የሕዝብ ሀብትን ያለከልካይ መርጨት ካለእውቀት ማጨብጨብም ወንጀል ነው

1 min read

በጀት ቁም ነገር ላይ የሚውለው መቼ ነው ? ባሳለፍነው አመት ብቻ በርካታ ገንዘቦች የባከኑባቸው ጭፈራዎችና ድግሶች በተለያየ ሰበብ ወጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሰዎች የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ የራሳቸውን ገጽታ ለመገንባት የሃገሪቱን ገንዘብ ረጭተዋል።

ሕዝቡም ካለእውቀት አጎንብሶ ያጨበጭባል፤ ቀና ብሎ መጠየቅን አልተካነበትም። የተለያዩ ባለስልጣናት ከፍተኛ ወጪ የወጡባቸው ድግሶችንና ስብሰባዊ ፋይዳቢስ ጭፈራዎችን በሃገሪቷ በጀት በትነዋል። የገጽታ ግንባታና የምርጫ ድምጽ መግዣ ከመንግስት ካዝና በድግስ፣ በሽልማትና በጭፈራ ሰበብ የሚወጡ ገንዘቦች ሃገሪቱን አደጋ ላይ እየጣሏት ነው።

በተለይ አዲስ አበባ ላይ ለነዋሪው ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ያለው አንድም የረባ ስራ ባልተሰራበትና ስትራቴጂ ባልተነደፈበት ቀደም ብለው የተሰሩን በማንሻፈፍ ጊዜያዊ ስራዎችን ለእይታ ሲሰሩ የነበሩ ባለስልጣናት ሊፈተሹ ይገባል። የሕዝብ ንብረትን እንደ ግል በቆጠረ ደረጃ ብዙ ወጪ የፈሰሰባቸው የእራት እና የጭፈራ ድግሶች በከተማ አስተዳደሩ ወጪ መደረጋቸው ሳያንስ ዘንድሮ በመጪው እሁድ በሚደረግ ፓርቲ የሕዝብ ሀብትን ያለከልካይ መርጨት አንድ ተብሎ ይጀምራል።በሰብብ አስባቡ የሕዝብ ሐብት መባከኑ ያጠያይቃል።

የግብር ከፋዩ ሕብረተሰብ ገንዘብ ለባለስልጣናት የምርጫ ድምጽ መግዣ እየዋለ መሆኑንና ይህም እስከመቼ እንደሚቀጥል የታወቀ ነገር የለም። በማሕበራዊ ድረገጽ አጨብጫቢዎችንና አስጨብጫቢዎችን ከመቅጠር አንስቶ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የሕዝብ ንብረቶች ሕጋዊ ላልሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች እስከማስተላልፍ የሚደረግ ሕገወጥ ድርጊት ከተጠያቂነት አያድንም። #MinilikSalsawi

Office of the Prime Minister-Ethiopia
Mayor Office of Addis Ababa

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.