አቶ አንዱዓለም አራጌ «የኦሮሞ እንቅስቃሴ»ን በሚመለከት ስለተናገረው ጥያቄ አለኝ ?! – አቻምየለህ ታምሩ

1 min read

አንዱዓለም አራጌ ባለፈው ሰሞን ዋሽንተን ዲሲ ያደረገውን የአዳራሽ ንግግር አደመጥኩት። ከዚህ ቀደም አንዱዓለም፣ በቀለ ገርባ ማዕከላዊ ሳሉ ስለ ገዳ የነገረውን እንዳለ ሳይመረመር ስለ ገዳ ዲሞክራሲያዊነት በመጽሐፉ ሊነግረን የሞከረው ነገር አልገረመኝም ነበር። አንዱዓለም እንደዚያ ብሎ መጻፉ ያላስገረመኝ እንኳን እሱ ከእስር ቤት ሆኖ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮችም ኦነጋውያን የፈጠሩትን ትርክት ሳይመረምሩ እየደገሙ ስለ ገዳ ዲሞክራሲያዊነት ሲሰብኩና ሲጽፉ ስናይ ስለምንውል ነው። በመሠረቱ ገዳ በዲሞክራሲ ምሳሌነቱ ሳይኾን ዲሞክራሲ የኾነ ሥርዓት ምን ዓይነት ሥርዓት መኾን እንደሌለበት ለማስተማር በምሳሌነት የሚቀርብ ወታደራዊ ሥርዓት ነው። ገዳ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ፍጹም ተቃራኒ ስለመኾኑ ማንበብ የሚሻ «የገዳ ሥርዓትና ዲሞክራሲ ምንና ምን ናቸው?» በሚል ያቀረብኩትን ጥናት ፈልጎ ያንብብ።

አንዱዓለም አራጌ ዲሲ ካደረገው ንግግር ተነስቼ ልጠይቀው የምፈልገው ጥያቄ በአባ ዱላ የተመራውን የሉባዎች ወታደራዊ ወረራን በሚመለከት ስለሰጠው አስተያየት ነው። አንዱዓለም ‹የኦሮሞ እንቅስቃሴ› በሚል የገለጸውን በአባ ዱላዎች የተመራ የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወታደራዊ የሉባዎች ወረራ በሚመለከት በሰጠው አስተያየት «ኦሮሞ ከባሌ ተነስቶ ራያ በመድረሱ ኩራት ይሰማኛል» ሲል ተናግሯል።

አንዱዓለም በአባ ዱላ የተመሩት ሉባዎች ከባሌ ተነስተው አንጎት/ራያ እስኪደርሱ ድረስ ባገኙት የኢትዮጵያ ምድር ላይ ሁሉ ያገኙትን ባለ ርስት የሬሳ ክምር እያደረጉ ያካሄዱትን ወታደራዊ ወረራ የዶሮ ላባ ጨብጠው፣ ቄጠማ እየነሰነሱና ጠበል እየረጩ ከባሌ ተነስተው ራያ የደረሱ ይመስለዋል፤ ወረራውን ‹የኦሮሞ እንቅስቃሴ› በማለት ማቃለሉ በሰው ቁስል እንጨት መስደድ መኾኑ የተገለጠለት አይመስልም።

አንዱዓለም አራጌ «ኦሮሞ ከባሌ ተነስቶ ራያ በመድረሱ ኩራት ይሰማኛል» በማለት በገለጸው ወረራ ምክንያት ኦሮምኛ የማይናገሩትን ሰልቅጦ በሚበላው በሞጋሳ ሥርዓት የራሳቸው ቋንቋ፣ ባህልና ማንነት የነበራቸው ብዙ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠፍተዋል። አማራን ጨምሮ ከ28 በላይ ነባር የኢትዮጵያ ነገዶች ከባሌ፣ ከደዋሮ፣ ከፈጠጋር፣ ከወጅ፣ ከሸዋ፣ ከዳሞት፣ ከቢዛሞ፣ ከገኝና ከእናርያ የጠፉት አንዱዓለም ‹የገዳ ዲሞክራሲ› በሚለው ወታደራዊ ሥርዓት ነው።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለዶክትሬት ማሟያቸው እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም. ባዘጋጁት «History of the Sayyoo Oromoo of Southwestern Wallaga, Ethiopia, from about 1730 to 1886» በሚለው ጥናታቸው ከገጽ 92 እስከ 136 ባቀረቡት ዝርዝር ጥናት በደቡብ ምዕራብ ወለጋ በሰዮ አካባቢ ብቻ በኦሮሞ ወረራ ምክንያት የሞጋሳ ልጅ ኾነው በግዳጅ የማንነት ለውጥ አድርገው እንዲጠፉ የተደረጉት ቀዳሚ የኢትዮጵያ ነገዶች ቁጥር ከአስራ ሦስት በላይ ናቸው። ዶክተር ነጋሶ በደቡብ ምዕራብ ወለጋ ሰዮ ወለጋ ውስጥ ብቻ ኦሮሞ ካጠፋቸው ነገዶች መካከል አማራ፣ ካንቺ፣ መጀንግ፣ ክወጉ፣ ክዋማ፣ ማኦ፣ ቡሳሴ፣ ኮንቺ፣ ጋንቃ፣ ወራጎ፣ ዳሞታ፣ ካዛ፣ አጋዲ፣ ገበቶና ሙጩኮ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። ፕ/ር ሕዝቅኤል ጋቢሳ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ወለጋ ውስጥ ይኖሩ ስለነበሩ ነባር የኢትዮጵያ ነገዶች ዝርዝር ከዚህ በፊት የጻፍኩትን መለስ ብሎ ማየት ይቻላል።

የተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት (United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO)) ባደረገው ጥናት መሠረት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 28 የጠፉ እና በመጥፋት ላይ ያሉ ቋንቋዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ የጋፋት፣ የአርጎባ፣ የአንፊሎ፣ የባምባሲ፣ ሆዞ፣ ክዋማ እና የዛይ ነገዶች እና ቋንቋ ተናጋሪዎች ይገኙበታል።

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው «A historical overview of the Wärğəḥ Muslim community in the Christian highland of Šäwa» በሚል በ2016 ባዘጋጀው ምርምር ከአንቀጽ 18-20 እንዳቀረበው፣ ፕ/ር መርዕድ ወልደ አረጋይ እ.ኤ.አ. በ1997 ዓ.ም. ባሳተሙት «Military Elites in Medieval Ethiopia» በሚለው ጥናታቸው ከገጽ 177-178 እንደጻፉት እና ዶ/ር ታደሰ ታምራት እ.ኤ.አ. በ1988 ዓ.ም. «Ethnic Interaction and Integration» በሚል ባቀረሙት ምርምር ገጽ 142 ላይ እንዳረጋገጡት ታሪካቸውን ብቻ የምናነብላቸው ሙሉ በሙሉ ቋንቋቸው እና ማንነታቸው ከጠፉት የኢትዮጵያ ነገዶች ውስጥ የማያ እና ወርጅህ ነገዶች ይገኙበታል።

ቀደም ብዬ የጠቀስኳቸው የማያ፣ የወርጅህ፣ የጋፋት፣ የአንፊሎ፣ የዛይ፣ አማራ ካንቺ፣ መጀንግ፣ ክወጉ፣ ክዋማ፣ ማኦ፣ ቡሳሴ፣ ኮንቺ፣ ጋንቃ፣ ወራጎ፣ ዳሞታ፣ ካዛ፣ አጋዲ፣ ገበቶና ሙጩኮ የሌሎችም የደቡብ፣ የምዕራብና መካከለኛው ኢትዮጵያ ነገዶች የዘር መሳሳትና ጨርሶ የመጥፋት ዕጣ ፈንታ የገጠማቸው አንዱዓለምአራጌ እንደሚኮራበት በነገረን የኦሮሞ መስፋፋት ምክንያት ርስታቸው ስለፈለሰ፣ በጅምላ ስለተገደሉና የተረፉት የሞጋሳ ልጆች እንዲኾኑ ተገደው ማንነታቸው እንዲለውጡ ስለተደረጉ ነው። የማኦ፣ የዛይና የአርጎባ ማኅረሰቦች ዘራቸው እጅግ በጣም የሳሳና እንደጠፉ የሚቆጠሩም ናቸው። እዚህ የዘረዘርናቸው ነባር የኢትዮጵያ ነገዶች ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት በጣም ሰፋፊ የርስት መሬት የነበራቸው ነበሩ፤ ለአብነት እኒህን ጠቀስን እንጂ በኦሮሞ ጎሳዎች ወረራና ሰፈራ ምክንያት ከአጽመ ርስታቸው የፈለሱት እና የሞጋሳ ልጅ ኾነው የጠፉት የጥንት ነገዶች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው።

አንዱዓለም የሚኮራበት እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት ዛሬ ኦሮሚያ በሚባለው ምድር ይኖር የነበረው ነባር ሕዝብ የኦሮሞ ባህልና ቋንቋ በግድ ሳይጫንበት በኢትዮጵያ ፊደል የሚጽፍ፣ በግዕዝ የሚቀድስ፣ በሌላው የሴም ቋንቋ በዐረቢኛ ዱአ ያደርግ የነበረውን ክርስቲያንና ሙስሊም የነበረ ሕዝብ ነው።

ዛሬ ኦሮሚያ በሚባለው ክልል የሚኖረው አንዱዓለም በሚኮራበት እንቅስቃሴ ኦሮምኛ ተናጋሪ እንዲኾን የተደረገው ሕዝብ ከአባ ገዳዎችና ከተወላጆቻቸው በስተቀር የተቀረው የኦሮሞ ባህልና ቋንቋ በግድ ሳይጫንበት የሐዲያ፣ የሲዳማ፣ የአማራ፣ የከምባታ፣ የትግሬ፣ የጉራጌ፣ የዛይ፣ የዳሞት፣ የጋፋት፣ የአርጎባ፣ የጋሞ፣ ወዘተ ተወላጅነት የነበረውና ሙስሊምና ክርስቲያን የነበረ ሕዝብ ነው። ይህንን ታሪክ ዐረቦችም አውሮፓውያኑም የጻፉት እውነት ነው።

ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ክርስቲያን የነበረውና በግዕዝ ይቀድስ የነበረው ይህ ሕዝብ እስከ ጳጳስ የደረሰ የነፍስ አባት ነበረው። ለዚህም ዝቋላን፣ አዳዲ ማሪያምን፣ ዝዋይን፣ መናገሻን፣ ዋሻ ሚካኤልን፣ ደብረ ሊባኖስን የደበረ፤ ባሊ የሚገኘውን የላሊበላ ውቅር ገዳም የፈለፈለ ሕዝብ መኾኑን እንደ አብነት ማንሳት ይቻላል። ይህ ሕዝብ ኦሮምኛ ተጭኖበት ኦሮምኛ መናገር ሳይጀምር፣ ማንም ሳይጭንበት የራሱ የኾነውን ግዕዝን ያውቅ የነበረ ሕዝብ ነው፡፡

እንግዲህ! አንዱዓለም በሚኮራበት እንቅስቃሴ ኦሮሞ ከባሌ በታች ተነስቶ ራያ የደረሰው ከ1514 ዓ.ም. ጀምሮ ነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች ድምጥማጣቸውን እያጠፋ፣ ማንነታቸውን እየቀየረ፣ ቋንቋቸውን እየደመሰሰ፣ በመሬታቸው ላይ ጭሰኛ እያደረገ፣ የነበራቸውን ቁሳዊና መንፈሳዊ ሥልጣኔ እያወደመ፣ የኢትዮጵያን ምድር የሰው ልጅ ግዳይ ክምርና የደም ጎርፍ የሚፈስበት ገሀነም በማድረግ ግፍ እየሰራ ነው። ባጭሩ ኦሮሞ ከባሌ በታች ተነስቶ ራያ የደረሰው እያጠፋ ነው። ለዚህም ነው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን የጎበኘው ስኮትላንዳዊው ጀምስ ብሩስ እ.ኤ.አ. በ1791 ዓ.ም. ባሳተመው «Travels to discover the source of the Nile: in the years 1768, 1769, 1770, 1771, 1772, and 1773. In six volumes» መጽሐፉ ቅጽ ሁለት ገጽ 400 ላይ፡-“The Galla has contributed more to weakening and reducing the Abyssinia than all its civil wars and foreign enemies put together.” ሲል ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡት የውጭ ወረራዎች እና የግራኝ ወረራን ጨምሮ የሀገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነቶች፣ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሱት እልቂትና ውድመት በአንድነት ተደምሮ በአባ ዱላዎች የተመራው የሉባዎች ወታደራዊ ወረራ በኢትዮጵያ ላይ ካደረሰው ውድመትና እልቂት ያነሰ ሰው ሲል የኦሮሞን ወረራ የገለጸው!

አንዱዓለም አራጌ ምንም እንኳ በጀርመን ጉብኝቱ የአማራ ልጆች ሊያናግሩት ፈልገው «አማራ ነህ ከምትሉኝ ብትገድሉኝ ይሻለኛል» ቢልም ወያኔዎች ግን በግፍ አስረው ፍዳውን ያስከተቱት አማራ ነው ብለው ነው። በሌላ አነጋገር አንዱዓለም የወያኔዎች የግፍ ሰለባ የኾነው በማንነቱ ምክንያት ነው።

በማንነቱ ምክንያት ግፍ ለደረሰበት አንዱዓለም አራጌ የማቀርበው ጥያቄ፣ ኦሮምኛ የሚናገር ‹ቢርመዱዳ እንጡቂና› ኦሮምኛ የማይናገር ‹ዲና በሌሣ› ወይም ‹ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ፡፡› በሚል በማንነት ላይ የተመሠረተ ማጥፋትን ፖሊሲው በነበረው የገዳ ሥርዓት አማካኝነት ነባር የኢትዮጵያን ነገዶች እያጠፉ ርስታቸውን የሬሳ ክምር እያደረጉ ከባሌ በታች ተነስተው ራያ በደረሰው በኦሮሞ አባ ዱላዎች በተመራው የሉባ ወታደሮች የግፍ ወረራ የሚኮራ ከኾነ ወያኔዎች እስር ቤት አስገብተው ባደረሱብህ ግፍስ ኩራት ይሰማሀል ወይ? የሚል ነው። ወያኔዎች በአንዱዓለም ላይ የፈጸሙት ግፍ ከባሌ በታች ተነስቶ ራያ የደረሰው በአባ ዱላዎች የተመራውን የሉባዎች ወታደራዊ ወረራ ካደረሰው ጥፋት ጋር ሲወዳደር በጣም ቀላልና በግለሰብ ደረጃ የደረሰ ነው። የሉባዎቹ የግፍ ዘመቻ ግን ከ28 በላይ የኢትዮጵያ ነባር ነገዶችን ጠራርጎ ያጠፋ ነው። ከኦሮሞ ውጭ ያሉትን የኢትዮጵያ ነገዶች ጠራርጎ በመደምሰስ ላይ የተመሰረተው የገዳ ወታደራዊ ወረራ ውጤት የሆነው ከባሌ በታች ጀምሮ እስከ ራያ የደረሰው «የኦሮሞ እንቅስቃሴ» ሊኮራበት የሚገባ መልካም ነገር ወይስ በእጅጉ ሊወገዝና በጥብቅ ሊኮነን የሚገባው የግፍ ተግባር? እስቲ መልስልን?!

14 Comments

 1. Galas:

  Do you have now an intellectual who can challenge Achamyeleh? Ewnetim Achamyeleh

  I have a great respect for Andualem Arage, but I understand why he stated the gala invasion of North Ethiopia as “oromo movement”. If he listens, I advise him to dissociate himself from the traitors like Brehanu Nega so that he can speak for himself and the truth and only the truth.

 2. ስለ ገዳ ስርአት የፃፍከውን እንተወውና የኦሮሞ ወረራ ብለህ በገለፅከው ጉዳይ ብዙ በደል ተፈፅሟል እያልከን ነው። እውነት ነው ብለን ወቀሳ እናቅርብ ቢባል አንተ ደሞ በኦሮሞ ወገን ሆነህ ሚሊሊክ በወረራ ወቅት አደረሰ ስለሚባለው ጉዳት ሚሊሊክን ለመውቀስ ዝግጁ ነህ???? ወይስ ያንተን እውነት ነው ብለን የነሱን ተረት ነው እንበል?????

 3. ለአንድነትና ለአብሮ መኖር ሲባል ያለፈውን ቁስል አለመንካቱ ይሻል ነበር። ችግሩ የግፍ ሰለባ አድራሾቹ የኛን ዝምታ እንዳለማወቅ ቆጥረው በፈጠራ ትርክት እኛን መወንጀልና የፈለጉትን ሲያደርጉ ቁልጭ ቁልጭ እያልን በፀፀት እንድንሸማቀቅላቸው የክፋት ሰበዝ ሊመዙብን ይሻሉ።
  ስለዚህ ያለምንም ርህራሄ ታሪኩ በአደባባይ መነገር አለበት።

 4. unless the so called oromos (real name borena, oromo is german invention) are told to keep the peace or if not to go back to Ceylon (sri lanka), things can only get worse down the road. politicians like andualem behave as if they are running for the office of chief priest or pastor.

 5. Every anti-Ethiopian forces directly or indirectly conciously or unconciously are working for the interest of the invisible hand of the synagogue of international jewry.It is being wise to read the protocols.

 6. Every anti-Ethiopian forces directly or indirectly conciously or unconciously are working for the interest of the invisible hand of the synagogue of international jewry.It is being wise to read the protocols.

 7. Ante ye nefxenya shint hoyi, tamehal. Amanu’el hid. Ahun Oromo keristu leqo yanten ligag yemiyastenagidibet dereja layi yale yimesilihal. Yeza tamami Prof. tabiye debtera Getachew Haile ye af qizen iwunet mesloh tiqazyleh ayidel????? Qizyetam. Yetinyawum yalem hizib be hizibinetu yeseferebetin bota ageru argo yinoral, iyenorem new. Nafxanya gin be mengist dereja (institutionally)neber Oromon yewererewu. Yan meqelbes gid yilal. Oromo mebtun yaskebiral begid. Tayaleh. Qizenam.

 8. No Oromo can challenge/disprove Achamyeleh’s historical facts.We will have more to say ahead if the current OLF madness continues.

 9. What proof should one bring up against a rude insult?? That is what your Achamyeleh is best at: insults and vomitting his anti-Oromo venom laced with half-truths and outright lies. One can not argue with a sick mind. Look, he quotes himself as ‘proof’ of his mental diarrhea! “ገዳ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ፍጹም ተቃራኒ ስለመኾኑ ማንበብ የሚሻ «የገዳ ሥርዓትና ዲሞክራሲ ምንና ምን ናቸው?» በሚል ያቀረብኩትን ጥናት ፈልጎ ያንብብ።” ይልሃል! According to him, Prof. Asmerom Legesse, who wrote 2 book on Gadaa, and many other antropologists and ethnologes, and UNESCO are all wrong!

  Just a simple info for this sick mind: Moggasa is not and has never been a forced conversion. It was a naturalization process initiated by the convertee on his/her free will, the same way today migrants to Europe and USA ask for citizenship! Oromuma was/is not a question of blood or DNA. That is why we say OROMO is a NATION.

  More importantly, the narration that Oromos migrated from some south corner of present day Ethiopia is FALSE! A fabrication by the NefTegna system to legitimize its conquest of the Oromo and the South. There was/is always back and forth population movement, but Oromo was indigenous to its present settlement and even beyond. Oromo is the core Kush, from which others split off. Even Achamyeleh should check his own genealogy, if he can!

  • Why should a person voluntarily gets converted into gallaness. Is it to have inferiority complex, to be savage, to have a “kegna” attitude etc?

   NO one voluntarily gets converted into gallaness unless told that he or she will loss his penis or her breast, respectively.

 10. Everybody has a little bit of the sun and moon in them. Everybody has a little bit of man, woman, Amhara, Orimo and animal in them. Darks and lights in them. Everyone is part of a connected cosmic system. Part earth and sea, wind and fire, with some salt and dust swimming in them. We have a universe within ourselves that mimics the universe outside. None of us are just black or white, or never wrong and always right. No one. No one exists without polarities. Everybody has good and bad forces working with them, against them, and within them.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.