በድጋሚ እንጮኻለን – ሁሉም ከህግ እና ስርአት በታች ካልሆነ ማናችንም ከጥቃት ሰለባነት አንተርፍም! (ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

የትናንት ማታውን ክስተትም ይሁን የሰሞኑን ጉዳይ በነጠላው ማየት አይገባም – እየተንከባለለ የመጣ ከህግ እና ስርአት በላይ የሆነው አይነኬ “ሁለተኛው መንግሰት” ላለፉት በርካታ ወራት ውስጥ በተፈጠሩ ክስተቶች የነበረውን ሚና መለስ ብሎ መመርመር ከተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዳንደርስ ይረዳናል። የሚሆነው ሁሉ ትናንት እንደ አዲስ የተፈጠረ አይደለም –

እኔ ነገሩ የበቃኝ ኦብሳ የተባለው ጉብል ሽጉጥ በቅምጥል ይዞ ፌስቡክ ላይ ፎቶ የለጠፈ ጊዜ ነው። ይህ ልጅ የኢሬቻ ሆረ ፍንፊኔ ቀን ወደ በአሉ የሚሄደውንም የማይሄደውንም የአዲስ አበባን ህዝብ እና በአሉን ለማክበር በዙሪያው ካሉ ከተሞች የመጡ ዜጎችን በየአስር ሜትር በፍተሻ እያዘለሉ ከስርአት ውጪ ቴረራይዝ ሲያደርጉ የነበሩትን ፎሌዎች በማዕከል ሲመራ ነበር። ያው ከዛ ቀደም “የባላደራው” መግለጫ ላይ ተገኝቶ ግጭት የፈጠረው ሸበላው ባለአፍሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ልጅ ማለት ነው።

ቅርብ ጊዜም ባላደራው ስለጠራው ሰልፍ መግለጫ በሰጠበት ቀን በቦታው ተገኝተው “የተቃውሞ ሰልፍ” ያካሄዱትን ወጣቶች ዞር ብሎ የሚመራውም እርሱ ነበር። (ለአዋቂዎችም – ለማታውቁም እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከጀርባ ረብጣ ገንዘብ እየፈሰሰ ፈንድ እንደሚደረጉ ለመጠቆም አወዳለሁ)

የሰሞኑ ክስተት ላይ ደግሞ ከህግ እና ስርዓት በላይ የሆነው “ሁለተኛው መንግስት” መሳፍንቶች ከሆነው አንዱ “የግድያ ሙከራ” በሚል የተቀባባች ማመካኛ የብዙዎችን ነፍስ የነጠቀ ሁከት ሲፈጠር ይሄው ልጅ መሳሪያ ታጥቆ ከመሰሎቹ ጋር በህግ ላልተቋቋመው “ሁለተኛ መንግስት” ጥበቃ ሲያደርግ ብዙዎች አይታችኋል።

ያው መንግስታዊ መዋቅሩም badly compromised እንደተደረገ እና ከነዚህ አዲስ አበባ ላይ ኢመደበኛ መዋቅር ከዘረጉ “የሁለተኛው መንግስት” ሰራዊቶች ጋር ተናቦ እንደሚሰራ ሊታወቅ ይገባል (አንዳንዴ ያዙታል ሌላ ጊዜ ይታዘዙታል)። ይህ speculation አይደለም የመንግስት ባላስልጣናትን ሳይቀር ያስጨነቀ FACT ነው።

ትናንት ማታ “በባላደራው” ሰዎች ላይ የሆነው ነገር ዜጎች ተሳቀው በፍርሃት አሜን ብለው ለአፋኙ “ተደራቢ መንግስት” እንዲገዙ፣ የመንግስት ሰዎችም ሆኑ ህዝቡ “በሁለተኛው መንግስት” ተፅዕኖ ስር እንዲወድቁ የሚደረግ ጥረት አካል ነው። ይህ ከህግ እና ስርአት ውጪ የሆነ “ኢመደበኛ መዋቅር” አይደለም “ለባላደራው” እና ላልተደራጀን ተራ ዜጎች ይቅርና ለባለስልጣናትም እንደማይመለስ ለማሳያ እንዲሆን አንድ አጋጣሚ ልጥቀስ…

ይህ “ተደራቢ መንግስት” ከከተማ መስተዳደሩ ፕሮቶኮል እና የመንግስት አሰራር ውጪ የኢሬቻ ሆረ ፍንፊኔ ዋዜማ በአል ላይ የክቡር ከንቲባችንን (የሚወክሉት ህዝባችንን) ክብር በሚነካ መልኩ ከተፈቀደው parameter በጉልበቱ ጥሶ ገብቶ መድረኩን በታጣቂዎች ሲያምስ እንደነበር በወቅቱ ጉዳዩን በቲቪም በአካልም ሲከታተሉ የነበሩ ዜጎች የታዘቡት ሀቅ ነው። ይህ ከህግ ወጪ የመሆን ነገር እንዲሁ በብዙ አጋጣሚዎች ሲንፀባረቅ የቆየ ነው። እያንዳንዱን ጥቃቅን ምልክት ብዘረዝረው አያልቅም!

እንደውም እኔ መንግስት ህግ እና ስርአት እንዲያስከብር ለመወትወት እጅግ ዘግይቻለሁ። አጓጉል ከነገ ዛሬ ራሳቸው መልክ ያስይዙታል ብዬ በእርጋታ ስታዘብ ቆይቻለሁ። አሁን ግን በዛ – ትዕግስቱ በዛ፣ ቸልተኝነቱ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት እያሳጣን ነው። ይባስ ብሎ የሀገሪቱን ፖለቲካ ሊያቃውስ ከጫፍ ደርሷል። ተስፋችንን ሊነጥቅ እያደባ ነው።

ተስፋ የጣልንባችሁ የለውጡ መሪዎች እባካችሁ ተመከሩ – ይህ ሀይል ለናንተም እንደማይመለስ ብዙ ምልክት አሳይቷችኋል። የተሰጣችሁ የህዝብ አደራ እና የህዝብ ስልጣን በሚገባው ቦታ ላይ ይዋል። ሁላችን ከህግና ስርአት በታች ካልሆንን ሁላችንም በአራዊት ህግ ልንገዛ እንገደዳለን።

ይህ ከህግ እና ስርአት በላይ የሆነ “ሁለተኛ መንግስት” ፈተና ስለሆነባቸው አንዳንድ “የባላደራዎቹ” ልጆችም ድምፅ አልባ መሳሪያዎች ይዘው ራሳቸውን መጠበቅ መጀመራቸውን ሰምቻለሁ – በቶሎ ህግ እና ስርአት ካላስከበራችሁ ዜጎች ደህንነታቸው ለመጠበቅ በራሳቸው እንዲንቀሳቀሱ ይገደዳሉ። ተፈጥሯዊ ነውና –

ደህንነታችንን ያስጠብቅልናል ያልነው የምንታመንበት መንግስት ቸል ካለ መተማመኛ መፈለግ ተፈጥሯዊ ነው – ችግሩ ይህ አማራጭ ለስርአት አልበኝነት መስፋፋት በር መክፈቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የእርስ በእርስ ግጭት/ጦርነት ሊያስከትልም ይችላል።

መንግስት ሆይ ፍጠን። ከመደበኛው መንግስት ውጪ ሌላ ተደራቢ መንግስት እንደሌለ አስረግጠህ ለዜጎች በግብርህ አስታውቅ። ሳይረፍድ ቤትህንም አፅዳ – “ሁለተኛው መንግስት” የፀጥታ መዋቅርህን ሳይቀር ጠልፎታል – ታውቃለህ – እንደ ካንሰር ከውስጥ በልቶህ አደጋው ሳይገዝፍ ከውስጥም ነቅለህ አውጣው –

ህግ እና ስርአት ማስከበር አንባገነንነት አይደለም። የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ዴሞክራሲን ማፈን አይደለም። ይልቁንስ ሁሉም ከህግ እና ስርአት በታች ካልሆነ ዴሞክራሲም ከንቱ ነው – ፍትህም በጥቂቶች እጅ ትወድቃለች – ማንም ከጥቃት ሰለባነት አይተርፍም!!! እንግዲህ የሚሰማ ቢኖር ተናግረናል!

4 Responses to በድጋሚ እንጮኻለን – ሁሉም ከህግ እና ስርአት በታች ካልሆነ ማናችንም ከጥቃት ሰለባነት አንተርፍም! (ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ)

 1. ዮናታን ሰሞኑን አፍህን እስከ ቂጥህ ድረስ መክፈት ጀምረሃል። ለመሁኑ ኦብሳ በሚል ስም ሌላ ሰዉ ሽጉጥ ያዘዉን ወጣት አለመለጠፉን ምን ማስረጃ አለህ? እንዳንተ አይነቱን ወላዋዮች ለመቀስቀስ ሲል ለጣፊዉ ትግሬም፤ አማራም ሊሆን ይችላል። ወይ ደግሞ አንተዉ ራስህ ልትሆን ትችላለህ።

  Avatar for ጓዴ

  ጓዴ
  November 3, 2019 at 12:24 pm
  Reply

 2. ደንቆሮን ደንቆሮ ነው ማይል መሪ ኢትዬጲያውያን የማሻገርም ሆነ የመምራት አቅም አይኖረውም! በሌላ ቋንቋ #ተንሻፎ# የተፈጠረ መሪ ድሮም ሸፋፋ መሆኑ አይቀሬ ነው! እያዳሉ ፍርድ እና የተንሻፈፈ ፍርድ እየሰጡ ብሎም እየፈረዱ የኢትዮጵያ መሪ ነኝ ማለት ለኔ አይዋጥልኝም!አልሰማም! እኔም ሀገር የገነባሁ ሀገር ያቆየሁ ምርጥ #ነፍጠኛ# ስለሆንሁ! ከገንጣይ ከጠባብ ብሎም የሰውን ልጅ እንደ በግ ከሚያርዱ ደንቆሮ ግለሰቦች ዛሬም ሆነ ነገ ትብብርም የለኝም! መሪ ተብየው ግን ከአስገዳይ ከገዳይ ጋር እያውም የሰው ልጅ እንደ እንስሳ ከሚያርዱ ከብት አስተሳሰብ ካላቸው ጋር በኢትዮጵያ ምድር መደራደር ከዚህ በላይ ክህደት እያውም በመሪ ሲፈፀም ምን ማለት ነው? ሌባን ሌባ ማለት ያልቻለ መሪ ኢትዮጵያን የማሻገርም ሆነ የማዳን ምንም አይነት ስራ መስራት እንደማይችል በተግባር አየን! በዚህ ዘመን #ሁለት ምላስ# ሚያራምድ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪካችን አየን ሰማን! ሁለት ምላስ ያለው ማን እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን ማርዳት ለሰይጣን ማስተማር ነው ሚሆነው! ሲበቃ በቃ ማለት ሚያውቅ ማህበረሰብን ማጭበርበር ግን ሀገር ማታለል ስለሆነ መሪ ነኝ ብለው ሚዶሉቱት ጠ/ር እና #ጀዋር# ባስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ! መሪዎች አቅም ከለላየውም በአስቸኳይ ለህዝብ ያሳውቁ! ቀጣዩ እጅግ የከፋ እና የመጠፋፋት ዘመን መሆኑን ስለምናውቅ!ለዚህም ጠ/ሚር ተብየው እሰሩ መሆናቸው አለም ያወቀው ሚስጥር ነው! ደም ሚጥማቸው! ሰው እያለቀሰ ሚደሰቱ ለይምሰል መግለጫ እና እንባ ሚያነቡ! በአገሬ ቋንቋ #ከአስመሳይ መሪ እና ሰው እግዚአብሔር እኛንም ሆነ ሀገራችንን ይጠብቅልን!# እረ ወሬ እና ስብከት ጠላን!!!

  Avatar for Babillon Jutass

  Babillon Jutass
  November 3, 2019 at 1:40 pm
  Reply

 3. Yonatan,

  You are like chamaeleon. Stop your double standard. You were growing up with the psychology of hatred. Don’t use the name Regassa. You have to change it to Kitachew or Yeyhired.

  Avatar for Gamadaa

  Gamadaa
  November 3, 2019 at 11:43 pm
  Reply

 4. Yonatan,

  I used consider you as a rational thinker. But you behave in the last couple of weeks like those form the Debtera school of thought. You live in Finfinne and observe the campaign against the great Oromo people. But you have said nothing about the daily campaigns against the Oromo people in general and the Oromo cultural values in particular by all the medias outlets based in Finfinne and abroad. Really, it is ridiculous!

  The malicious politics of the hatemongers will not work in the new Ethiopia any more. The scramble for Oromia like the Menilik’s era is no more possible. But the ultranationalists can keep on their making noises in the coming years. But it will not keep back the democratization process in Ethiopia. The main problems with the offsprings of the ex-neftengas are their greediness and selfishness. They are still dreaming for the “golden” time of the their forefathers. 

  De-Amharanisation of the whole Ethiopian politics is indispensable and absolutely necessary in order to reform and reshape Ethiopia as a country of multinational state. The politics of one language, one culture  and a single nation cannot be accepted any more. Also there is no Ethiopian identity as some idiotic individuals try preach us those like the chameleon Ermias Legesse. It is a fake identity and ridiculous. Dissociating Ethiopia from the politics of Menilik is indispensable for emancipation of all  the nations and natinalitis in Ethiopia.

  Avatar for Gamadaa

  Gamadaa
  November 5, 2019 at 2:01 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.