እነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በዋስ ተለቀቁ

1 min read

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2012 ዓ/ም (አብመድ) ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ ዐባይ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተለቀቁ፡፡

በሰኔ 15 ጥቃት ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ በእስር የቆዩት ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው ሐሙስ ዋስትና ጠይቀው ነበር፤ መዝገቡን ተመልከቶ ውሳኔ ለመስጠትም ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር፡፡

በዋስትናው ዙሪያ መዝቡን ተመልክቶ አስተያዬት ለመስጠትም ለዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በቀጠሮው መሠረትም ዐቃቤ ሕግ አስተያዬት ሰጥቷል፡፡

ከምርመራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የተጣሩ መሆናቸውንና ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለው ጭብጥ ዋስትና የሚያስከለክል አለመሆኑን ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ መግለጹን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክልል ዐቃቤ ሕግ ኢዮብ ጌታቸው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲወጡ አዝዟል፡፡

በዚህ መሠረትም ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና አቅርበው ከሰዓት በኋላ መውጣታቸውን አቶ ኢዮብ ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.