ተው ለውሻ አትሩጥ! – በላይነህ አባተ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

አብሮኝ የኖረ ነው ብልህ እየተረትክ፣
ያበደውን ውሻ ተለማዳ ቆጥረህ፣
እየተንዘላዘልህ መኖሩን ታላቆምህ፣
ተነክሰህ ተነክሰህ ጉምድ ትሆናለህ፡፡

 

ውሀ ሙላት ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፣
ውሻም የሚነክስህ በምላስ ልሶ ነው፡፡

 

ውሻን ሳታስከትብ አብሮ እንዲኖር ታረክ፣
ተላይ ተራስጌህ ታቅፈሀው ታደርክ፣
በሬቢስ በሽታ አብደህ ትሞታለህ፡፡

 

መፈርጠጥ ታበዛህ ውሻ ሲያባርርህ፣
ልብህ ይነከሳል እንኳን ሊተርፍ እግርህ፡፡

 

እንደ ሰው ለመኖር በጤና በክብር፣
የውሻን አመሎች ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

 

በመጣብህ ቁጥር እግሬ አውጪኝ ታበዛህ፣
በእንፉቅቅ መሄድ ነው ታፋን ተዘንጥለህ፡፡

 

ተቆሎ ተማሪ ጥበብ ዘዴ ተማር፣
ውሻ ሲመጣብህ ኮራ ቀብረር በል፡፡

 

ሊበላህ ሲመጣ አብዶ ሰክሮ ውሻው፣
በመፈርጠጥ ፋንታ ፊትለፊት ግጠመው፡፡

 

ቅንዝንዝን ውሻ ዘወር በል ስትለው፣
ጅራቱን ወትፎ እሚፈተለክ ነው፡፡

 

ትዕግስትን ፍርሃት አርጎ ስለሚያየው፣
በሸሸኸው ቁጥር ውሻ አባራሪ ነው፡፡

 

ስለዚህ ወገን ሆይ ለውሻው አትሩጥ፣
እግሩን ሰቅሎ እንዲሄድ ፊትለፊት ተጋፈጥ፡፡

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

3 Responses to ተው ለውሻ አትሩጥ! – በላይነህ አባተ

 1. ግሩም መልዕክት ነው እናመሰግናለን

  Avatar for ግርማ ቢረጋ

  ግርማ ቢረጋ
  October 13, 2019 at 2:17 am
  Reply

 2. Serenity Now!!

  There are two kind of problems in these world.

  1. Problems that can be corrected/fixed.

  2.Problems that cannot be corrected/fixed.

  Look at it this way when people get into a cat accident they see the damage and decide whether to get the car fixed/corrected or they decide to call it totalled and cut their losses then search for another car.

  Having a wisdom to know the difference between the above two kind of problems, is what our country is not yet capable of, for example the current con institution of Ethiopia drafted by con artists Meles Zenawi & Co. need to be changed not corrected. The current con institution got too many flaws it is beyond repair, it is better to draft a new real constitution rather than trying to correct Meles Zenawi & Co.’s con institution.

  Avatar for Tadiyos

  Tadiyos
  October 14, 2019 at 5:39 am
  Reply

 3. ሰዎች፤ ይህ ርዕስ ስድብ ኣይደል?, ምን ዓይነት ኣባባል ነው?

  Avatar for Mulugeta Andargie

  Mulugeta Andargie
  October 15, 2019 at 8:12 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.