አንድነት ፓርክ ተመረቀ (ኢ.ፕ.ድ)

1 min read

በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራው የአንድነት ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ ተመረቀ።

በፓርኩ ምረቃ ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች እና አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

እንዲሁም የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

በዛሬው እለት የተመረቀው የአንድነት ፓርክ የመደመር እሳቤ ማሳያ ነው ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት።

በዛሬው እለት የተመረቀው የአንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት የሚደረግ ይሆናል።

በዚህም መሰረት በነገው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራውን የአንድነት ፓርክ የሚጎበኙ ይሆናል።

ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ በእድሜ ታላላቅ ዜጎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤተ መንግስቱን እንደሚጎበኙም አስታውቀዋል።

ከስኞ ማለትም ከጥቅምት 3/ 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት እንደሚችልም ተገልጿል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢሲ ነው።

https://www.facebook.com/EBCzena/videos/725071807919006/?t=45

1 Comment

  1. GOOD JOB !!!
    Congratulations Dr. Abiy !
    Your name will be written in golden ink in the annals of Ethiopian History.
    God bless Abiy and Ethiopia !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.