በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

1 min read

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው “መደመር” መፅሃፍ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል።

የመፅሃፉ ምረቃም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች በአንድ ቀን የሚከናወንም ይሆናል።

በዋናነትም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች ይመረቃል።

በምረቃ ስነ ስርዓቶቹ ላይም የየከተሞቹ ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሴቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በየአካባቢው ባህል መሰረት የምረቃ ስነ ስርዓት የሚከናወን ሲሆን፥ ስለ መፅሃፉ አጠቃላይ መረጃም የሚሰጥ ይሆናል።

ይህ መፅሃፍ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን፥ 1 ሚሊየን ቅጂዎችም ታትመዋል።

የመፅሃፉ ዋጋ 300 ብር ሲሆን፥ ገቢውም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ይውላል ነው የተባለው።

ከሀገር ውስጥ ምረቃ በኋላም በውጭ ሀገራት በአሜሪካ እና ኬንያ በተለይም በዋኝንግተን ዲሲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ እና ናይሮቢ የምረቃ ስነ ስርዓቱ የሚከናወን ይሆናል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ፥ መፅሃፉ በመደመር እሳቤ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በአማርኛ፣ ኦሮሚኛ እና ኢንግሊዘኛ ቋንቋዎች ነው የተፃፈው።

የኢንግሊዘኛው ቅጂ ግን ከሶስት ወራት በኋላ እንደሚደርስ አስታውቀዋል።

በአልአዛር ታደለ/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.