አቶ አዲሱ አረጋ ሰከን ይበሉ!

1 min read

አቶ አዲሱ አረጋ የኖቤል ሽልማቱን አስመልክቶ የደስታ ሰልፍ ጥሪ አድርገዋል።ያ ችግር የለውም።
ችግሩ የሰልፍ ጥሪ ያደረጉት ለጥቅምት 2 ቀን ነው መባሉ ነው።

ሁሉም እንደሚያውቀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው ባላደራው ምክር ቤት ከሳምንታት በፊት አንስቶ ለጥቅምት 2 ቀን ሰልፍ ጠርቷል። ለአዲስ አበባ መስተዳድር አሳውቋል። መስተዳድሩ በተቀመጠለት ጊዜ ምላሽ ባለመስጠቱ በህጉ መሰረትም ሰልፉ እንደተፈቀደ ተቆጥሯል። ያንንም ተከትሎ ዛሬ ጧት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ይህ ሁሉ ሂደት ካለቀ በኋላ ድንገት ብድግ ብሎ ለጥቅምት 2 ሰልፍ ጥሪ ማድረግ፤ ሆን ብሎ ግጭት ለመቀስቀስ ማሴር ነው። የተወሰኑ የተላኩ ወጣቶች (ዛሬ ጧት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኒቬል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው በታወጀበት ሰዓት ሳይቀር) ፤ ጋዜጣዊ መግለጫውን ለማደናቀፍ ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።ወጣቶቹ የኦነግ ሳይሆን የኦህዴድ ካድሬዎች መሆናቸውም ታውቋል። በዛሬው የዓለም ትልቅ ሽልማት ዕለት ከተለያዩ አቅጣጫዎችወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶች ተዘግተው ተጓዦች ወደመጡበት መመለሳቸውንም ሰምተናል።በሥልጣን ላይ ያሉ አካላት በዚህ ዐይነት ትንኮሳ እና ማስፈራራት የዜጎችን መብት ማፈን ሊያቆሙ ይገባል።

እስክንድርም፣ ተከታዮቹም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሃሳባቸውን የመግለጽም ሆነ የመሰለፍ ህገ መንግስታዊ መብት አላቸው። የተገኘው የኖቤል ሽልማት እነኚህ መብቶች ይበልጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያበረታታ እና ጉልበት የሚሰጥ እንጂ፤ የዘዴ አፈናን ለማበረታታት የሚውል አይደለም።

አቶ አዲሱ ረጋ ይበሉ!! ሰከን ይበሉ!!! ካልጠፋ ቀን ዛሬ ተነስተው ለጥቅምት 2 ጥሪ ማድረግዎ ክፋት ነው። ያርሙ።

2 Comments

 1. በዚህ ጉዳይ እኮ ብዙ መጨነቅም ብዙ ማሰብም
  ተገቢ አይደለም:: የታየ የአደባባይ ሚስጢር ነው::
  ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ በጳጳሳት ስብሰባ በድንገት
  እንዲገኙና ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁ ጊዜ
  እሽ: እሽ: እሽ: ብለውና ይቅርታ ጠይቀው እንዴት
  ሲባል እንዴት ታስቦ ነው የኦሮሚያ ተዋሕዶ ቤተ
  ክርስቲያን የሚሉት የሚቋቋመው ማለታቸው ይታ
  ወሳል:: በዚያው ቅጽበት ከመቸው ደረሱ እስኪባል
  ኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ(OMN) ቢሮ ደርሰው
  አላልኩም ዓይኔን ግንባር ያድርገው ማለታቸውም
  ይታወሳል::
  እኒሁ ጉደኛ ሰው በእሬቻ የምስጋናና የሠላም በዓል
  ላይ ጉደኛ ቀረርቶና ፉከራ አድርገው በ97 ኦቦ ጁነዲን
  ሳዶየዛሬውን አያድርገውና እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን
  አዳማ ስትመጡ እንተያያለን ብለው ያን ጊዜ ክርክሩን
  ያዳመጠና የተመለከተ ሰው ሁሉ አስደምመዋል::

  አሁንም የዛሬውንአያድርገውና ፕሮፌሰሩ የያኔውን
  ሌላኛ ተከራካሪያቸውን አቶ በረከት ስምኦንን በስም
  ጠርተው እኔና እርስዎ እዚያ ከጦር ሜዳ እንተዋወቃለን
  እኒህ ደግሞ ከወዴት የመጡ የድል አጥቢያ አርበኛ ናቸው
  ሲሉ የዛሬውን ታሳሪየያን ጊዜውን አሳሪ እንዳስደመሙና
  ፈገግ እንዳሰኟቸታስታውሳላችሁ ብየ እገምታለሁ::

  ኦቦ ሽመልስ በደነፉ ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት ይሁን
  በሌላ ተገፋፍተው ባይታወቅም ኦቦ አዲሱ አረጋ ኦቦ
  ሽመልስን ተረጋጋ የሰበረም የተሰበረም አልነበረም
  አሁንም የለም እንዳሉ ይታወቃል:: መቼም በዚያ
  ቤት ማን በል አለህ ምንስ ቤት ነህ የሚል አዛዥ ናዛዥ
  እንዳለ ሳይታለም የተፈታ ይመስላል:: እናማ እንሂንም ሰው
  ያው አዛዥ ናዛዥ ቁጭ ብድግ እንዳስደረጋቸው ብንገ
  ምት ስህተት ነው አንባልም:: ለምን ቢባል መልሱ እንደ
  ኦቦ ሽመልስ በል ተብለውስ ቢሆንስ :: ሁኔታው እኮ ባፍ
  ይጠፉ በለፈለፉ ዓይነት ነው የሚመስለው:: የመሰላቸውን
  ይናገሩና መልሰው አላልኩም ወይም በጫና ማካካሻ ቢጤ
  አዛዥ ናዛዡን ያስደሰቱ መስሏቸው የማይታሰብ ማሰብ::
  እንዲያው ድንገት ከመኝታ ተነስቶ የሰላማዊ ሰልፍ ፊሽካ
  መንፋት:: አይ ሥርዓት አዲዎስ::

  • Addisu Arega is the most stupid gala who I came across and does not seem to have his own gray matter. Think about how many times he changed his mind when his Godfather the Lieutenant of Alkaida in East Africa, Jo war, criticized him about the things he said. So, my brother Mr. Solomon, although i respect your right to respectfully address this guy, arega is simply a shit.

   Another person I want to say about is Nigiusu Tilahun, the condom of gala, previously the condom of woyane.

   A big shame you say you call yourself Amhara. As one guy put it correctly, the things that the galas possess in Amhara kilil are Awash bank, OI bank and Nigusu`s party, the former EPDM.

   Praise the great ESKINDER NEGA, a GENTLEMAN and student of MARTIN LUTHER KING.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.