እያንሰራራ የመጣው ኦነጋዊ ፋሽዝም በኢትዮጵያ!

1 min read

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት               ረቡዕ መስከረም ፳፰  ቀን ፪ሺህ፲፪..                      

ቅጽ ፯ቁጥር ፲፮

 

“ … እንደ ዐማራ ትንሽ ማሰብ ያለብን ጊዜ ብቻ ስይሆን ፤ መስራት  የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። በታሪካችን ወደ ኋላ ሂደን ከ500 ዓመት  በፊት እንዲህ ያለ ትልቅ ፈተና ገጥሞን ነበር። አሁን ከዚህ ደርሰናል። ….አሁን ትንሽ ጠንከር ያለ ፈተና አለ። የትም ቦታ በዘራችን የመጠቃት  ስሜቶች አሉ። ይህን የመቀልበስ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው።… ልዩ ኃይል ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ።”

( የዐማራ ሕዝብ ጀግና መስዋዕቱ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ አዲስ ለሰለጠኑ የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተናገሩት፤ ሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ/ም፣ ባሕር ዳር፣ ኢትዮጵያ )

                 እና

“ የኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነው የተሰበረው። እዚህ ነው ውርደት የጀመረው።…. ዛሬ ነፍጠኞች በሰበሩን ቦታ ላይ፤ ራሳቸውን ሰብረን፤ ከስሩ ነቅለን  ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ተከብሯል። ኦሮሞ እንኳን አሸነፍክ።”

( የኦሮሞ ክልል ተብየው ምክትል ፕሬዝዳንት ግራዚያኒ ሽመልስ አብዲሳ፤ የኢረቻ ክብረ በዓል ለማክበር በመስቀል አደባባይ ለተሰበሰበው የኦሮሞ ሕዝብ ያደረገው ጦርነት ቀስቃሽ ንግግር፤ መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ/ም፤ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ)

ጀግናው ጄኔራል አሳምነው ጽጌ እንደተናገሩትና የዐማራን ሕዝብ እንዳስጠነቀቁት፤ ከ500 ዓመት በፊት ነባር ኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ምን ችግር ገጠማቸው? ምን አስከፊ ነገር ተፈጠረባቸው? በአሁኑ ሰዓት ልባቸው ያበጠው የኬኛ ኦነጋውያን የሃሰት ትርክታቸውን ትተው፤ እውነተኛው ታሪካቸውን እንዲያውቁ ወደ ኋላ 500 ዓመት ተጉዘው በዓለም ላይ ያሉትን የታሪክን መዛግብት እንዲመረምሩ አጥብቀን እንጠይቃለን። እኛም ከታሪክ መጽሐፍት ያገኘነውን በአጭሩ እናቀርባልን።

የዛሬ 476 ዓመት ማለትም በ1543 እ.አ.አ. የኦሮሞ ሕዝብ ከሰፈረበት የሱማሌ መሬት፤ የሱማሌ ነባር ጎሳዎች ቢናድሮችና ባንቱዎች በጣምራ በከፈቱባቸው ጦርነት ተገፍተው ከወጡ በኋላ፤ በግራኝ መሐመድ ጦርነት ወደ ተዳከመችው ኢትዮጵያ ሰተት ብለው ሲገቡ መሬቱን ማርና ቅቤ እየቀቡ፤ ለነባር ሕዝቡ ቀጤማ እየሰጡ በስላም አልገቡም። በታሪክ ታይቶ ተስምቶ የማይታወቅ ወረራ በማካሄድ ነባር ጎሳዎችን እየጨፈጨፉና እያፈናቀሉ (ዐማራ፣ ሀዲያ፣ ከንባታ፣ ሚያ፣ ዳውሮ፣ ዳሞቴ ወዘተ…)፤ ግማሾችን በባርነት በማስገበር አገልጋይ በማድረግ የኦሮሞ ማንነት በግዴታ በመጫን ማንነታቸውን በማስቀየር (ሲያሞካሹት ሞጋሳ የሚሉት)፤ የዋቄ ፈታ እምነት ተከታዮች በመሆናቸው አብያተክርስቲያናትን እና መስጊዶችን እያቃጠሉ፤ ንብረት እየዘረፉ፤ የወንድ ብልት እና የሴት ጡት እየቆረጡ፤ አንገት እየቀሉ፤ የነባር ቦታዎችን ስሞች እየቀየሩ (ባሊ – ባሌ፣ ፈጠጋር – አርሲ፣ ደዋሮ – ሐረር፣ ግራርያ – ሰላሌ፣ እናርያ – ኢሊባቦር፣ ላኮመልዛ – ወሎ፣ አንጎት – ራያ ወዘተ…)፤ በጣም የከፋውና ታሪክ ይቅር የማይለው ደግሞ አንዳንድ ነባር ጎሳዎችን (እንደ ጋፋት ወዘተ…) ባካሄዱት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ከምድረ ገጽ በማጥፋት ነበር ነው ኢትዮጵያን ለብዙ መቶ ዓመታት ትርምስምሷን ያወጧት። ስለዚህ፣ ታሪክ ይመስክር ማነው ወራሪ ማነው ተወራሪ? ማነው መጤ ማነው ነባር? ማነው ጨፍጫፊ ማነው ተጨፍጫፊ? ሃቁ ይውጣ ከተባለ፤ በዛሬዋ ኢትዮጵያ መሬት በነገድ ይከፋፈል (ይታደል) ቢባል፤ መጤው የኦሮሞ ነገድ አንድ ጋት መሬት አይኖረውም።

እ.አ.አ. በ1543 ዓ/ም ኦሮሞዎች ወደ ኢትዮጵያ በወረራ ከመግባታቸው በፊት፤ የዛሬዋ አዲስ አበባ ከተማ የድሮዋ በረራ በአጼ ዳዊት ቀዳማዊ ዘመን ( 1380 – 1413 ) የተመሠረተች ናት። ይህ ማለት፣ ኦሮሞዎች ወደ ኢትዮጵያ ከመግባታቸው 153 ዓመት በፊት ማለት ነው። ስለዚህ፣ የት ላይ ታዲያ ነው ኦሮሞ የተሰበረው? መቸ ከሱማሌ እና ከሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ተንቀሳቀሰና። ታሪክ የሚያሰረዳው ይኸንኑ ነው። የኦነጋውያን የሀሰትና የፈጠራ ትርክት የትም አያደርስም። እንኳን አዲስ አበባ፤ አሁን ኦሮሞ ያለበት ቦታዎች በሙሉ፤ ወለጋ፣ ጅማ፤ ኢሉባቡር፣ አሩሲ፣ ባሌ፣ ሐረር ወዘተ.. የነባር ጎሳዎች አጽመ-ርስቶች ናቸው። አሁን ግን፤ በወረራ ተይዘዋል። የታሪክ ዶሴ ሲከፈት የሚመሰክረው ሃቅ ይኸው ነው።

የወቅቱን የኦሕዴድ-ኦነግ ጣምራ ከፍተኛ ሴራ የተገነዘቡት፤ ለዐማራው ሕዝብ የተሰውት ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከላይ የጠቀሰነውን ንግግር የተናገሩት፤ ሁለተኛ ዙር ከበባና ጦርነት በዐማራው ሕዝብ ላይ እንደተጠነሰሰ አስቀድመው በማወቃቸው ነበር። እኛም በበኩላችን የኮሎኔል ዶ/ር አብይ አሕመድ “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” እንዲሁም የአቶ ለማ መገርሳ “ኢትዮጵያ ሱስ ናት” አነጋገር ለኢትዮጵያውያን ያፍዝ አደንግዝ ምትሃት እንደሆነ በተለያዩ መግለጫዎቻችን አስታውቀናል። ከዚህም በላይ፤ ትሕነግ/ሕወሓት እና ኦሕዴድ-ኦነግ እየተናበቡ በሚስጥር ስለሚሠሩ፤ የዐማራው ሕዝባችን በሰሜን ከትሕነግ/ሕወሓት፤ በደቡብ ከኦሕዴድ-ኦነግ የሚደገስለትን ከበባ እና ጦርነት ከወዲሁ አውቆ እንዲጠነቀቅ በተደጋጋሚ አሳስበናል።

ኦነጋውያን ከፍተኛ እርምጃ የጀመሩት፤ በረቀቀ ዜዴና በተቀነባበረ ሴራ አራቱ የዐማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በባሕር ዳር ከተማ ከተገደሉ በኋላ ነው። ይኸም፣ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ የተገደሉት አዲስ ለሰለጠኑ የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ምረቃ ሥነ-ሥረዓት ላይ በዐማራ ሕዝብ ላይ የተሽረበ ሴራ እንዳለ በንግግራቸው በገለጹ በ5ኛው ቀን ነበር።

የጸረ-ዐማራ እና በጸረ-ኢትዮጵያ የጥላቻ መርዝ አጥንቱ ድረስ ዘልቆ የገባበት ግራዚያኒ ሽመልስ አብዲሳ መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ወደ 50 ሚሊዮን የሚገመተውን የዐማራ ሕዝብ እየሰደበ ቅርሻቱን የተፋው፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከፍተኛ ዶላር እያፈሰሱ ያደራጁትና ያስታጠቁት ኦነጋዊ ፋሽዝም በኢትዮጵያ በሩን መክፈቱን ያመለክታል። ኦነጋውያን እንደ ቅድመ-አያቶቻቸው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን በኢትዮጵያ ላይ 2ኛ ዙር ወረራ ለመክፈት መዘጋጀታቸውን በቀጥታ እና በግልጽ የሚያሰረዳ ነው። ለዚሁ ወረራ ቀን ከሌት ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ፕሮፓጋንዳ እያካሄደ በዐማራው ሕዝባችን ላይ መርዝ የሚረጨው የአረብ ቅጥረኛ በሆነው በሃጅ ጀዋር መሐመድ የሚመራው የኦነጋውያን ልሳን የሆነው የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (Oromo Media Network-OMN) ነው።

የግራዚያኒ ሽመልስ አብዲሳ ጸረ-ዐማራ እና ጸረ-ኢትዮጵያ ንግግርን ከታሪክ ምዕራፍ ጋር ስናገናዝብ፤ የዛሬ 79 ዓመት የጣሊያኑ ፋሽስት መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ አገር በመውረር ታላቁን የጣሊያን ግዛት ለመመስረት በማቀድ ሮም አደባባይ ላይ እ.አ.አ. ሰኔ 10 ቀን 1940 ዓ/ም ለጣሊያን ሕዝብ ያደረገውን ንግግር ያስታውሰናል። ፋሽስቱ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በጣሊያንኛ ያደረገውን ንግግር ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ከተተረጎመው ውስጥ አንዱን ብንጠቅስ እንዲህ ይላል፥

“There is only one order. It is categorical and obligatory for everyone. It already wings over and inflames hearts from the Alps to the Indian Ocean. Conquer!’’

ወደ አማርኛ ቋንቋ ሲተረጎም፥

“ አንድ ትእዛዝ ብቻ ነው ያለው። እርሱም፣ ለእያንዳንዱ አስፈላጊና ግዴታዊ የሆነ ነው። ከአልፕስ እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ አስቀድሞ የተዘረጋ እና ልቦችን የሚያቀላ ነው። ውረር!”

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!

ተስፋፊው እና ትምክተኛው የጣሊያን ፋሽዝም ድባቅ ተመቶ የታሪክ ትቢያ እንደሆነ ሁሉ፤ ለወረራ የተዘጋጀው አደገኛው ጠባቡ እና ጨካኙ ኦነጋዊ ፋሽዝም ማንኛውም ሃገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ በህብረት ተነስቶ መመከትና ዳግም እንዳያንሰራራ መመታት ያለበት ነው። በትዕቢት የተወጠረው ኦነጋዊ ልብ መተንፈስ አለበት። በመራራው ትግልህ የትሕነግ/ሕወሓት ፋሽዝም አንኮታኩትህ እንዳንበረከክ ሁሉ፤ የአደገኛውን የኦሕዴድ-ኦነግ ፋሽዝም ድባቅ መትተህ የኢትዮጵያ ሃገርህን አንድነት፤ ነጻነት እና ሉዓላዊነት አስከብር።

 

የዐማራ ሕዝብ ሆይ!

የዛሬ 476 ዓመት በአባቶቻችና በእናቶቻችን የመጣባቸው ከበባና ጭፍጨፋ በአንድ አቅጣጫ ነበር። የዛሬው ከበባ ለየት የሚያደርገው በሁለት (2) አቅጣጫዎች ከሰሜንና ከደቡብ መሆኑ ነው። ይህን የከበባ ጦርነት የሚያካሂዱት የዐማራው ጣምራ ጠላቶች የሆኑት ትሕነግ/ሕወሓት እና ኦሕዴድ-ኦነግ ናቸው። ይኸን ከወዲሁ ተረድተህ፤ ቀደም ሲል አባቶቻችን እንዳደረጉት በየቀየህ በጎበዝ አለቃ ተደራጅትህ የሚመጣብህን ወራሪ ተከላከል። በቁም ከሞተው ብአዴን ምንም ነገር አትጠብቅ። ለጠላቶችህ መሳሪያ ሆኖ 28 ዓመት ያስቀጠቀጠህ እና በማስቀጥቀጥ ያለው ብአዴን ነው። ብአዴን ቀደም ሲል የትሕነግ/ሕወሓት ተላላኪ በመሆን እንዳስጠቃህ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ የኦሕዴድ-ኦነግ አሽከር በመሆን እያስጠቃህ ይገኛል። የጀግኖች አባቶቻችንን እና እናቶቻችንን ወኔ ሰንቀህ ወራሪ ጠላቶችህን መክተህ ወደ መጡበት መልስ።

 

በተጓዳኝ፣ በሰኔው 15 ቀን 2011 ዓ/ም የዐማራ መሪዎች ግድያ ሳቢያ በኦሕዴድ-ኦነግ ትዕዛዝ ቅጥረኛው ብአዴን ያሰራቸው እና በእስር እንዲማቅቁ ያደረጋቸው የዐማራው ሕዝብ የቁርጥ ቀን ከፍተኛ መኮንኖች እና ሲቪሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማድረግ በተቀናጀ መልክ፤ ሲሆን በዋና ዋና የዐማራ ክልል ከተሞች ካልሆነ በክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር የ2 ወይም የ3 ቀን የስራ ማቆም ወይም እቤት ውስጥ የመዋል አድማ እንዲጠራ እና በተግባር እንዲውል በዐማራ ወገናችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

አዲስ አበቤ ሆይ!

በየቀኑ የኦነጋውያን ብትር እየደረሰብህ ነው። ቤትህን፤ ንግድህን፣ ስራህን እየተቀማህ ነው። ደህንነትህ አደጋ ላይ ነው።  ወጥቶ ለመመለስ ዋስትና የለህም። እምነትህ እና የተቀደሱ የእምነት ቦታዎችህ እየተደፈሩ ነው። የከተማይቱ ባለቤትነትህን እየተነጠቀ ነው። ለዓለም ሕብረተሰብ ያለህበትን አሰቃቂ ሁኔታ ለማሳየት፤ በቅንጅት ወቅት እንዳደረከው ሁሉ፤ አሁንም ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስማት በተጠናከረ መንገድ በውስጥ ለውስጥ መስመር ተደራጅተህና ተናበህ የኦነጋውያንን ፋሽዝም ለማጋለጥ 2 ወይም 3 ቀን የሚወስድ መሬት አንቀጥቅጥ የሥራ ማቆም ወይም የቤት ውስጥ የመዋል አድማ  እንድታደርግ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ አዲስ አበባችን የዓለምን ህብረተስብ ዓይን የምትስብ ከተማ ስለሆነች፤ በትራንስፖርት ዘርፉ የተሰማራችሁ፣ የንግዱ ማህበረስብ እና ተማሪዎች በዚህ አድማ ግንባር ቀደም እና ታላቅ ሚና መጫዎት እንደምትችሉ እናሳስባለን።

 

በውጭ ሃገራት የምትገኙ የዐማራ ተወላጆች ሆይ!

በዐማራው ሕዝባችን ላይ የሚያንጃብበውን ከፍተኛ አደጋ ተገንዝባችሁ በደንብ የምትተዋወቁና የምትተማመኑ የዐማራ ድርጅቶች፤ ማህበራት፣ ታጋዮች፤ ምሑራን፣ ወጣቶች ወዘተ… በአስቸኳይ በያላችሁበት ተሰባሰቡ፤ በከፍተኛ ንቃት በየእለቱ የሚካሄዱትን ሁኔታዎች ተከታተሉ። የዐማራው ሕዝብ ጣምራ ጠላቶች ትሕነግ/ ሕወሓት እና ኦሕዴድ-ኦነግ የዐማራውን መሬት በወረራ ለመንጠቅ በጎንደርና በሰሜን ሸዋ ጦርነት ከፍተዋል። ይህ ጅምሩ ነው። የሚደገስልን ከፍተኛው ወረራ እየመጣ ነው። ስለዚህ፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን የትውልድ ኃላፊነት በብቃት መወጣት አማራጭ የሌለው በመሆኑ፣ ጠላትና ወዳጅን የለየና በአንድ ጎራ ቆሞ የተናበበ ትግል በማድረግ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ አስወግዶ ኢትዮጵያን እንዲታደግ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

በመጨረሻም፥

ባለፉት 28 ዓመታት በትሕነግ/ሕወሓት እና በኦሕዴድ-ኦነግ ጣምራ ኃይል መሪነት እንዲሁም ብአዴንና መሰል ተባባሪዋቻቸው እጀታነት በዐማራ ሕዝብ ላይ በተካሄደው የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማራ ወገኖቻችን አልቀዋል። አሁንም በዚች ሰዓት እያለቁ ነው። የዐማራው የህልውና እና የማንነት ተጋድሎ መከታ የሆኑት የጎበዝ አለቆቻችንን ከኦሕዴድ-ኦነግ ጦር ኃይል ጋር እየተባበረ የሚያስገድለው እና የሚገድለው ብአዴን ነው። መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ/ም የሆነውም ይኸው ነው፤ ብአዴን የዐማራ ሕዝብ ጀግናውን ሻለቃ አስቻለው ደሴን አስገድሎና ገድሎ በዐማራው ሕዝብ ላይ እየፎከረ ነው። ስለዚህ፣ የዐማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ከጎኑ ያለው ባንዳውና ቅጥረኛው ብአዴን ነው። ብአዴን! ነገ አይቀሬው መሬት አንቀጥቅጥ ሕዝባዊ አብዮት ሲመጣ ለከፍተኛ ሕዝባዊ ፍርድ እንደምትቀርብ ከወዲሁ እናሳውቅሃልን።

በዚህ ምክንያት፣ ትግላችን መራራ እና እረጅም ትውልድ ተሻጋሪ ሆኗል። በመሆኑም፣ ከዘመኑ የትግል ስልት ጋር የሚመጣጠን ትውልዳዊ ትግል ተጠናክሮ በቆራጥነት እና በጽናት በገጠር እና በከተማ በወጣቱ፣ በጎልማሳው፣ በሴቶች፣ በአዛውንቶች፣ በሃይማኖት አባቶች ወዘተ… ልብ ውስጥ ተቀጣጥሎ እንዲቀጥል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ታሪካዊ የትግል ጥሪውን ያቀርባል።

 

መጤዎች እንዲያውቁት፥

ነፍጠኛ ነፍጥ (የጦር መሣሪያ) ታጥቆ አገር ወራሪ ሲመጣ የአገሩን ነጻነት እና ዳር-ድንበር ለማስከበር ከወራሪው ጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ፤ ደሙን የሚያፈስ አጥንቱ የሚከሰክስ አርበኛ ነው። የ3 ሽህ ዓመት የታሪካችን ገድል የሚያስረዳውም፣ የሚያስተምረውም ይኸንኑ ነው። ስለዚህ፣ እኛም ከአባቶቻችን እና ከእናቶቻችን በወረስነው ሃገራዊ ወኔ እና ፍቅር መሠረት፤ ትላንትም ነፍጠኞች ነበርን። ዛሬም ነፍጠኞች ነን። ነገም ነፍጠኞች እንሆናለን። ዝንተ-ዓለምም ነፍጠኞች ነን።

 

እምዬ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

የዐማራው ሕዝብ ኅልውናና ማንነት በጀግና ልጆቹ ይከበራል!

ጀግናው አሳምነው ጽጌ የትግላችን ቀንዲል ነው!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

 

2 Comments

  1. አንድ ፋሺስት ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቢኖር ሞረሽ ወገኔ ነው!
    “ትላንትም ነፍጠኞች ነበርን። ዛሬም ነፍጠኞች ነን” ካላችሁ፣ ባለፈው የነፍጠኛ ስርዐት በኦሮሞ እና በደቡብ ህዝቦች ላይ ለተፈጸመው እልቂት፣ ሰቆቃ፣ ጭቆናና በፖሊሲ ደረጃ ለተፈጸሙ አካላዊና ባህላዊ ጀኖሳይድ ሃላፊነት ወስዳችኋል ማለት ነው! ለጀርመን ናዚዎች የኑርንበርግ ፍርድ ቤት ተቋቁሞ የእልቂቱ ወንጀለኞችን ለህግ እንዳቀረቡትና እስከዛሬም በወንጀል እንደሚፈለጉት ሁሉ፣ እናንተም ለፍርድ ትቀርባላችሁ! እስከዚያው መደንፋት ትችላላችሁ፣ ወንጀላችሁን እያመናችሁ መሆኑን ግን እወቁ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.