የትውልደ ኢትዮጵያዊው ሚሊዬነር የአሟሟት እንቆቅልሽ! (በታምሩ ገዳ)

1 min read

በቅርቡ የበርካታ ሚሊዬን ዶላሮች አሸናፊ ለመሆን የበቁት እና በአገራችፕው ኢትዮጵያ ውስጥ የችግረኞችን ህይወት ለመቀየር ውጥን የነበራቸው ትውልደ ኢትዬጵያዊው ሰሞኑን በአገራቸው ኢትዬጵያ ውስጥ ሞተው የመገኘት ዜና ቤተሰቦቻቸውን በእጅጉ አስደንግጧል።

በካናዳው ፣ቶሮንቶ ግዛት ውስጥ በአንድ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ የነበሩት የአርባ እንድ አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ሚካኤል ገብሩ የዛሬ ሁለት አመት(እኤአ ሰኔ 2017) የቆረጡት ሎተሪ ግፋ ቢል 14 የካናዳ ዶላር አሸናፊ ያደርገኛል ብለው ከመጠበቅ ውጪ ሌላ ሀሳብ አልነበራቸውም ነበር።

ይሁን እና ያቺ በድንገት የተቆረጠች ሎተሪ አቶ ሚካኤልን የ10 .7ሚሊዬን የካናዳ ዶላር ( ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ሚሊዬን ብር በላይ)አሸናፊ እንዲሆኑ በማድረግ ህይወታቸውን በአንድ ቀን ጀንበር ሙሉ በሙሉ እንደቀየረው ብዙዎች በአግራሞት ይናገሩላቸዋል።

በወቅቱ ከሚሰሩበት ስራ ተቀንሰው (ተባርረው) በነበረበት ወቅት የሚሊዬነርነት ማድረጊያ ሎተሪ እድለኛ ለመሆን የበቁት አቶ ሚካኤል በወቅቱ ከካናዳው ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (CBC) ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ”ሎተሪ ባገኝ ፣ሎተሪ ቢደርሰኝ ፣ማረፊያ ቤት ገዝቼ፣ወደ አገሬም ሄጄ ደሀዎችን እረዳበታለሁ”ሲሉ ምኞታቸውን ተናግረው ነበር።ምኞታቸውም ሳይውል ሳያድር ተሳካ ።

የአቶ ሚካኤል የቅርብ ዘመድ የሆኑት ሶስና አስፋው በትላንትናው አርብ እለት ለንባብ በበቃው ለሲቢሲ(CBC) ድህረ ገጽ በላኩት መረጃ ሎተሪውን ካሸነፉ ማግስት ጀምሮ ከቶሮንቶ ካናዳ ወደ ኢትዬጵያ እየተመላለሱ ሁኔታዎችን በማጥናት ላይ የነበሩት አቶ ሚካኤል ከሁለት ሳምንት በፊት ለተመሳሳይ ተልእኮ ወደ ትውልድ ቀያቸው በመምጣት አሳዛኙ የኑሮ ውጣ ውረድ ጋር የሚጋፈጠው ማህበረስብን ለመርዳት እና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለመድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ባለፈው ቅዳሜ መንስኤው በውል ባልታወቀ ሁኔታ ሞተው መገኘታቸውን ሶስና በምሬት ተናግረዋል።

ህይወታቸው በአንድ ጀምበር ከተራ ጥሮ አዳሪነት ወደ ሚሊየርነት መለወጡ በካናዳ ፣ቶሮንቶ ከተማ ውስጥ በምትገኘው በግምት ስድስት መቶ ሺህ ነዋሪዎች በሚኖሩባት ስካርቦሮው ክፍለ ከተማ አልፎ ኢትዬጵያ ውስጥ በትውልድ አካባቢያቸው ሳይቀር ዝናቸው የናኘው አቶ ሚካኤል ገብሩ አሟሟት ድንገተኛ ሳይሆን “ተገድለው ነው” የሚል መረጃ እንደደረሳቸው የሚናገሩት ቤተሰቦቻቸው ከኢትዬጵያ ፖሊስ በኩል እስከአሁን ድረስ በቂ መረጃ ባለማግኘታቸው የካናዳ መንግስት (አ/አ የሚገኘው ኢምባሲ)በጉዳዩ ዙሪያ ጣልቃ እንዲገባ እና እንዲያጣራላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በዜጋው መሞት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የገለጸው የካናዳ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ሁኔታው የግለሰብ ጉዳይ በመሆኑ ህጉ በሚደነግገው መሰረት ከቤተዘመድ ጋር ከመወያየት በቀር ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለዜና ሰዋች ከመስጠት ተቆጥቧል። ከስራ ገበታቸው በተቀነሱ ማግስት ሚሊየነር ለመሆን የበቁት አቶ ሚካኤል በትውልደ ኢትዬጵያዊ ከመሆናቸው ውጪ የትውልድ ስፍራቸው ሆነ አሳዛኙ ድርጊት የተፈጸመበት አካባቢ በዝርዝር በዘገባው ላይ አልተካተተም። ይሁን እንጂ ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ አንዳንድ ያልተረጋገጡ ምንጮች ግን ግድያው ከዝርፊያ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ስፍራውም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ውስጥ የተፈጸመ መሆኑን ይናገራሉ።

(በታምሩ ገዳ)

1 Comment

  1. I have not talked to a single family member or friends of mine in Ethiopia for years because I am scared same thing that happened to Michael Gebru would happen to me, the last thing the family or friends know about me is that I am unemployed food stamps welfare recipient residing in USA homeless .

    In Ethiopian’s culture people like to gossip and throw a web of scandal being a master of conspiracy when it comes to fooling people , which makes Ethiopians that suddenly rise to wealth vulnerable to robbery or murder, so I decided to cut off contact to save my life. In a way the ever rising cost of living and the habit of hiding large amount of money burried in the backyard in Ethiopia could be to blame. IN SITUATIONS LIKE THESE I KNOW NOT TO TRUST NO PERSON!!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.