እያረምን ወይስ እያበድን እንሂድ? (በዳንኤል ክብረት)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ገበሬው ለሙግት ወደ ሸንጎ ሄዶ ሲመጣ የገዛ ወዳጆቹ የዘራውን እህል ሳያርሙ፣ ሳይኮተኩቱ ጠበቁት፡፡ ማሳውን እያየ ያብዳል፡፡ እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? ይህን ያደረጉት እነ እንቶኔ ናቸው? ይህን ያደረጉት እኔን ሊጎዱ ነው? ድሮም እነርሱ አይወዱኝም ነበር፤ በቃ የሰው ነገር መጨረሻው እንደዚህ ሆነ ማለት ነው? በቃ የእርሻዬ ነገር አበቃለት ማለት ነው? እያለ ፀጉሩን እየነጨ ያብዳል፡፡
አንድ ሽማግሌ ከሩቅ አይተዉት መጡ፡፡ እየዛበረ የሚናገረውን ሰሙ፡፡ ከዚያም ‹እባክህ ረጋ በል› አሉት፡፡ ‹ምን ረጋ እላለሁ፤ እንዲህ ሲሆን እያዩት፤ ከዚህ በኋላ ምን ተስፋ አለኝ› እያለ ሲጮኽ ሽማግሌው ሰሙትና ‹ወዳጄ ይህ ሁሉ ቢሆንም፣ እያረምን እንጂ እያበድን መሄድ አለብን እንዴ› አሉት አሉ፡፡
ኢትዮጵያም እንዲህ ነው እየሆነች ያለችው፡፡ አንዱ ስንዴ፣ ሌላው እንክርዳድ ይዘራል፤ አንዱ ያቀናውን ሌላው ሊያጣምመው ይተጋል፡፡ በዚህ ሲደፈን በዚያ ይቦተረፋል፤ ራስ ሲነቃ እግ ይጎተታል፤ ብዙዎቻችን እንደዚያ ገበሬ የምናየውና የምንሰማው ለዕብደት እየዳረገን ነው፡፡ ማበድ ግን ሀገር አያቀናም፡፡ መቆጨት እንጂ መናደድ መፍትሔ አያመጣም፡፡ አበቃ፣ አለቀ፣ ደቀቀ፣ ሞተ ተቀበረ፣ ሄደ፣ አከተመ፤ ነጠፈ፣ ተሟጠጠ እያሉ ማልቀስ ነገሩን አይቀይረውም፡፡
አርበኞቻችን ሀገራችንን ከጣልያን ቀንበር ሊያላቅቁ ላይ ታች ሲሉ አያሌ ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ገጥመዋቸዋል፡፡ የንጉሡ መሄድ፣ የአንዳንድ ታዋቂ ሰዎች ከጣልያን ጋር ማበር፤ ሌላው ቀርቶ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ ከጣልያን ጎን መቆማቸው፤ ለገንዘብና ለሹመት ሲል መረጃ እየሰጠ የሚሾልከው ባንዳ፤ በእነርሱ ላይ የሚወረወረው ፕሮፓጋንዳ፤ ስንቅና ትጥቅ ሲያልቅበት ተስፋ የሚቆርጠው ጭፍራ፤ ጣልያን እያሸነፈ ነው እያለ የሚቦተርፈው ወሬ በጉንጩ፤ የአንዳንድ ጀግና ዐርበኞች በጊዜ መሠዋት መክፈል፤ መንገዱን ረዥም ትግሉን መራራ አድርጎባቸው ነበር፡፡
የሀገር ነጻነት እንኳንስ ለማየት ለመስማት የሚቀርብ አይመስልም ነበር፡፡ ዓለም በሙሉ ከጣልያን ጋር ያበረ ነበር የሚመስለው፡፡ ንጉሡ በዓለም ማኅበር ያቀረቡትን ተማጽኖ ሊሰማ የወደደ አልነበረም፡፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ ደግሞ ነገሩ ሁሉ የተቆረጠና ያለቀ ይመስል ነበር፡፡
ያንን የመከራ ዘመን የተሻገርነው ማረም እንጂ ማበድ እንደማያዋጣ በገባቸው ዐርበኞች ትከሻ ነው፡፡ መቼምና ምንም ቢሆን የኢትዮጵያ ነጻነት የማይቀር እውነት መሆኑ ገብቷቸው፣ ከሚያጋጥማቸው ፈተና ይልቅ የሚገኙትን ድል በሚያስቡ ዐርበኞች ነው፡፡ አንድ ጥግ ይዞ ከመቆዘምና ፀጉር ከመንጨት ይልቅ ወደ መፍትሔው የሚደርስ አንዳች ነገር ማድረግ የተሻለ መሆኑን በተረዱ ዐርበኞች ክንድ ነው የተሻገርነው፡፡
የዐርበኞች ትግል ከተናጠል ወደ ኅብረት፣ ከኅብረት ወደ ትብብር፣ ከትብብር ወደ ግንባር እያደገ መጣ፡፡ በመጀመሪያው ዓመት የነበሩትን ነገሮች እያረሙ፤ የተሻለም መንገድ እየተለሙ ተጓዙ፡፡ ሌሎች በመቶ ሃምሳ ዓመት ያልገፉትን ቅኝ ገዥ እነርሱ በአምስት ዓመት አሰናበቱት፡፡ እገሌ እንዲህ አለ፤ እዚህ ቦታ እንዲህ ተዘፈነ፤ እገሌ ለጣልያን ገባ፤ እገሌም ከዐርበኞች ከዳ፤ እገሌ ደግሞ ወደ ዐርበኞች መጣ፤ እነ እገሌ ዐርበኞችን ደምስሰን ሀገሪቱን እንቆጣጠራለን አሉ፤ እነ እገሌም በመሣሪያ ኃይል ተደራጅተው ሊዘምቱብን ነው፤ የሚለውን ሐሞት አፍሳሽ ወሬ መስማት ተው፡፡
የማይሠሩትን ትተው ከሚሠሩት ጋር ብቻ ለመተባባር፤ ስለ ጠላት ከማሰብ ስለ ወገን ብርታትና ጥንካሬ ለማሰብ፤ ከማበድ እያረሙ ለመሄድ በመቁረጣቸው ከ1930 ዓ.ም. በኋላ የዐርበኞች ትግል እየተጠናከረና መልክ እየያዘ መጣ፡፡ የጸሎት ዐርበኞችና የጦር ዐርበኞች ተባብረው ባደረጉትም ትግል ኢትዮጵያ ቀንበሯን ሰበረች፡፡
ዛሬም የሚያስፈልገን እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ በትንሽ በትልቁ በማለቃቀስና በማበድ ጉልበታችንን ሁሉ ለልቅሶና ለዕብደት ከምናውለው፤ ስሕተቱን እያረምን፤ ሰውን እያተረፍን መጓዝ ነው ያለብን፡፡ መሬቱ ላይ የበቀለ አረም ካለ አረሙን እናርማለን፡፡ መሬቱን ግን እንፈልገዋለን፡፡ ዛሬ አረም አበቀለ ማለት ለአረም የተፈጠረ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ እነ እገሌ እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ ሆኑ፣ እንዲህ አሉ እያልን የተራረፈ ወሬ እየለቃቀምን የተጣለልን የአጀንዳ ፍርፋሪ እያነሣን ልባችንን አናድክመው፡፡ በራሳችን ዕቅድ ወደምንፈልገው ዓላማ እንሂድ፡፡ ኢትዮጵያን መድረስ ወዳለባት ሠገነት ለማድረስ የማንም ቡራኬና ፈቃድ አያስፈልገንም፡፡ ‹እህ›ም ተባለ ‹አሃ› መንገዳችንን አይለውጠውም፡፡ እያረምን እንጂ እያበድን አንሄድም፡፡

13 Responses to እያረምን ወይስ እያበድን እንሂድ? (በዳንኤል ክብረት)

 1. It is good. Yabeduten enante tawekalachehu. Dear kadri, please dont use our religion’s spritual tittle.DEACON.

  Hailu
  October 9, 2019 at 3:54 pm
  Reply

 2. ዲያቆን ክብረት
  በውነት ታውረን የለ፤ በዕውነት
  ከዕውር ፤ከቄስ ጋር ኣታሞ ይዘን እንጫወት
  ኣይደል ክብረት?
  ኣሁንስ ቤተክሲያንም ገባችበት

  Mulugeta Andargie
  October 9, 2019 at 7:36 pm
  Reply

 3. ለማይኖሩበት ዘመን ለእውነትና ላመኑበት ታግለው ያለፉ ዛሬ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ቀና ብለው ማየት ቢችሉ ከመኖር መቃብር የሚመርጡ ይመስለኛል። ጊዜው መሸ እንጂ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ በሱማሊያ ፓስፓርት ተጉዘው አንድ ቦታ ላይ ተቀምጠዋል። አስተናጋጅ ተቀብሎ ወደ ሃገሪቱ የስለላ ቢሮ ይወስዳቸዋል። በዚያ የሆነውን አናውቅም። ግን ለኢትዮጵያም ሆነ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅም ሥራ እንዳልተሰራ ግን ጊዜ ቆይቶ አሳይቶናል። አሁን ደግሞ የወያኔ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ከግብጽ የስለላ መረብ ጋር ላደረገውና ወደፊትም ለሚያደርገው ግንኙነት በሌላ ስም የተዘጋጀ የኢትዮጵያ ፓስትፓርት፤ በሌላ ስም የተዘጋጀ የሌላ ሃገር ፓስፓርት ይዞ እንደሚንቀሳቀስ በቅርብ የማውቀው ኢንዲያን ኦሽን የተሰኘ የወሬ መረጃ ክፍል ሰራተኛ የነበረ ሰው አጫውቶኛል። የሚገርመው ወያኔ ሃገርን ለማፍረስና ድንበርን ቆርሶ ለመስጠት አይኑን የማያሽ ለመሆኑ በፊትም የታወቀ ዛሬም በተግባር የታየ ነው። ራሳቸው እንገንባ ብለው የጀመሩትን የአባይ የሃይል ማመንጫ ግድብ አሁን ሊያፈርሱት ከግብጽ ጋር መዋዋላቸውን የዶ/ር አብይ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል። እንዲያውም ስለዚህ ጉዳይ የውጭ መንግሥታት በቀጥታ የስለላ ድርጅታቸው የደረሰበትን አካፍለዋል። ዝምታው ለምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም። ሌላው ቢቀረ በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ዜና ለህዝባችን ሊነገረው ይገባ ነበር። እያረምን ወይስ እያበድን ነው ለሚለው የላይኛው የሃሳብ ክፍል መልሱ እያበድን ነው። ባለፈው ዘመን ከባህር ማዶ በተሻገረ ርዕዪተ – ዓለም ተሰልፈን እርስ በእርሳችን ስንተራረድ እንዳልነበር ሁሉ ያ የመደብ ፊልሚያ ዛሬ በወያኔ የዘር ፓለቲካ ተተክቶ ዳግም ሞት ህዝባችን ይሞታል። ትሻልን ትቶ ሁሌ ትብስን የሚያፈልቀው የሃገራችን ፓለቲካ አሁን ደግሞ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ነው። ቄሶቹ ሲያጠምቁም ስምህን ቀይረው ነው እያሉ የሚያላዝኑ የሙታን ሙሁር ነን ባዮችን አፍርታለች።
  የውሸት ድሪቶ የተላበሰው የኦሮሞ ፓለቲካ ያለፈን እያላዘነ ከወያኔ በከፋ መልኩ ዘርና ቋንቋውን ተገን አርጎ ከክልሌ ውጡልኝ፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፤ አማርኛ ቋንቋ ጨቋኝ ቋንቋ ነው ወዘተ እያሉ መደንፋታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። በመግለጫና በስብሰባ ዲስኩር የደነቆረቸው ይህች መከረኛ ሃገር በህልም ዓለም ለሚኖሩ ወይም በዘርና በጎሳቸው ተጠግተው ጠበንጃን አንግተው ሌላውን የሚያንገላቱ ብቻ የሚወላዱባት ሆናለች። በቅርቡ ለቁጠር የበዙ ተፎካካሪ ፓርቲ አባሎች መጪውን ምርጫ አስመልክተው ከመንግሥት ጋር ባለመግባባታቸው የራብ አድማ ሊያደርጉ ነው መባሉን ሳነብ ወደው አይስቁ አሳሳቅ ዓይነት አሳቀኝ። ይገርማል። የደላው ሙቅ ያኝካል ይላሉ አበው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ጦሙን እያደረ አይደል የኖረው። ባለመብላት መፍትሄ የሚመጣ ቢሆን ኑሮ እንደ ሃገራችን ህዝብ የተራበ በምድር ላይ የለም። ዝም ብሎ የፓለቲካ ጫወታ ነው። በራስና በህዝብ ስም ገበጣ ጫወታ!የእነርሱ ሶስት ጊዜ በልቶ ማደር የነዲያን ሃገር የሆነችውን ኢትዮጵያን ሁሉን አብልታ ታሳድራለች ብሎ ማሾፍ ነው። አብዪታዊ ዲሞክራሲ የፓለቲካ እይታችን ነው ይላሉ ወያኔና ኦዴፓ/አደፓ… ይህ ውሸት ነው አብዪታዊ ብሎ ዲሞክራሲነት የለም። ደም ማፋሰስ እንጂ! በአለም ላይም በየትኛውም አህጉር ዲሞክራሲ የለም። መሰል ዲሞክራሲ ስርዓቶች ግን አሉ። ተጨፈኑና ላሞኛቹሁ የሚሉ አይነቶች። የአሜሪካው እንደ ምሳሌ ተጠቃሽ ይሆናል!የአልቃሽ አስለቃሽ እየተፈራረቀ ፍዳ በሚያሳያት በዚህች ያልታደለች ሃገር ትላንት ጀግና የተባለውን በማግስቱ በጥይት ደብድቦ የሚገል ሥርዓት ያለባት ሃገር ናት። ሰው ገድሎ የሚፎከርበት ምድር!ኦሮሞው ተሳደበ በማለት ተበሳጭተው ተመልሰው ራሳቸው የስድብ ጋጋታ የሚያሰሙ፤ ትግሬው በደለኝ ብለው መልሰው ለመበደል ድንጋይ የሚፈነቅሉ፤ አማራው እንዲህ እና እንደዚያ አደረገ ብለው ሃበሳውን ዛሬም ከወያኔው ዘመን የበለጠ መራራ ለማድረግ የፓለቲካ አሻጥር የሚነዙትና እሳት የሚያቀብሉት ሁሉ አበሮ መጥፋት እንዳለ አይታያቸውም። ለወገን ለሃገር አንድነት በማለት በድር በበረሃው በመንከራተት ሃገርን ያቀበሉን ሁሉ ከሞላ ጎደል አፈር ተመልሶባቸዋል። ወያኔ የጀግኖች የልጅ ልጆችን ሳይቀር እንደመነጠረ ህዝባችን ያውቃል። ስለሆነም እሳቱ በምድሪቱ ቦግ ብሎ ይንደድና ይለይለት ባይ ነኝ። አስለቃሽዋ እንዳለቸው።
  ያን ማዶ ተራራ እርጥቡ ጋረደው
  ገብቶ የነደደው ደርቅ ደረቱ ነው። አሁን ግን ደርቅም እርጥብም አብሮ ይጋያል። የብሄርና የጎሳ የዘር ፓለቲካ ፍትጊያ ውስጥ ቋሚ ወሬ ነጋሪ አይኖርም። ቆይተን እንይ!

  Tesfa
  October 9, 2019 at 7:38 pm
  Reply

 4. ወንድሜ፤ ለመታረም ዝግጁ የሆነ ሰው ሲገኝ እኮ ነው የሚታረም። ዐውቆ ሆን ብሎ በጥፋትና በተንኮል ጎዳና ጥላቻን ተሞልቶ የሚሄደውን የጃዋር ነው ጀዋር? ዓይነቱን ግን አርማለሁ ማለት ከንቱ ሞኝነት ነው። ዓላማውም እስላማዊ መንግሥት ነው። ለጊዜው እሬቻ ገዳ እያለ ዘመዶቹን ያታልላል። ይልቅ የሚበጀው ሌላ የመዳኛ መንገድ መፈለግ ይመስለኛል። እግዚአብሔርም ኢትዮጵያን ጥሎ አይጥላትም። በእኛ ሞኝነት ይሁን ፍርሃት ግን ብዙ ወገኖቻችን እያለቁ ነው።

  ethio
  October 9, 2019 at 10:10 pm
  Reply

 5. We need to weed out those power hungry individuals that want to be hero from zero.PM Abiy had spent his lifetime fighting for Ethiopia, proving he is intelligent world class leader that started from zero through hard work and countless selfless sacrifices ended up being a hero that no other person alive right now can match. That being said those that go against him are doomed to be getting their a**ses whipped. We are ready at any place be it in diaspora or not they going to get whipped, nowhere to run for the broken power hungry , nephtegna symphatizers, haters of Abiys administration.

  Gashaw
  October 10, 2019 at 4:13 am
  Reply

  • kimalam gashaw

   mindenew yemitilew selay shkabach le siltenew yemitrotew

   yejimila chifchefawun antene yemitmeraw ashebario siponseru antenhe tikikil new tplf siltan setachuh afachuhun awutitachuh menager jemerachuh derrg eko lijihun eyegedele yetiyiyt kifel yilih neber

   ebet yenefsegeday lij wushetam haymantotegna tabot shach yanech bariya yakum eseregna arfeh sahinihin eteb

   daniel kibret siltan ena genzeb new yemirotew genzeb filega wushetam ye kebero melkitegna gibbot esat selay new

   weyanew
   October 10, 2019 at 11:46 am
   Reply

   • You are the beggars that sucked the Ethiopian blood , took everything we Ethiopians had and run to the hellwhole you climbed out of ,you should be glad for the mercy the PM Abiy extended to you ,Qizenamoch .

    Gashaw
    October 13, 2019 at 12:30 am
    Reply

 6. ማረም ማለት!!!? ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን ማለት ነው? ወይም አይተው እንዳላዩ? እኔን የሚመስለኝ ግን ከስሩ መንግሎ መጣል ነው፡፡

  ስዩም
  October 10, 2019 at 8:17 am
  Reply

 7. Amhara region should be divided into four according the histrical heritage wollo,gonder,gojam and shewa. We then can we cooperate and work together. Amhara is a baseless TPLF made nation and region. Let us come to the right way by making amhara region four regions and help them to work jointly. Otherwise what is expected is the unexpected.

  Son
  October 10, 2019 at 10:02 am
  Reply

 8. የዚህ ጽሁፍ ጭብጡ ምንድነው ተናግሬ ነበር ከማለት ባሻገር?

  ሰመረ
  October 10, 2019 at 10:24 pm
  Reply

 9. Jawar, Bekele and the Oromo intellectuals are is very respected and honored not only among the Oromo, but also among other freedom loving Ethiopian peoples.  All those who are campaigning against Bekle Gerba, Jawar Mohammed only the ultranationalists of Amahara. They have been accusing them only due to their persevering stand about the demands of the Oromo people. Thus, their hatred is not directly about Bekele  or Jawar as a person, but it is the reflections of their feelings against the great Oromo people. But all such attempts will be nullified as usual. No one can stop the nation from achieving its objectives. The De-Amharaization process of the Ethiopian politics will be processed with an interesting speed.

  Endalkachew
  October 11, 2019 at 2:54 am
  Reply

 10. Abiy deserves the gold medal , just because he is a mercenary fundded by those who award him with isayas afewerki in arab world. coldblooded messanger of arabs who want to see ethiopia destroyed .

  UNHCR likes abiy .that he maintain peace. does unhcr like peace or war mongers who kill people and produce refugees ? I am confused and I guess everyone is perplexed with this kind of sataric and ironic message ???
  Amhara is messenger of those who want detsroy ethiopia
  amhara sex with animals and amhar is killer, kuwanja korach not oromo

  bandaamhara
  October 11, 2019 at 12:35 pm
  Reply

 11. Serenity Now!!

  There are two kind of problems in these world.

  1. Problems that can be corrected/fixed.

  2.Problems that cannot be corrected/fixed.

  Look at it this way when people get into a cat accident they see the damage and decide whether to get the car fixed/corrected or they decide to call it totalled and cut their losses then search for another car.

  Having a wisdom to know the difference between the above two kind of problems, is what our country is not yet capable of, for example the current con institution of Ethiopia drafted by con artists Meles Zenawi & Co. need to be changed not corrected. The current con institution got too many flaws it is beyond repair, it is better to draft a new real constitution rather than trying to correct Meles Zenawi & Co.’s con institution.

  Tadiyos
  October 14, 2019 at 5:34 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.