የተለያዩ ተቋማት ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው

1 min read

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 01፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የሀገር ውስጥ ተቋማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልክተው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ላደረጉት ጥረት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀው የድንበር የይገባኛል ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ተነሳሽነትን በመውሰዳቸው የ2019 የኖብል የሰላም ተሸላሚ ሆነዋል።

ይህንን ተከትሎም የተለያዩ የሀገር ውስጥ ተቋማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው።

በዚህ መሰረትም የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን፣ የኢፌዴሪ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ፅህፈት ቤት፣ አዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

FBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.