የእሁዱ የአዲስ አበባ ሰልፍ ተፈቅዷል

1 min read

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እሁድ ለሚደረገው ሰልፍ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ ፕሬስ እንደዘገበው፣የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ከነገ በስቲያ እሁድ ጥቅምት 2 የጠራውን ሰልፍ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት አቶ ጌቱ አርጋው ለአሃዱ ኤፍ ኤም ገለፁ።
ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ሰልፉ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፦ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከብሄራዊ ትያትር ወደ መስቀል አደባባይ፣ መሿለኪያ፣ ከውጭ ጉዳይ እስጢፋኖስ ፣ መስቀል ፍላወር እስከ ደምበል ሲቲ ሴንተር፣ ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ ወደ ሰልፉ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና
0111 -11- 01-11፣
0111- 26- 43- 59፣
0111- 01- 02- 97፣ መጠቀም የሚችል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታቋል።
Addis Ababa Press

 

***

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.