/

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ናት – ፕ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ

1 min read

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ ካስተላለፉት መልእክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

* ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰንድቅ ዓላማ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ናት፤

* ዛሬ የምናከብረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን አንድምታው ሰፊ ነው፤

* ሰንደቅ ዓላማ የትላንቱን ታሪክ፣ የዛሬውን እውነት፣ የነገውን ራዕይ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

* በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖረንም እንኳን ሰንደቅ ዓላማችን የብሔራዊ አንድነት ምልክት ነው፤

* ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ ማንነት መገለጫ ነው ስንል፦ ሀገርን ይወክላል፤ በየትኛው ቦታ ላይ ሰንደቅ ዓማችን ሲውለበለብ ሀገራችንን እና የሀገራችንን ጥቅም የሚያስከበር ተቋም አለ ማለት ነው፤ ከሌሎች ሀገሮች ጋር እኩል መሆናችንን ያሳያል፤

*ሰንደቃላማችን የሉአላዊነታችን መገለጫ ነው

*ሰንደቅ ዓላማ ሀገራችን የተመሠረተችባቸውን እርስ በርስም ሆነ ከሌሎች ጋር የሚያገናኙንን እሴቶች ሁሉ የሚያሳይ ነው፤

* እኔ ባደግኩባት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀልም ሆነ ሲወርድ ዜጎች ቆመው የሚያከብሩት ነበር፤ የዛሬው ቀን ለሰንደቅ ዓላማችንን ክብር መመለስ የሚችል መሆን አለበት፤

* ለልጆቻችን የሰንደቅ ዓላማን ክብር እናስተምር
* ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን መገለጫ እንጂ በፖለቲካ ምክንያት የልዩነታችን መገለጫ መሆን የለበትም

* ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ሲውለበለብ ከክልል አርማዎች ሁሉ ከፍ ብሎ የሚታይ መሆን አለበት

* አትሌቶቻችን ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገው በማሳየት ነው ክብራችንን የሚገልጹት

*ሀገራችን ኢትዮጵያ ጀግኖችን ትፈልጋለች፣ ግጭትን የሚደግሱ ሳይሆኑ የሰላምን ውድነት የሚሰብኩ፣ ልዩነትን ሳይሆን አንድነትን የሚሰብኩ፣ ሀገሬን የሚሉ ዜጎችን ትፈልጋለች

* እልፍ አዕላፍ የተሰዉላትን ሰንደቅ ዓላማ እኛ ዛሬ አንድ ሆነን ብዙ ተዓምሮችን እንሥራላት

* የክብራችን መገለጫ የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ለዘለዓለም ከፍ ብሎ ይውለብለብ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.