የዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማትና የኤርትራ ሁኔታ!  – በፍቃዱ ኃይሉ

1 min read

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥም እንዲህ እንደትላንቱ በደስታ እና በሙገሳ ተነስቶ አያውቅም። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያዊ ዜጋን ደጃፍ ያንኳኳው እና በዓለም በትልቅነቱ ወደር የማይገኝለት የኖቤል የሰላም ሽልማት ብዙዎች ዳግም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ተስፋ እንዲያጭሩ አድርጓቸዋል።

በፍቃዱ ኃይሉ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥም እንዲህ እንደትላንቱ በደስታ እና በሙገሳ ተነስቶ አያውቅም። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያዊ ዜጋን ደጃፍ ያንኳኳው እና በዓለም በትልቅነቱ ወደር የማይገኝለት የኖቤል የሰላም ሽልማት ብዙዎች ዳግም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ተስፋ እንዲያጭሩ አድርጓቸዋል። ለመሆኑ የሰላም ኖቤል ሽልማቱ እና የኢትዮ-ኤርትራ እርቀ ሰላም ለኢትዮጵያውያን እና ለኤርትራውያን ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?

ስለ ኖቤል ሽልማት ብዙ ተብሏል። ነገር ግን ዝናውን የሚያወርድ ነገር አልተገኘም። የዐቢይ አሕመድ መሸለምም የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ክብር ተደርጎ ነው በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተወሰደው። ብዙ ጊዜ ችግሮቻቸው ብቻ የዓለም መነጋገሪያ የሚሆንባቸው ኢትዮጵያውያን እንዲህ ባለ ሽልማት መሪያቸው ሲከብር መደሰታቸው አያስገርምም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል ተሸላሚ የሆኑበት ምክንያት ሲገለጽ “ለሰላምና ዓለም ዐቀፍ ትብብር ያደረጉት ጥረት” እንዳስመረጣቸው ተነግሯል፤ ይህንን በተመለከተ “ይገባቸዋል” ለማለት የሱዳን ተቃዋሚዎችን እና ወታደራዊ አመራሩን በማሸማገል የሔዱበትን ርቀት ማስታወስ ይበቃል። ሱዳናውያን በሁለቱ ጎራዎች ሥምምነት ላይ ሲደረስ ደስታቸውን ሊገልጹ አደባባይ ሲወጠ የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙት ለዚያ ነበር። በመቀጠልም ሽልማቱ የተሰጣቸው “በተለይ ከጎረቤታቸው ኤርትራ ጋር የነበረውን ግጭት ለመፍታት የወሰዱት ቆራጥ ተነሳሽነት” ታይቶ እንደሆነ ተገልጿል።

በአጭሩ ለማስታወስ ያህል የኢትዮ-ኤርትራ እርቀ ሰላም ፍፁም አስገራሚ ነበር። ለሁለት ዐሥርት ዓመታት በኩርፊያ የነበሩት አገራት ድንገት በጠቅላይ ሚኒስትር በር አንኳኪነት ተሰበረ። ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስመራ ሔደው የተደረገላቸው ሕዝባዊ አቀባበል በቴሌቪዥን ሲተላለፍ ብዙዎችን በደስታ እምባ አራጭቷል። የስልክ መሥመር ሲከፈት ሰዎች በደስታ አቅላቸውን አጥተው የማያውቁት ሰው የኤርትራ ቁጥር ላይ ደውለው አውርተዋል። የተጠፋፉ ቤተሰቦች ዳግም ተገናኝተው ተላቅሰዋል። ሰዎች በአፈና የዘነጉትን የእህትማማች፣ ወንድማማችነት ትዝታ ከተዳፈነበት ቆስቁሰው አውጥተውታል። በድንበር አካባቢ ያለው ጉርብትና ታድሶም በአጭር ጊዜ ገበያው ሲደራም ታይቶ ነበር። እናም ድርጊቱ በቅርብ ጊዜ በቀጠናው ከታዩ ክስተቶች ሁሉ እጅግ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነበር።

ለኤርትራውያን ግን…

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ባወረዱ ባጭር ጊዜ ውስጥ እልፍ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ የስደተኛ ካምፖች በገፍ ይጎርፉ ጀመር። በዚህ የተደናገጡት ኢሳይያስ ድንበሩን መልሰው ዘጉት። ድንበሩ ድጋሚ ቢከፈትም ድጋሚ ተዘግቷል።

በጠቡ ጊዜ በኢትዮጵያ መንግሥት እየተደገፉ የኤርትራን መንግሥት ይቃወሙ የነበሩት ኤርትራውያን የደኅንነት ሥጋት ገባቸው። ተቃዋሚዎቹ ዐቢይ አሕመድ ለእርቁ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ለፕሬዚደንት ኢሳይያስ አሳልፈው እንደማይሰጧቸው እርግጠኛ መሆን አልቻሉም። ድንጋጤ ወደ ሌላ አገር እንዲሸሹ ያደረጋቸውም ነበሩ።

በሌላ በኩል ፕሬዚደንት ኢሳይያስ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ለውጥ ሳያመጡ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም በማውረዳቸው ብቻ ጥርስ ነክሰው በማዕቀብ ሲያዳክሟቸው የነበሩ ኀያላን አገራት ማዕቀቡን አስነሱላቸው። በርካታ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ አክቲቪስቶች ኢሳይያስን ዳግም ቅቡልነት አስገኙላቸው በሚል በዐቢይ አሕመድ ቅሬታ ገባቸው።

ዐቢይ አሕመድ እርቀ ሰላሙን ያወረዱት ዓለም ዐቀፍ ውሳኔ የሆነውን የአልጀርስ ሥምምነት ለማክበር ቃል ገብተው ነው። ይሁን እንጂ ሥምምነቱን መሬት ለማውረድ እና ለማስቀጠል የሚያበቃ ምን ያህል እርምጃ እንደተሔ ግልጽ አይደለም። ብዙዎቹ ሥምምነቶች በሁለቱ መሪዎች እና በምስጢር በመያዛቸው ከጊዜያዊው ሁኔታ ባሻገር ዘለቄታውን መገመት አልተቻለም።

…አሁንም ተስፋ አለ?

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ባወረዱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በስደት ያሉ ኤርትራውያን የመብት ተሟጋቾች “ይአከል” (ይበቃል) የሚል መፈክር ያለውን ትግላቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አጧጡፈዋል። በሳተላይት ቴሌቭዥኖችም የተቃውሞ ድምፆች ተጋግለው ቀጥለዋል። አልፎ ተርፎም በኤርትራ ምርጫ ላለማካሔድ እንደ ሰበብ የተወሰደው ጦርነት አሁን ስለሌለ “ምርጫ ይደረግ” የሚል ጥሪ አቅርበዋል። የኋላ ኋላ ደግሞ የአፍሪካ ታዋቂ ሰዎች ተሰብስበው ኢሳይያስ በፖለቲካ ሰበብ አስረው ያሰነበቷቸውን ሰዎች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ጻፉላቸው። አምነስቲ ኢንተርናሽናልም የታሰሩት ይፈቱ የሚል ዘመቻ በቅርቡ ጀምሯል። ኢሳይያስ ግን ለሁሉም “ጆሮ ዳባ ልበስ” እንዳሉ ናቸው።

ይህ ተቃውሞ እና ግፊት በሁለቱ አገራት እርቀ ሰላም ማውረድ የመጣ ነው። ኢሳይያስ መንግሥታቸው ከዓለም ተቆራርጦ እና በማዕቀብ የኖረበት ዓመታት ችግር ስለማይዘነጋቸው ተመልሰው እዛ ውስጥ ለመግባት የሚፈልጉ አይመስልም። ሆኖም ሥልጣናቸው አደጋ ላይ የወደቀ ከመሰላቸው መልሰው ሰላሙን ከማደፍረስ የሚመለሱ ዓይነት ሰው አይደሉም።

ይሁንና ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ውስጥም አልጋ ባልጋ አይደሉም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቀጠናው ላይ ሰላም ለማምጣት የጣሩትን ያክል አገር ውስጥ ለማምጣት አልቻሉም በሚል በዜጎቻቸው ይታማሉ። ነገር ግን የኖቤል የሰላም ሽልማቱ የበለጠ ጠንክረው እንዲሠሩና ሥማቸውን የሚመጥን ሥራ እንዲሠሩ ጫና ያሳድርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። በጥቅሉ የኖቤል ሽልማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ለአገራቸው የምሥራች ነው። ኤርትራውያን ግን የዚህ ደስታ ተቋዳሽ አለመሆናቸው ሳይጠቀስ የማይታለፍ አሳዛኙ ገጽታ ነው።

በዚህ አምድ የቀረበው አስተያየት የጸሀፊው እንጂ የ«DW»ን አቋም አያንጸባርቅም።

በፍቃዱ ኃይሉ

5 Comments

 1. BEFEKADU HAILU,

  I greatly appreciate what you contributed to create democratic Ethiopia although we are always going back. I know the number of times you have been sent to jail and the beatings and the tortures you went through. For that, I call you a beacon of freedom and democracy.

  Having said that, I have to also mention my misgivings about you. Why do you hate Amharas? In the contributions you made to The Habesha, you clearly showed your bias towards Amharas. Quite recently, you were also heard saying that the reason you do not support the party led by Berhanu is because several members of the party are Amharas.

  I simply guess that you had an Amhara friend who betrayed you, or an Amhara cadre who tortured you or you were brainwashed by Amhara haters like Joo war and his mengas like Shimeles co. or something else. However, we Amharas are at least 40 million people with different political opinions, religions, educational level, economic status etc. Even we disagree as to whether we should organize as Amharas as most Amharas believe, especially in the old times, to do so is to go inline with TPLF and OLF. Whether you accept it or not, if you love Ethiopia, these are the people you have to like since contrary to most ethnic groups who adore article 39, Amharas are always with Ethiopia.

  I hope, next time, you will say something on this issue and rectify your bias towards Amharas, the most Egalitarian people I ever now.

  Respectfully,

   • Retarded “ujulu” aka tinb gala,

    First, do not use the name of real and innocent Ethiopians from Gambella. You are gala with little brain. The fact is that I do not hate you but I simply called you by your real name which reflects who and what you guys are: backward, savage, stinky and full of inferiority complex.

    • በፈለግሁት ስም መጠራት እችላልሁ። የነ አባስገድድ ነፍጠኛ ስርዓት ላይመለስ አክትሞአል። ዋ ተጠንቀቅ! ኡጁሉ አይምሬ ነው ይከትልሃል።

 2. Ethiopian government in early 1998 was best friends with the Eritrean government. Within a matter of few months Eritrean government became worst enemies with the Ethiopian government.
  Unless the core reason of the Ethio-Eritrean war is adressed not one but hundreds of peace prizes do not bring lasting peace between the two countries. Both sides need to figure out what it was that turned the best of friends relationship they had into the worst of enemies that quick , then both countries leaders must instill in themselves and in their whole countries people to do a conscious effort the reason that brought the Ethio Eritean war doesn’t happen again.

  Sugar-coating the real reason of why the Ethio-Eritrean war started by saying the reason was the two cousins family feud (Meles Zenawi and Isayas Afeworki) personal feud war or border war over Badme, is not the way peace is achieved.

  The real truth of why the war started need to be addressed.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.