በአፋር 17 ሰዎች መገደላቸውን የአፋምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ

1 min read

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳይታ ዱብቲ አካባቢ የውጭ አገር መታወቂያና ተሽከርካሪ ይዘዋል የተባሉ ታጣቂዎች ከትላንት በስቲያ ሰነዘሩት በተባለው ጥቃት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

የአፋምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን አሊ 17 ሰዎች መሞታቸውንና 34 ሰዎች መቁሰላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድን ጠቅሰው ሦስት ህፃናት እና አራት ሴቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 16 ሰዎች መገደላቸውን ዘግበዋል።

ሕፃናትን ጨምሮ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ዜጎች በተለያዩ ሆስፒታሎች በሕክምና ላይ እንደሚገኙም የወረዳው ኃላፊ ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.