እስክንድር ነጋ ማነው?

1 min read

ሩትጋር ዩንቨርሲቲ ከሚሰራው አባቱና የአሜሪካን ዩንቨርሲቲ ኦፍ ቤሩት አስተማሪ ከሆነችው እናቱ በ1960 ዓ.ም ተወለደ።

በሳንፎርድ ት/ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ጨርሶ ዋሽንግተን በሚገኘው አሜሪካን ዩንቨርሲቲ ተቀላቀለ ። እዛም ፖለቲካል ሳይንስና ኢኮኖሚክስ ተምሯል ።

ዘወትር ሰለአገሩ ማሰብ የማይታክተው እስክንድር ከደርግ ውድቀት በኋላ ለጉብኝት ወደ አገር ቤት የመጣው እስክንድር መንግስት የሰጠውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ተመርኩዞ የመጀመሪያ ጋዜጣውን ኢትዮጲስን በ1985 ዓ.ም ማሳተም ጀመረ ። ነገር ግን ቃሉን የበላው መንግስት ጋዜጣውን አገደው ።

የሰርካለም አሳታሚ ዋና ስራአስኪያጅ በመሆን አስኳል ፣ ሳተናው ፣ምኒሊክ የተባሉ ጋዜጦች ያሳትም የነበረ ቢሆንም ሁሉም በመንግስት ታግደዋል ።

እስክንድር ለሰብዓዊ መብት መከበር ባደረገው ትግል ዘጠኝ ጊዜ ለእስር ተዳርጓል ። የ1997 ዓ.ም ምርጫ ውጤትን ተከትሎ ብዙ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ሲታሰሩ ከነዛ ውስጥ እሱና ባለቤቱ ሰርካለም ይገኙበታል ።

ሰርካለም ነፍሰጡር የነበረች ሲሆን በማረሚያ ቤት በደረሰባት ስቃይ ምጥ ያለቀኑ ቢመጣባትም ሰብዓዊነት የሚጎድላቸው የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎችና ባለስልጣናት ምንም ሊረዷት ስላልቻሉ ያለጊዜው ለመገላገል በቅታለች ።

ጨቅላውንም ማሞቂያ ክፍል ማስገባት ሲገባቸው አንድ ክፍል ውስጥ ደረቅ አልጋ ላይ በመተው እንዲሞት የተውት ቢሆንም ያ ሳይሆን ቀረ ። ከዚህም የበለጠ መከራና ስቃይ እንኳ እየደረሰበት እስክንድር ከአላማውም ውልፍት አላለም ።
ከሁለት ዓመት እስር በኋላ የተፈታ ቢሆንም የጋዜጠኝነት ፍቃዱ ተሰርዞ ጋዜጣውም በመታገዱ በኢንተርኔት መጻፉን ቀጠለ ።

ሆኖም የወጣውን የጸረ ሽብር ሕግ በመቃወሙና የታሰሩ የመብት ተሟጋቾች እንዲፈቱ በመቀስቀሱ በሽብርና አገርን በመሰለል ወንጀል ተከሶ የግንቦት 7 አባል ነህ በሚል የ18 ዓመት እስር ስለተፈረደበት ወደ ወህኒ ተላከ ።

የግንቦት 7 አባል እንደሆነ እንዲፈርምና እንዲፈታ የተጠየቀ ቢሆንም በውሸት ላለመስማማት በአቋሙ ጸንቷል ።

ከሰባት ዓመት እስር በኋላም የዐቢይ መንግስት መምጣቱን ተከትሎ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች በመፈታታቸው ከእስር ሊወጣ ችሏል ።

እስክንድር የእድሜውን እኩሌታ ለታገለለት ሰበዓዊ መብት እና/ወይም የመናገር ነፃነት ዓለምአቀፍ ሽልማቶችን ፣ እውቅናና ክብር አግኝቷል ።

ከእነዚህም :-
1. 2004ዓ.ም (2012) PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
2. 2006ዓ.ም (2014 ) World Association of Newspapers’ Golden Pen of Freedom Award
3. 2009ዓ.ም (2017) International Press Institute World Press Freedom Hero
4. 2010 (2018) Oxfam Novib/PEN Award
እስክንድር ብሔርን፣ ቋንቋን፣ ዘርን መሰረት ሳያደርግ ለሰበዓዊነት የሚታገል ያሰበውም ሳይሳካ እርምጃውን የማይገታ እንደሆነ ይናገራል ። “ሁላችንም ተጓዦች ነን ፤ ፍጥነታችን ቢለያይም መድረሻችን አንድ ነው – ነፃ ዲሞክራሲ” ብሏል ።

አሁን ላይ ደግሞ ለአዲስ አበባ ነዋሪ መብት መከበር የቆመ ባልደራስ የተሰኘ ባለአደራ ምክርቤት በማቋቋም እየሰራ ይገኛል ።

ይህ የሲቪክ ማኅበር የነዋሪውን የራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ‘የኔ ነው’ ከሚሉት ሌሎች ብሔሮች ተጽዕኖ እንዲላቀቅ ፣ ከመዋጥም እንዲተርፍ ብሎም የአገሪቱ ፖለቲካዊ ማዕከል በመሆኗ በከተማዋ ላይ የሚተላለፍ ማንኛውም ውሳኔ የአሪቱን ዕጣ ፋንታ የሚቀይር በመሆኑ ፍትሐዊ አሰራር እንዲሰፍን ይሰራል ።

ከዚህ በተጨማሪ በጋዜጦች ጀምሮት የነበረውን ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት አጠናክሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሯል ።
ዋቢዎች :-
1. https://en.m.wikipedia.org/wiki/

9 Comments

 1. እስክንድር ነጋ ማነው?

  እስክንድር ነጋ በማንኛዉም ሁኔታና መንግስት ስር በሰላም መኖር የማይችል ተራ ሽብርተኛ ነዉ። እርሱ ሰላም የሚያገኘዉና ለሰዉ ሰላም የሚሰጠዉ ማዕከላዊ ወስደዉት እንደ ወያኔ ቂጥ ቂጡን ሲሉት ነዉ። ወይ ደግሞ መንግስቱ ኃይለ ማርያም እንዳለዉ አፍንጫዉን ሲሉት ነው።

  • እስክንድር ከበሬታ ያገኘው የምን ጎሳ ወይም ከማን በመወልዱ ሳይሆን ባነገበው እውነት ነው ።እሱን በግል ማጥቃት የያዘውን ህቅ የበለጠ ያለመልመዋል እንጂ ኣያዳፍነውም ።ከመጻፋችን በፊት ትንሽ ራስን ለህሊና ማስገዛት ይገባል የእንጀራ ጉዳይም ቢሆን ።

  • አንድ ተራ ጉድጓድ የማሰች የመቀሌ አይጥ ስለ እስክንድር ነጋ ምንም ብትል ምንም የሚሰማት አይኖርም ፡፡

 2. እስክንድር ነጋ ከማንኛውም ሁኔታና መንግሥት ስር በሰላም መኖር የማይችለው ፦
  1 እስክንድር የዲሞክራሲና የፍትህ ታጋይ በመሆኑ ዲሞክራሲ አልቦ በሆነ በማንኛውም ሁኔታና መንግሥት ሰላም ስለለሌ ነው ።
  2 እሱ ሰላም የሚያገኘውና ለሰላም ነሺዎችና ለአሸባሪዎች ሰላምን የሚሰጠው ተረኚነት ሲቆምና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሲመሰረት ቢቻ ነው ።
  3 እስክንድር ነጋ ማእከላዊም ሆነ ሌላው እስርቤት ብሎም የዘረኞች ቶርቼር የማይበግረው የነጻነት አርበኛ በመሆኑ መፍትሄው ዲሞክራሲን ማስፈን ፣ ተርኚነትን ማቆምና ሁሉም ኬኛን መተው ነው ። ሀገራቺን ለሁላችንም ትበቃናለች ።

 3. እስክንድር ነጋ እንደ ቭርሃኑ ነጋ ቦንገር የሚያጭበረበር የመርካቶ ጉራጌ ነው። ጉራጌዎች ባሁኑ ጊዜ እየተሞላቀቁ ነው። እኛ ስንጽፍ እንከለከላለን። ስልጤዎችም

  • Stone head mulugeta,

   Either do not write at all or do not write to assassinate the characters of people. This world would have been nicer without people like you since you are born only to gossip.

 4. This man is not an Ethiopian.He is biased,stubborn,snobish and arrogant who wants to create clash among Oromo and Amara.What is “Baladera”? Is it NGO,Political party or private company? As to me he is private company runner wants to profit from peoples massacre.He is not an activist,but terrorist who is buying armaments,and bullets to enjoy death of the people in Addis Ababa.Please,stop what you are doing in hidden way.You will be sad with the consequences of you wrong doing on innocent people.

 5. አንዳንድ ሰዎች እስክንድርን ለመተቸት ሲሞክሩ ይገርሙኛል። ለተበደሉ፣ ፍትህን ለተጠሙ ሁሉ ድምፅ ሆኖ ዕድሜውን የሚያሳልፍን የነፃነት ታጋይ እንዴት በክፉ ማንሳት ይቻላል። ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የእስክንድርን ለመንቀፍ ሞራል አይኖረውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.