አማራው በአንድነቱና በህብረቱ ህልውናውንና የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስከብራል

1 min read

ከዓለም አቀፍ የአማራ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ

የዓማራው ታሪክ የሚአስረዳው ሐቅ ቢኖር አማራ አገሩንና ወገኑን የሚወድ፤ በሀገሩ ሉአላዊነት የማይደራደር፤ ወራሪ ጠላት ሲመጣ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ገንፍሎ በመውጣትና ከሌላው ወገኑ ጋር ደሙን በማፍሰስ አጥንቱን በመከስከስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስከብር ለሃገሩ ቀናኢ የሆነ፤  በአገሩና በባንዲራው ድርድርን የማያውቅ ህዝብ ለመሆኑ ቀደምት ታሪኩ ይመሰክራል።

ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ በውሸት ትርክት ዓማራውን መዝለፍ፤ ማፈናቀል፤ ማሳደድ፤ መግደልና ብሎም ይህን ማህበረሰብ ቢቻል ከምድረ ገጽ ማጥፋት ባይቻል ከሁሉም አናሳ ሆኖና አንገቱን ደፍቶ እንዲኖርና እንዲገዛ የሚፈልጉ ጽንፈኞችና የዘር ፖለቲካ አራማጆች እያዋከቡት ይገኛል። የፊደል ድልድይ ቀርጾ ሁሉን ብሄረሰብ የሚአገናኝ የመግባቢያ ቋንቋ ፈጥሮ ያስተማረ፤ በሬ ጠምዶ ማረስና መመገብ ያሳየ፤ አገርን አንድ ያደረገ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ያስተማረና የሰበከ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ሕገ መንግስት ቀርጾ የፍትሕ ስርዓትን ያስጀመረ ሕዝብ መመስገን እንጂ መሳደድ አይኖርበትም።

ዓለም በሥልጣኔ፤ በብልጽግና፤ በሰላምና በአንድነት ተያይዞ ወደፊት በሚጓዝበት የሃያአንደኛው ክፍለ ዘመን በጎሳ ልዩነት የራስን ሕዝብ ለመለያየትና አገር ለመበትን ሌት ከቀን ሲሰራ ማየት እጅግ ያሳዝናል። በውጭ ጠላቶች ተደግፈው፤ ለስልጣን ሽሚያ የሰከሩ ጽንፈኞች አዲሱን ትውልድ በሌለ ታሪክ ሕሊናውን በጥላቻ መርዝ እየበረዙ ወጣቱን እርስ በእርስ በማጋጨት የኢትዮጵያን ሰላምና የዓማራን ሕዝብ ደህንነት የሚተናኮሱ ጽንፈኞች እኩይ ተግባራቸዉን እንዲያቆሙ መደረግ ይኖርበታል። ሕዝቦች አንድ ሲሆኑ ዓማራ ሲከበርና ሰላም ሲሆን ነው ሃገራችን የሰላም አየር የምትተነፍሰው፤ እድገትና ብልጽግናም እውን የሚሆነው። አገር ገንቢውን፤ ለሃገር ነፃነት የተዋደቀውን ዓማራ እያሳደዱ ሰላምና ብልጽግናን ማምጣት ዘበት ነው።

ስለሆነም ስላምና ፍቅር የተጠማወን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘወትር ሲመኘው የኖረውን ዲሞክራሲ፤ ብልጽግና፤ አንድነትና እኩልነት ተጎናጽፎ እንዲኖር ለማድረግ፤ ለአሃገር ሰላምና እድገት ሲባል መንግስት የሚከተሉትን ጉዳዮች ተግባራዊ እንዲአደርግ እንጠይቃለን።

1ኛ/ አማራው በአራቱም አህጉር አማራ በመሆኑ ብቻ እየተገደለና እየተፈናቀለ ተወልዶ ካደገበት፣ እትብቱ ከተቀበረበት መሬት እንዳይኖር እየታረደና እየተሳደደ ስለሆነ ይህ እንዳይሆን መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ። ሕዝብን እያጋጩ የኢትዮጵያን ሰላምና የዓማራን ሕዝብ ደህንነት በሚተናኮሱ ጽንፈኞች ላይ መንግስት ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድ።

2ኛ/ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ፤ አማራንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሕልውናን ለማክሰም ከውጭ ጠላቶች ጋር ተማምሎ ለ27 ዓመት ሲዘርፍና ሲገድል፤ የግል ጥቅሙንም ሲያሳድድ የመሸበት የትግራይ ነፃ አውጭ ጎጠኛ ቡድን መቀሌ ላይ መሽጎ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረፈው ሃብትና ንብረት እየደለለ ፀረ አማራ ሃይሎችን ከባድ መሣሪያ እያስታጠቀ በአማራው ላይ ያጥፍተህ ጥፋ ቀጥተኛ ጦርነት  ዘመቻ ጀምሯል። የዚህ ማስረጃ በክልሉ ልዩ ሃይል፤ የፖሊስ ሃላፊዎች፤ የሰላም ጠባቂዎችና ሕዝብ እጅ ሰለሚገኝ የፌዴራል መንግሥት የማያወላውል ሕጋዊ እርምጃ ወሰዶ ነገሩ ተባብሶ አደገኛ ጥፋት ሳይደረስ በፊት ባስቸኳይ እንዲአስቆመው እንጠይቃለን።

3ኛ/ በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ አማሮች ልጆቻቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በአማርኛ እንዳይማሩ እየተደረገ ነው። ልጆችና ወጣቶች ሌላ ቋንቋ እንዲያውቁ መደረጉን ባንቃውምም፤ ነገር ግን ዓማርኛ  በሕገመንግስቱ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ እንዲሰራበት የጸደቀ ሆኖ ሳለ ያማራ ልጆች በራሳቸው ቋንቋ እንዳይማሩ መደረጉ ታላቅ ግፍና በደል ስለሆነ ትምህርታቸውን በአማርኛ ቋንቋ እንዲማሩ እንዲደረግ አጥብቀን እየጠየቅን በዚህም ምክንያት የተዘጉ ተምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ እናሳስባለን።

4ኛ/ አንዳንድ የክልል ባለሥልጣኖች በሕዝብ በዓላት፣ በመንግሥትና በማህበራዊ የዜና ማሰራጫዎች ያልወከላቸውን ህዝብ እንደወከላቸው አድርገው በመጠቀም የነበረውን እንዳልነበረ በማድረግ፣ ታሪክ በማዛባት በዓማራው ህዝብ ላይ የጥላቻ ዘመቻቸውን፣  በማስፋፋት ህዝብ ለህዝብ ማጋጨትን እንዲያቆሙ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ የገባዋል፡፡ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የሚቀርብ ይህ ዓይነት የጥላቻ ንግግር ሰላምንና መረጋጋትን፤ ብልጽግናን እና እድገትን አያመጣም። ስለሆነም መንግስት እነዚህን የክልል፤ የፌድራልና የከተማ አስተዳድር ባለስልጣናት ክዚህ እኩይ ተግባርና ፕሮፖጋንዳቸው እንዲታቀቡ እንዲአድርግ በድጋሜ እንጠይቃለን።

5ኛ/ በሰኔ 15 በተፈጠረው ክስተት ምክንያት ያለምንም ማስረጃ የታሰሩት የአዓማራ ክልል የጦር መኮንኖች፣ የሲቪል የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ባስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ለተገደሉት የክልሉ መሪዎች ምርመራው  በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ውጤቱ በአስቸኳይ ለህዝብ እንዲቀርብ፤

6ኛ/ የአማራውን አንድነት የሚፈሩና የሚያርበደብዳቸው በልዩ ልዩ ዘዴም በመካከል እየገቡ እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚሰሩ ስላሉ መላው አማራ ይኽን ነቅቶ እየጠበቀ ሰለሆነና ትርፉ ኪሣራ በመሆኑ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ መንግስት የበኩሉን እንዲአደርግ እንጠይቃለን፤

7ኛ/ ሕግ ከመነደፉ በፊት ከአማራው ከልል ላይ በጉልበት ተነጥቆ የተወሰዱትን መሬቶች አስመልክቶ ከጎንደር የወልቃይትና ጠገዴን ከወሎ  የራያ መሬት ከጎጃም ቤኒሻንጉል መተከልን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዓማራው እንዲመለሱለት እንጠይቃለን።

8ኛ/ በሰሜን ሸዋ በአማራው ላይ የሚደረጉተን ህገ ወጥ ተግባሮችና በግፍ ከመሬታቸዉ  ለሚፈናቀሉት ሁሉ መንገሰት ባስቸኳይ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲቀርቡ  ይኖርበታል።

9ኛ/  የአዱስ አበባ አስተዳደርን በተመለከተ፣ 70 በመቶው ያማራ ህዝብ በሚኖርበት አዲስ አበባ ከተማ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት መብቱ እንዲጠበቅ፣ እና ከሰላም ጠባቂ ፖሊስ አልፎ ለጦርነት የሠለጠነ በሚመስል ልዩ ሓይል የተፈጠረ ስለሆነ በአስችኳይ እንዲታገድ፡፡

10ኛ/ በድሬዳዋና በሀረር 40/40/20 እና 49/50-አስከፊና-ዘረኛ-አስተዳደራዊ-መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡

ለእውነተኛ ለውጥ በመከባበር  በመተሳሰብና  እንዲሁም በእዉቀት ላይ የተመሰረተ አንድነት ወሳኝ ነው፡፡

ከዚህ በላይ በአጭሩ በዘረዘርናቸው ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግስት ሚዛናዊ የሆነ አመለካክታቸውንና የመሪነት ግዴታቸውን በመወጣት አማራው ላይ የሚደርስበትን ዘርፈ ብዙ በደሎች ባስቸኳይ እንዲአስቆሙ እናሳስባለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

ዓለም አቀፍ የአማራ ሕብረት

ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም

 

 

 

4 Comments

 1. አማራው ኢትዮጵያ የግል ንብረትህ አይደለችም፡፡ የብዙ ብሔረሰቦች ሐገር ናት ፡፡ አትዮጵያን ሠራናት ብለህ እንደምትፎክር ሁሉ በዚህ ዘመን ለመፍረሷ ምከንያት አንተው ትሆናለህ፡፡

  ዛሬ ትላንት አይደለም ፡፡ ትላንት አንተ ብቻ ይዘኸው የነበረ ና ያስገበርክበት ነፍጥ ዛሬ ሁሉም ጋ አለ ፡፡ ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ ፡፡ በዚህች ሐገር የእረስ በርስ ጦርነት ቢነሳ ምክንያቱ አንተ ና አንተ ብቻ ነህ ፡፡ በእብሪት ከሁሉም ጋር ተናክሰህ በየሐገሩ ተበትነህ አየኖርክ የምትለኩሰው እሳት ከሁሉ በላይ የሚለበልበው አንተኑ ነው፡፡

  ከእስከዛሬ የመጣህበትን ቆሞ ማሰቢያህ አሁን ነው ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ዘረኝነት ምንጩም መሰረቱም አንተ በሌሎች ጣትህን በሌሎች ላይ እንደምትቀስረው ሳይሆን አንተውና አንተው ብቻ መሆንህን ማመን አለብህ፡፡

  ፉከራ ያጠፋህ እንደሆነ የትም አያደርስህም ፡፡ ትላንት ስትንቃቸው ፤ ስታዋርዳቸው ስትገድላቸው የነበሩ ህዝቦች ዛሬም እንደምታስበው እንደትላንቱ በኢትዮጵያዊነት ስም ጭቆናን የሚቀበል ይቅርና ትንኮሳህ አስነስቶት ቂም አገርሽቶ ለከፋ ችግር ልትዳረግ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ እንኳን ለኢትዮጵያ አንድነት ብቸኛው ጠበቃ እኔ ነኝ ብለህ መፎከር ይቅርና በክልልህ በሠላም ለመኖርህ ዋስትና የለህም፡፡

  ስለዚህ ዛሬም በድሮ እብሪት ና ትዕቢት ሐገር ለማመስ ከመጣር አቅምህን መዝነህ ከሌላው ህዝብ ጋር እርቅ አውርድህ በሰላም ና በእኩልነት ለመኖር ልቦና ይስጥህ

 2. አማራው ኢትዮጵያ የግል ንብረትህ አይደለችም፡፡ የብዙ ብሔረሰቦች ሐገር ናት ፡፡ አትዮጵያን ሠራናት ብለህ እንደምትፎክር ሁሉ በዚህ ዘመን ለመፍረሷ ምከንያት አንተው ትሆናለህ፡፡

  ዛሬ ትላንት አይደለም ፡፡ ትላንት አንተ ብቻ ይዘኸው የነበረ ና ያስገበርክበት ነፍጥ ዛሬ ሁሉም ጋ አለ ፡፡ ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ ፡፡ በዚህች ሐገር የእረስ በርስ ጦርነት ቢነሳ ምክንያቱ አንተ ና አንተ ብቻ ነህ ፡፡ በእብሪት ከሁሉም ጋር ተናክሰህ በየሐገሩ ተበትነህ አየኖርክ የምትለኩሰው እሳት ከሁሉ በላይ የሚለበልበው አንተኑ ነው፡፡

  ከእስከዛሬ የመጣህበትን ቆሞ ማሰቢያህ አሁን ነው ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ዘረኝነት ምንጩም መሰረቱም አንተ በሌሎች ጣትህን በሌሎች ላይ እንደምትቀስረው ሳይሆን አንተውና አንተው ብቻ መሆንህን ማመን አለብህ፡፡

  ፉከራ ያጠፋህ እንደሆነ የትም አያደርስህም ፡፡ ትላንት ስትንቃቸው ፤ ስታዋርዳቸው ስትገድላቸው የነበሩ ህዝቦች ዛሬም እንደምታስበው እንደትላንቱ በኢትዮጵያዊነት ስም ጭቆናን የሚቀበል ይቅርና ትንኮሳህ አስነስቶት ቂም አገርሽቶ ለከፋ ችግር ልትዳረግ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ እንኳን ለኢትዮጵያ አንድነት ብቸኛው ጠበቃ እኔ ነኝ ብለህ መፎከር ይቅርና በክልልህ በሠላም ለመኖርህ ዋስትና የለህም፡፡

  ስለዚህ ዛሬም በድሮ እብሪት ና ትዕቢት ሐገር ለማመስ ከመጣር አቅምህን መዝነህ ከሌላው ህዝብ ጋር እርቅ አውርድህ በሰላም ና በእኩልነት ለመኖር ልቦና ይስጥህ

  • የምታወራው ስለግለሰቦች ከሆነ ይቻላል፡፡ ነገርግን የምትለው ስለአማራው አጠቃላይ ከሆነ እብደት ነው፡፡ አማራው እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ለአገሩ ተዋድቋል፤ ጭቆና ደርሶበታል፡፡ ይህ እብሪትና ንቀት የተሞላበት አስተሳሰብህ የራስህ ብቻ ነው፡፡ አማራው እንደኢትዮጵያዊ እንጂ እንደብሄር ኖሮም አያውቅ፡፡ በየአገሩ የተበተነው አገሩ ስለሆነ ነው፡፡ ያልተበተነ ስለመኖሩ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ፡፡ ከሶማሌ ክልል ብቻ ከ1ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ ሲወጣ ለካ ሶማሌ ክልል ላይ 30 ከመቶ ኦሮሞ ነበር እንዴ ብላናል፡፡ የህቺ አገር በማስፈራራት ሳይሆን በእኩል የምኖርባት መሆን አለባት ካልክ እንዲህ ከልክ ያለፈ ማስፈራራትህን አንተና መሰሎችህ ማለትም ወያኔና ኦነጎች ብቻ ናችሁ፡፡ በዚህች አገር ሁሉም ነሁሉም ስፍራ መኖር፣ ንብረት ማፍራትየዜጋ ሁሉ መብቱ ነው፡፡
   እንግዲህ ምን ትሆን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.