400 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

1 min read

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 5/2012ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 3 ወራት ውስጥ 32 ሺህ 890 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር በዳረገው ስምምነት መሠረት ነው በእስር ላይ የነበሩ 400 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ቀይ ባህርን አቋርጠዉ ሲጓዙ በሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታ ሀይል ተይዘው በእስር ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።

የዛሬዎቹን ተመላሾች ጨምሮ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ 32 ሺህ 890 ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.