የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለትህነግ መግለጫ የሰጠው አስደናቂ ምላሽ!

1 min read
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
ለትህነግ መግለጫ የሰጠው አስደናቂ ምላሽ!!!!!
————————-
የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ 7 ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ የጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለ VOA Amharic ዛሬ ማታ ምላሽ ሰጥተዋል።

ትህነግ በትላንቱ መግለጫው “እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም ፣ ከተዋሃዱም ኢህአዴግን ከማፍረስ ባሻገር ሃገርን ያፈርሳል” ማለቱ ይታወሳል።

አቶ ንጉሱ ዛሬ በሰጡት ምላሽ “በህወሃት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣላት ሳይሆን ከመጣበት ህዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው” ብለዋል፡፡

ለዚህም ምክንያቱም “መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅም መኖሩን እና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው” ብለዋል፡፡

የኢህአዴግን የውህደት እንቅስቃሴ አስመልክቶ ህወሃት በመግለጫው ያሰፈረውም ለዓመታት ሲያንፀባርቀው ከነበረው አቋም የተለየ እንደሆነ አቶ ንጉሱ ተናግረዋል፡፡አክለውም፥ ይህ የውህደት ሃሳብ ዛሬ የመጣ ሳይሆን ከ 7ኛ የድርጅት ጉባኤ ጀምሮ ሲብላላ የነበረና ለብዙ አመታት ውይይትና ጥናት ሲደረግበት የነበረ ነው ብለዋል። ይህ ውህደት አገራዊ አቅምን የሚጨምር እና የተሻለ ብሄራዊ መግባባትን የሚፈጥር ነው። በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል።

አሁን የመጣው የለውጥ ሂደት መቶ በመቶ ሳንካ አልባ ባይሆንም በርካታ አወንታዊ ለውጦችን እያስመዘገበ ነው። ይህ የለውጥ ሂደት ሁለት ነገሮች ላይ አበክሮ እየሰራ ነው።

1ኛ) ለሶስት አሰርት አመታት የቀጠሉ ችግሮችን ፣ ቁርሾዎችን ፣ የጥላቻ ትርክቶችን ወዘተ የማስተካከል እና ብሄራዊ መግባባትን የመፍጠር ስራዎችን ይሰራል ፤

2ኛ) የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ፣ የልማት ፣ የፍትሃዊነት ፣ የተጠቃሚነት ጥያቄዎችን የመመለስ ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው።

ይህን ለውጥ በመቃወም በተፃራሪ የሚያጣጥል መግለጫ የሰጠው ቡድን (ትህነግ) << ለውጡ መጣበት እንጅ ለውጡ አልመጣለትም ማለት ነው። >> ብለዋል።

ይህ ቡድን (ትህነግ) የህዝብ ፍላጎት እያፈነ ፣ የራሱ ህዝብ ወደ አደባባይ እንዳይወጣ እየከለከለ መሆኑን እናውቃለን። ይህን ሁሉ የሚያደርገውና ለውጡን እየተቃወመ ያለው ጥቅሙ ስለቀረበት መሆኑም ይታወቃል።

በጣም የሚገርመው ይህ ቡድን (ትህነግ) ለሁለት አስርት አመታት አጋር ያላቸውን ድርጅቶች ወይም ዜጎች አይደላችሁም ብሎ በአጋርነት ፈርጆ ከፖለቲካዊ ውሳኔ ሰጭነት ያገለላቸውን ድርጅቶች፣ ዛሬ ጥሪ እያቀረበላቸው ይገኛል በማለት አቶ ንጉሱ አግራሞታቸውን ገልፀዋል።

መተቸት ካለበት ከለውጡ በፊት የነበረው ፌደራሊዝም በትህነግ ብቻ የሚዘወር እና አሃዳዊ የነበረው ፌደራሊዝም ነው መተቸት የነበረበት ብለዋል አቶ ንጉሱ። ቀጥለውም << #የጡት_አባት ቀርቷል ፣ ህወሃት ብቻውን የሚዘውረው አሃዳዊ አገዛዝ አክትሟል >> በማለት እቅጩን ተናገርዋል።

በአጠቃላይ፣ አሉ አቶ ንጉሱ ፣ የህወሃት መግለጫ ከጊዜው ጋር የማይሄድና #ጊዜውን የማይመጥን መግለጫ ነው በማለት የህወሃትን መግለጫ አፈር ድሜ አብልተውታል። ይህ የጠ/ሚር ፅ/ቤት የሰጠው ምላሽ ግሩም ነው ማለት ይቻላል። የተለመደ አይነት አለመሆኑ አስደናቂ ነው።

ይህ የሚያሳየው በፌደራል መንግስት በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉን እና ትህነግ ከዚህ ቀደም እምቧ ከረዩ ሲል ለማግባባት በሚል የሚደረግ ትርፍ እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው። በአንፃሩ ትህነግም ይህን የፌዴራል መንግስት ቁርጥ አቋም በሚገባ የተረዳ ይመስላል። ለዚያም ነው ዛሬ ከመሼ በራያ ወረዳዎች ለሚገኙ ሚሊሺያዎች እና የልዩ ሃይል አባላቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
—-
እንደኔ መረጃ ከሆነ ወደ #ራያ_ቆቦ ሰብረው ለመግባት እየተዘጋጁ ሲሆን ድንገተኛ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉ ተነግሮኛል። በተመሳሳይ የራያ ወፍላ ሚሊሺያዎችን ወደ #ሰቆጣ እያስጠጉ መሆኑንም ሰምቻለሁ። የሚገርመው ዘመናዊ ከባድ መሳሪያዎች እና ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ ፈንጆች ጭምር ዝግጁ ሆነዋል።

በመሆኑም ይህ ያበደ ቡድን ምን አይነት ጥፋት ሊፈፅም እንደሚችል መገመት ስለማይቻል የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና አዴፓ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገው በተጠንቀቅ ዘብ እንዲቆሙ በራያ ህዝብ ስም ጥሪየን አቀርባለሁ። በዚህ ሰዓት የሁሉም ኢትዮጵያዊ አትኩሮት ወደ ራያ እና ወደ ወልቃይት እንዲሆን በማክበር እጠይቃለሁ። አመሰግናለሁ።

3 Comments

 1. ሰሞኑን የህውሃት መሃከላዊ ኮሚቴ በሚል የወጣው መግለጫ የትግራይን ህዝብ ህልምና አላማ ከማስቀደም ይልቅ፣በህዝባዊ ትግል ግፊት ኢህአዴግ ውስጥ በተደረገው መሸጋሸግ የበላይነቱ የተከረከመበትና፣ ይሄንን መቀበል ባለመፈለግና፣ ከተቻለም ለመቀልበስ መቀሌ መሽጎ የሚንቀሳቀሰው የስብሃት፣ አባይ ጸሃዬና ስዩም መስፍን ቡድን መግለጫ ነው ።
  የዛሬ ሁለት አመት ወር ፈጅቶ ያካሄደውን ስብሰባ ሲጨርስ መሃከላዊ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ‘አመራሩ የሃሳብና የተግባር አንድነት የጎደለው፣ጸረ ዴሞክራቲክ ተግባርና አስተሳሰብ ውስጥ በስፋት የተነከረ፣ በተልዕኮ ዙሪያ በመተጋገልና በመርህ ላይ የተመሰረተ አመራር የማይሰጥ፣ ህዝብንና አላማን ከማስቀደም ይልቅ የራሱን ክብርና ጥቅም የሚያስቀድም መሆኑ ታይቷል ‘ በሚል አስቀምጦት ነበር።

  ህወሃት ባለፉት ሁለት አመታት ይሄን መጠነ ሰፊ አስተዳደራዊ በደል አድርሼበታለሁ ያለውን የትግራይን ህዝብ ለመካስም ሆነ ፣ እንደ ድርጅትም ተሸክሜዋለሁ የሚለውን ድክመት ለማሻሽል ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ለ 27 አመታት ኢህአዴግን በሚያሽከረክርበት ወቅት ያደራጃቸውን ሎሌዎች በመጠቀም ሃገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ ከቦታ ቦታ እሳት ሲለኩስ የከረመ ድርጅት ነው።

  የዚህ መስረታዊ አላማም የኢህአዴግ ፈጣሪ እንደ መሆኔ፣ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በ እኩልነት ሳይሆን በበላይነት ማሽከርከር አለብኝ የሚለውን ዕብሪቱን ተግባራዊ ለማድረግና፣ የድርጅቱ መስራችና አይነኬ ነን ባዮቹን የስብሃት፣ አባይ ጸሃዬና ስዩም መስፍን ቡድን ወደለመዱት ስልጣን ማማ ለመመመለስ እንደሆነ ግልጽ ነው። ህወሃትም ሆነ ይሄ ስብስብ ያልገባቸው ነገር ቢኖር ያ ዘመን ላይመለስ ከሄደ ሁለተኛ አመቱን ሊያስቆጥር ወራት ብቻ እንደቀሩት ነው።

  የለውጥ ሃይሉ የበላይነትን ከተቀዳጀ ጀምሮ ማድረግ የነበረበት ቢሆንም፣ አሁንም ብዙ አልረፈደምና እህት ድርጅቶች፣ በህወሃት ውስጥ ያሉ ለውጡን የሚደግፉ ሃይሎች በገሃድ ወጥተው የስብሃት፣ አባይ ጸሃዬና ስዩም መስፍን ቡድን በቁጥጥራቸው ስር አድርገው፣ ከትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ጥቅምና ፍላጎት ውጭ የሚያሽከረክሩትን ድርጅት ነጻ አውጥተው ከተቀረው ወንድምና እህት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጋራ በመሆን ፣ በሀገራችን በተጀመረው ለውጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ በሚደረገው ትግል የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ሊይበረታቷቸው ይገባል።

 2. TPLF and the rest of the EPRDF are the same. If anyone is different from TPLF in ideology it is the 120 political parties, definitely not OPDO / ODP.

  Difference fire and hay are EPRDF the 120+ parties in the country, not TPLF and EPRDF member parties.. similar compared to the 120+ parties in the country.

 3. TPLF and the rest of the EPRDF are the same. If anyone is different from TPLF in ideology it is the 120 political parties, definitely not OPDO / ODP.

  Difference such as fire and hay are EPRDF the 120+ parties in the country, not TPLF and the other EPRDF member parties.. TPLF and the rest of EPRDF parties are alike sspeciallt when compared to the other 120+ political parties in the country.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.