በዛሬው ዕለት ጥቅምት 5/2012 በራያ ሕወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሯል

1 min read

ህብር ረዲኦ እንደዘገበው በዛሬው ዕለት ጥቅምት 5/2012 በራያ ሕወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሯል።ጥይት፣የወታደር ዩኒፎርም፣ቃሬዛ እና አካፋ ለታጣቂዎች እያከፋፈለ ነው።
የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ደጀኔ አሰፋ የሕወሓትን የጦርነት ዝግጅት የፌደራል መንግሥት እና አዴፓ ሊያውቁት ይገባል ሲል መረጃውን ይፋ አድርጉዋል።

 ሰሞኑን ለአንድ ሳምንት ስብሰባ ላይ የቆየው ሕወሓት ትላንት ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግን ውህደት ተቃውሞ፣ሕዝቡ ለመራራ ትግል ይዘጋጅ ሲል ጥሪ ማድረጉ አይዘነጋም። ተከታዩን ጥሪ ያንብቡት ሼር ያድርጉት

ጥብቅ መልዕክት ለፌደራል መንግስት እና ለአዴፓ
————
ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን በዚህ ሰዓት ለራያ ሚሊሻዎች ስምንት ስምንት ካርታ ጥይት (240 ጥይቶች) ፣ የሚሊተሪ መለዮ ፣ አስከሬን እና ቁስለኛ ማንሻ ቃሬዛ ፣ አካፋ ፣ ዶማ ወዘተ በአላማጣ አስተዳደር ፅ/ቤት ፊት ለፊት እየሰጧቸው ይገኛል። የፌደራሉ መንግስት እና አዴፓ ለእንደዚህ አይነት የትንኮሳ እንቅሰቃሴዎች በቂ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። የራያ ሚሊሻ መሳሪያህን እና ጥይትህን አጥብቀህ ያዝ። ምክራችን እውን የሚሆንበት ጊዜ ቅርብ ነው!!

 

2 Comments

  1. አንዳንድ ወገኖቼ የኢትዮጵያ የፌደራል ሲስተም በራሱ መጥፎ ኣይደለም። የጎደለው ዴሞክራሲ ነው ይላሉ።
    በርግጥ ግን የብሄር ፌደራል ስርዓትን ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ኣይቻልም። ህጸጾቹ ብዙ ናቸው። ግጭትና መፈናቀል ኣምራች ነው በራሱ። እነዚህ የብሄር ፌደራል ስርዓት ጠበቃዎች የአሁኑን ጊዜ ማየት ይበቃቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ትንሽ ለቀቅ ያለ ነውገር ይታያል። ነገር ግን ይህ ለቀቅ ያለ ነገር ሲመጣ በስርዓቱ ውስጥ የታመቀው ግጭትና መፈናቀል ኣይሏል። የበለጠ ለቀቅ ያለ ነገር ቢመጣ ሃገር ሊያፈርስ ይችላል። ከዚህ በፊት ህወሃት በወታደር ሰብስቦ ይዟት ነው እንጂ ስርዓቱ ኣገር ኣፍራሽ ነው። ስለዚህ የፌደራል ስርዓታችን በሃገር በቀል የፌደራል ስርዓጥ መሻሻል ኣለበት። በአሮጌ ኣቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ ኣይደረግም። ዴሞክራሲን በብሄር ፌደራል ስርዓት ኣንተገብርም።

  2. ወያኔና ህዝቅኤል ከሸፉ
    ኢህአዴግ vs ሲዳማ vs ወላይታ
    ህዝብ የመረጠውና መንግስትነትን የተረከበው ኢህአዴግ ጊዜው ሳይጠናቀቅ በውህደት ስም ሌላ ፓርቲ ሊመሰርት ነው ትሉናላችሁ፡፡ ለማለት የፈለጋችሁት ቀሪውን ወራቶች ኢህአዴግ በሌለበት ማነው የመንግስትነት መንበር የሚይዘው ስትሉ እውነት ያላችሁ ይመስለኛል፡፡ እኔም እስማማለሁ፡፡
    ግን ድጋፍ ስትሰጡት የነበረው የሲዳማውስ ጉዳይ ምን ልትሉት ነው፡፡ ክልሎች መንስታት ናቸው፡፡ ሲዳማ ክልል ሆኖ ቢጠናቀቅ ቀሪውን ጊዜ የትኛው መንግስት ነው የሚመራው፡፡ እስቲ ስለዚህ ህወትና ሌላው ደጋፊና የሲዳማ ክልልነት አወንቃኝ የኦነጉ ፕሮፌሰር ይህ አስረዱን፡፡ ወያኔ የኢህአዴግን ውህደት ጉዳይ በዚህ ማጣጣል ከተነሳችሁ የሲዳማንም ምን ሊሆን እንደሚችል፤ የሌሎቹንም በደቡብ ክልል ተመሳሳይ ጥያቄን ዲሞክራሲያዊ ነው ስትሉን ስለነበር ዛሬ ተያዛችሁ፡፡ መልስ ስጡን፡፡ በቀጣይም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቢነሱ እንዴት አዲስ የክልል መንግስት መመስረት ይቻላል፤ ማንው አሸናፊ ፓርቲ ተብሎ የአዲሱን ክልል መንግስት መስራች የሚሆነው፡፡ በህገመንግስቱ መሰረት ስልጣን የሚያዘው መንግስትነትም የሚመሰረተው በምርጫ ነው፡፡ አሁን ላይ ማነው ሲዳማ፣ ወላይታ… መንግስት መመስረት የሚችለው፡፡ ደቡብ ክልል በምርጫ ያሸነፈው ደኢህዴን ነው፡፡ ሲአን፣ ወህዴን፣ አይደለምና፡፡ ማነው አዲሱ ክልል ላይ ስልጣን የሚረከበው-ጉድ ፈላ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.