቲን ቱሩዲዬ ዋንኛ ተጠቃሽ ሲሆኑ ጠ/ሚ/ሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እኤአ 2001 ቫንኩቨር ውስጥ ዌስት ፖይንት ግሬይ አካዳሚ በተባለ ታዋቂ የግል ት/ቤት መምህር በነበሩበት ወቅት በአመታዊ የተማሪዎች የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ በቡድን ከተነሱት የማስታወሻ ምስል ላይ ጭንቅላታቸው ላይ ተርባን በመጠምጠም ፣በገመድም በማሰር፣ ፊታቸውን እና እጆቻቸውን ደግሞ በጥቁር ቀለም ተለቅልቀው የተነሱት ምስልን ያነሷቸው ወገኖች ይሁኑ እርሳቸው ብዙም ትዝ አይላቸውም።

ይሁን እንጂ እንደ እኛ አገር አንዱ ወገንን ለመካብ ፣አንዱን ወገን ለማንቋሸሽ ታልሞ (ፎቶ ሾፕ )ተደርጎ ሳይሆን አመታዊ የተማሪዎች የእራት ግብዣ ማስታወሻ ፎቶ ግራፉ ከእጁ የገባው ታዋቂው ታይምስ መጽሔት በፎቶው ላይ ምንም ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስ ቀደም ባሉት ጊዜያት ነጮች ጥቁር አፍሪካ አሜሪካኖችን ለማንቋሸሽ እና ድብእናቸውን ለመንካት ሲሉ ፊታቸውን ጥቁር ቀለም በመቀባት፣ሌላ ገጽታ(ምስል)በማድረግ የሚነሱት ምስል በጽኑ የተወገዘ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ታይምስ ሰሞኑን ለአንባቢዎቹ አቅርቦታል።

በወቅቱ ፖለቲካ ውስጥ በቅጡ ያልገቡት፣የሀያ ዘጠኝ አመት ወጣት የነበሩት ፣ ከለፈው አራት አመት ጀምሮ ካናዳን እየመሩ የሚገኙት ፣ የሊበራል (ለዘብተኛ)ፖርቲንም የሚመሩት ጠ/ሚ/ር ጀስቲን በትላንትናው እሮብ እለት ለምርጫ በተንቀሳቀሱበት አውሮፕላን ውስጥ አብረዋቸው ከተጓዙት ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ “በምስሉ ላይ ጥቁር ቀለም ተለቅልቆ የሚታየው ምስል በትክክል የእኔ ምስል ነው። ያደረኩት ነገር ተገቢ ያለመሆኑን ቀደም ሲል ባውቀው ኖሮ በታደልኩ ነበር ፣ ፈርዶብኝ የተለያዩ አልባሳትን መልበስ እወዳለሁ እንጂ እኔ ዘረኛ አይደለሁም፣የፈጸምኩት ድርጊት ስህተት መሆኑን አምኛለሁ ፣ለጥፋቴም ሙሉ ሀላፊነትን እወስዳለሁ ፣ ሀላፊነትንም በተመለከተ ለልጆቼ አስተምራለሁ፣ላጠፋሁት ጥፋት የካናዳ ሕዝብ ከልብ ይቅር ይበለኝ ፣” በማለት መጸጸታቸውን ገልጸዋል።

የሟቹ የቀድሞው የካናዳ ጠ/ሚ/ር ፔሪይ ቱሩዲዬ ልጅ የሆኑት የአርባ ዘጠኝ አመቱ ጠ/ሚ/ር ጀስቲይን ቱሩዶ የዛሬ አስራ ስምንት አመት የተነሱት ተገቢ ያልሆነ ፎቶግራፍ መሰራጨቱን ተከትሎ “የይቅርታ ይደረግልኝ ” ማለታቸውን አንዳንድ ተቃዋሚዎቻቸው ” ያልሆን ለመሆን የሞከሩት ጠ/ሚ/ሩ የፈጸሙት ስራ የዘቀጠ እና ለጥቁሮች ስድብ ነው ፣ ቀጣዩ የፖለቲካ ጉዟቸውም አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃል” በማለት የሰላ ትችት ሰንዝረውባቸዋል።

በሌላ ጎኑ ጠ/ሚ/ር ጀስቲን ከአመታት በፊት የሰሩትን ስህተት በአደባባይ ወጥተው ማመናቸው እና ይቅርታ መጠየቃቸው የአንድ ብልህ መሪ ምሳሌ እንደሆነ እና በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ የጎላ አሉታዊ ተጽእኖ እንደማይፈጥርባቸው የገመቱ የፖለቲካ ተጠባቢያኖች አልታጡም።
የጎረቤት አሜሪካ፣ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቅድሚያ ለአሜሪካ(አሜሪካ ፈርስት)በሚለው የፖለቲካ ቀመራቸው በስደተኞች ላይ አይን ያወጣ ጥላቻቸውን በተግባር ሲያሳዩ፣ወደአሜሪካ የሚገቡ ሽፕቀጦች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ለመጣል ሲሯሯጡ ጠ/ሚ/ር ጀስቲን በበኩላቸው ከአሜሪካ በበለጠ የስደተኛን ፍልሰትን መቀበላቸው እና የነጻ ንግድ ፖሊሲን በማቀንቀናቸው በሊብራል ዲሞክራሲ አመለካከት ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አስገኝቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.