የረሃብ አድማ ላይ ያሉት የህሊና እስረኞች ጤናቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

1 min read

ላለፉት 4ቀናት በርኃብ አድማ ላይ የሚገኙት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትና አመራሮች ለከፍተኛ የጤና ችግር ተጋልጠዋል።
***
ከሰኔ 15ቱ የአማራ ሕዝብ መሪዎችና የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ግድያ ጋር በተያያዘ ላለፉት 4 ወራት በአዲስ ፓሊስ ኮሚሽን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙት የአብን የሕዝብ ግንኙነትና የፅህፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ የአብን አባላትና አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች እስረኞች ፍትሕ አላገኘንም በሚል ከመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት 4 ቀናት የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ከርኃብ አድማው ጋር ተያይዞ የንቅናቄያችን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ተደለን ጨምሮ ለከፍተኛ የጤና ችግር ተጋልጠዋል።

ድርጅታችን ጉዳዩን በከፍተኛ ሁኔታ እየተከታተለው ሲሆን የንቅናቄያችን ደጋፊዎች፣ አባላት፣ መላው የአማራ ሕዝብና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግፍ ከታሰሩት ጎን እንድትቆሙ እየጠየቅን በቀጣይ አብን ለሚያደርገው ጥሪ ዝግጁ ሁናችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

ምንጭ፦ ፍኖተ አብን

1 Comment

  1. የአማራ የረሃብ አድማ ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ንጋቱ ሁለት ሰዓት ብቻ ስለሆነ ዝም ብላችሁ ጠብቋቸዉ። ጊዜዉ ሲደርስ ራሳቸዉ ይፈቱታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.