የሬሳ ዘር መቁጠሩ ሲገርመኝ የሟች ዘር የቁጥር ድልድሉ ይብስ ያስተዛዝባል – መስከረም አበራ

1 min read

በአሁኑ ወቅት በሃገራችን የሚከሰቱ ፖለቲካዊ ክስተቶች በሊቃውንት ቀርቶ በእኔ ቢጤው ተራ ሰው ውስን ግንዛቤ እንኳን ብዙ ትርጉም የሚወጣላቸው፣በርካታ ሰበዝ የሚመዘዝባቸው፣ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡ ሆኖም የተረዳሁትን ሁሉ ለመፃፍ አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም አንዳድ እውነቶች የሚነገሩበት ጊዜ አለ፤ እውነት ከሚነገር ይልቅ ባይነገር በጎ የሚሆንበት አንዳንድ የጭንቅ ወቅት አለ፡፡

ዛሬ ሃገሬ የምትገኝበት የጭንቅ ወቅት የተረዱትን ሁሉ በተረዱት መጠን፣ባዘኑበት ልክ የሚነገርበት መስሎ አይሰማኝም፡፡የምናገረው እውነት እንደሆነ ባውቅም፤ያለወቅቱ የተነገረ እውነትም ሃገሬን ሊያጠፋ ይችላል ብየ ስለማምን የጠ/ሚውን ንግግር ከሰማሁ በኋላ አሁን ልቦናየ የሚነግረኝን ነገር ሁሉ ከመናገር እቆጠባሁ፡፡

መግለጫውን ስለማ ግን ተስፋ ማጣት እጅግ ተፈታትኖኛል፣ሃገሬ ሰው አልቆባት ኦና እንደቀረች ተሰምቶኛል፣ማስተዋል ከነገስታት እንደራቀች ገብቶኛል፣መሪዎቻችን የእኛን የተመሪዎቻቸውን የማገናዘብ ደረጃ እንዴት አሳንሰው እንደሚያዩ በደምብ ተረድቻለሁ፡፡ ፖለቲካ እና ፖለቲኝነት ከምገምተው በላይ ረቂቅ ውስብስቦሽ እንዳለው ተገንዝቤያለሁ፡፡ፖለቲከኛ ሲኮን የሆነ የሰውነት መልካም ገፅታ ከሰዎች እንደሚሸሽም ጠርጥሬያለሁ፡፡

የትኛውም የሃገሬ ሰው እንዲሞት አልሻም፡፡ የሟች ብሄረሰብ ማንነት ለሞቱ የተሰማኝን ሃዘን አይጨምርም አይቀንስም፡፡ በደህና ቀን የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰሃሳብ የማረከኝ ሰው ነኝ!ከሰብዓዊነት የበለጠ ውብ ነገር አይታየኝም፡፡የሰብዊነት ዋነኛ ጠር ደግሞ ዘረኝነት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡እንደ ዘረኝነት የሰው ልጅን ከከፍታ የሚያወርድ ነገር እንደሌለ በዓለም ላይ የተከሰቱ አሰቃቂ የዘር ማጥፋቶች ምስክር ናቸው፡፡

የዛሬው የጠ/ሚው መግለጫ የሬሳ ዘር መቁጠሩ ሲገርመኝ፣የሟች ዘር የቁጥር ድልድሉ ይብስ ያስተዛዝባል፡፡የሬሳ ዘር መቁጠሩን ካነሱት ዘንዳ በኦሮሚያ ኮሽ ሲል የማን ሬሳ እንደሚታፈስ ማን ይጠፋዋል ተብሎ ነው ይሄ ሁሉ የቁጥር ጨዋታ? የሞተ ቀርቶ የቆመ ሰው ዘር መቁጠር ስራ ፈትነት እንደሆነ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም የዛሬው ሪፖርት የያዘው ሆድ ሲያውቅ የሆነ የቁጥር መረጃ ዘረኝነት ማለቂያ ወደሌለው አዘቅት እያወረደን እንደሆነ ህያው ምስክር ነው፡፡

ፖለቲካችን ከዘር ፖለቲካ ካልተዋጀ ሃገራችን እንደ ሩዋንዳ የሬሳ ክምር የሚያከረፋት፣የሞት መንፈስ የሚያስበረግጋት፣ስሟ ራሱ እልቂትን የሚያሳስብ የጣረሞት አምባ መሆኗ አይቀሬ ነው፡፡ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋቱ ካለፈ ብዙ አመት ቢሆንም በበኩሌ አሁንም ሩዋንዳ ሲባል የሚሰቀጥጠኝ ነገር አለ! በፍሪካ ሃገር ባልሄድባት የምመርጠው ሃገር ነች-ሩዋንዳ…..በሩዋንዳ ዛሬም በየመንገዱ የሚጮህ ደም የሚዋጋ አጥንት ያለ ይመስለኛል

አካሄዳችን ግን ሃገሬንም እንዲህ ዘመን የማይሽረው የጣረሞት ምድር እንዳያደርጋት ስጋት አለኝ ፤ያውም እንደ ሩዋንዳ ከእልቂት በኋላም ሃገር መሆን ከተቻለ ነው! ይጎዝላቪያን መሆንም አለ-መተላለቅም ሃገር ማጣትም የተጣመሩበት ሁለት ኪሳራ……

መስከረም አበራ

10 Comments

 1. አላማው መሪ ተብየ መን እንደሆነ እየነገረን እኦ ነው! በውሸትም ሆነ በእውነት ቢሞቱም የበዛው ብሄር የኔ ነው አያገባችሁም ነው! ከመሪ ይህ አይነት ትርክት ሲሰማ ለካ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሳናይ ምናምን የዋሆች ነን!እኛ ኢትዬጲያውያን ነጠየቅነው የሰው ልጅ እያውም በአምላክ የተፈጠረ ፍጡር መንግስት ባለበት ሀገር እነደንስሳ አይታረድ! አይገደል! ነው። በዘር ጫዋታ የራስን ድክመት ለመሸፈን የተደረገች አሻጥር! ሌባን ሌባ! አስገዳይን እና ገዳይን ላለመያዝ የተደረገች ሴራ! ለካ እንዲህ መንግስት ነኝ ያለ መሪ እንደመህ ወርዶ ይበላሻል! ያገሬ ሰው ሳላውቅ በስህተት እያወቀሰሁ በድፍረት ነሰራሀለተሰን ሀጢያት ይቅር በለኝ ጌታየ ይላል!!! አየሰን አውጦ ምንም አሰንዳልተፈጠረ ከሚያወራ መሪ ጌታ ይሰውረን! የንፁሀን እንባ እና ደም ይፋረድልን! ይቺ ሸርተት ሸርት ነጠር ነሰሩ አሸባሪዎችን ላለማሰር ከምትደረግ ተግባር አንዷ ናት! “ደሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” ነው የተባለው! “እኛም ከነቃን ቆየን ልናሳይ እውነቱን”! የኢትዬጵያ ምድር አሰንኳን እብዱን ቀርቶ ጤነኛ ሁኖ ነገር ካሰበ ብዙ ያስቀባትረዋል! ወደገደሉ ገብተው እስኪያልቁ የሞት ሞት ማውራታቸው መሪ ነኝ ከሚሉ ይጠበቃል! ስራ ስሩ …….!!! ወሬ በቃን…….!!! ገደሠዬች ይታሰሩ አስገዳዬችም ይታሰሩ……..!!! ፍርዱ ስለማይቀር!!!

 2. አይ አሳዛኙ ጠቅላያችን ወደ ሬሳ ድልድል ገቡ በጣም ያሳዝናል አሁን ይህ መግለጫ ሀገር ያረጋጋል ብለው ነው ያባብሳል እንጂ ስለዚ ከፖለቲካኖትዎ ይልቅ ፓስተርነትዎ ስብከትዎ የሚዋጣሎት ይመስለኛል ጠቅላይ ሬሳ አይቆጥርም መቁጠርም የለበትም፡፡

 3. You have been demonizing the Oromo people in general and the Qerroos in particular. But now it is clear who are the demons. Those who have been crying loudly are the demons. You are one of the members of those demons. Thus, you can keep on your crying till the demons in you will be casted out.

  • Mr. Gemed,

   Everything you are writing is out of the topic and rubbish. You are just like your mindless korkoro/Kero cousins. This forum would be a great place without you.

 4. “ባይገጥምም ሃሳቤ ማደር ስላልቻል በውስጤ …”
  ስሙን ሳይለውጥ የጡት አባቱን ትእዛዛ ሲፈጽም ሲያስፈጽም የቆየው ቅጠረኛና ባንድ ድርጀት ሁላ ምዝኪን ምን እንደሚሰራ የማያውቅ እጁ ተያዞ የሚድህ ህጻን አይነት ነገር ነው፡፡ አሁንም ለመዳህ ድጋፍ ስለሚያስፈልገው የድጋፍ ያለህ ጩኸት በመጪህ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ መዳሁን ሲያበቃ አፉ ሊፈታለት ይችል ይሆናል፡፡ ወይም በዚያው የማይናገር ልሳኑ የተሰጋ በሶስት በላ (በሶስት ሃሳብ የሚመራ) ሆኖ ይጠፋል፡፡ ምክንያቱም የጡት አባቱ የሰጠው ተልእኮ መፈጸም አይችልም፡፡ ሲጀመር ባንዳ ድርጅት ስለህዝብ ህልውና ቦታ የለውም፡፡ ባንዳ ፊት ለፊት ጥቅም ማሳደድ እንጅ ራዕይ የለውም፡፡ ራእይ ቢኖረውማ እያንዳንዱ ካዋሳኑ ካለው የጡት ልጆች ጋር ሆኖ ውርስ ይጠይቅ ነበር፡፡ የጡት አባትም ውስሩን ይፈቅድለት ነበር፡፡ በምን ሁኔታ መጠየቅ እንዳለበት እንዳያውቅ ተደርጎ የተሰየመ በመሆኑ ቆሞ ቀር ባንዳ ነው፡፡ ሁሉም የህዝብ አይደለም የቤተሰብ መሰረት የሌላቸው ጋጠ ወጥ አባላት የተሞሉ ስለሆነ ምንም ማሰቢያ የላቸውም፡፡ ወላ እህት ወላ አጋር ብትለኝ ምንም ምንም የላቸውም፡፡ ድግስ ቃራሚ ሆነው የሚነገዋለሉ አሳፋሪዎች ናቸው፡፡ ተቃዋሚ ወይም ተፈካካሪ ነኝ ብለው ለ50 አመታት የዘላበዱት ደግሞ ምንም ርእዮተ አለም ሰነድ ሳይኖራቸው ሲነቀዋለሉ የቆዩ አሾአፊ ባዶ ቤት ናቸው፡፡ ሀገር የሚመሩበት ፖሊሲ ሳይኖራቸው የፖለቲካ ፓርቲ ነን ብሎ እንደተራበ አራዊት ማግሳት በህዝብ ላይ መዝዝ ማምጣት ነው፡፡

 5. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሞቱትን ወገኖች ብሄር የደረደረው ኦሮሞ ሁሉ ገዳይ እንደሆነ ነገር ወሬ የምታራግቡና civil war የምትቀሰቅሱትን አፍ ለማዘጋት ነው:: አሁን ጎራው ለይቷል በአንድ ቡድን ህውሀትና የጃዋር ፀረ ኢትዮጵያ መንጋ ተሰልፏል::በሌላው ኢትዮጵያዊው የዐቢይ ቡድን አለ:: ጨው ለራስህ (ሽ) ጣፍጥ ይላል አበው ሲተርቱ:: አሁን ዐቢይን ማብጠልጠል
  የፀረ ኢትዮጵያ መንጋውን ሀይል ማጠናከር ብቻ ነው:: ለትችና ወቀሳ የፖለቲካ ቅምጥልነት ጊዜ ላይ አይደለንም sorry. ጉልበት ያለው በጉልበቱ በገንዘቡ የድጋፍ ሀሳብ በማሰባሰብ አማራጭ የሌለው ኢትዮጵያዊነት ከዐቢይ አሕመድ ጋር መሰለፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው:: ህውሀት ለአማራው ዐቢይን ኦነግ ለኦሮሞው ሀበሻና ነፍጠኛ ነው የሚለው ታፔላ ተሳክቶላታል:: ኢትዮጵያውያንም እንደ ከብት ከመነዳትና ለተቆፈረላቸው ጉድጏድ ከመግባት ቆም ብለው ይመርምሩ::

 6. This speech was warning by Oromo extremist symphatizer directed at reporters journalists not to report the truth about the dead people’s identity to international medias, locals know the truth .

  Few of those ones who the family members picked their dead bodies up, took home to bury avoiding paying bills for medical examiner ambulance or other medical costs were the ones reported as 50 dead Oromos.

  Those bodies picked up with public or Street cleaning took to where paperwork about their identities was documented are not called Oromos.

  Many others who perished are not even counted in his report.

  If PM Abiy was not a fraud about the so called reform and if he sides with the truth he should make available to the free journalists presses Or other concerned bodies the addresses of the victims/family members , the victims full name , the victims age and maybe after that their ethnicity too, all these should have been done for each of the people he reported dead now .It cannot be difficult for him to know their name age addresses while he knew their ethnicity.

  His job as a PM now was to make sure information is available for journalists not to be INSA agent info distorter just like old times, old habits die hard.

  Even some picture and their life story would be appropriate for reporters journalists to have access to so they can report the legacies of those lost, reporters should have free access to interview by contacting the families at whichever shelter they are hiding in since their homes were burnt.

  How many homes burnt should be reported too, along with to who the homes burnt belonged to should be reported by the free press. All Amaras that got video camera should try to document the victims story , victims both who died or are still alive deserve their stories heard by the world more than they need material help or food.

 7. ሬሣዉ አንቺ በቁም የሞትሽዉንና ከሩቅ ሁነሽ የምታስገድይዉን አሸባሪ ነፍጠኛ ሳይጨምር ነዉ። የተቆጠረዉ ባንቺ ቤንዚን አርከፍካፊነትና እሳት ጫሪነት በግፍ የተገደሉት ንጹህ ኢትዮጵያዉያን ሬሣ ብቻ ነዉ።

 8. Dear Meskerem, I think you have to come to your mind keeping away your hatreds on Oromo. You live in Oromia with oromos. Can you please confirm who instigated the conflict in Adama, Bishoftu, Mojo, Dukam, Dodola, etc. The Qeerroos came out to the street without any weapon as their Objective is to stand by Jawar. While the peaceful demonstration is going on, already prepared mercenary Neftegnas who were armed including knives and guns came to counteract the peaceful demonstrators. Eye witnesses tells you that Amharic speakers came to disperse the Qeerro and other peaceful demonstrators in the towns mentioned above. The Amharic speakers started firing life bullets and declared war on the demonstrators. Unarmed and unwarned peaceful demonstrators and any other Afan Oromo speakers were targeted by these armed groups. The demonstrators have to face such challenges they have never expected. Many of them injured and significant number also killed on the street, public property destroyed by the organized gangsters and lotted. Knowing this fact, I don’t understand why the Neftegan elements always side the perpetrators and condemn the innocent Qeerros and oromo people for anything that happens. I pray for you to come to your conscience and have a logical thinking instead of blind hatred. Hatred will bring counter hatred and will lead to another killings of innocent people. We have to come to our logical thinking and be able to say this group did wrong and ask the government to take appropriate action on the wrong doers. Simply supporting the organized looters and bandits will be counterproductive as everybody knows who did what.

  • ተወው ወንድሜ፣ የምንሊክን ዘመን ለመመለስ ከሚያልሙ የነፍጠኛ ቅሪቶች አመንክዮአዊ ውይይት እንዴት ትጠብቃለህ? These are Abysso neo-fascists, who are drumming up anti-Oromo and anti-federalism vile propaganda in unison hoping that they would turn around the wheels of history! My conclusion: ነፍጠኛን የሚገባው እርሳስ ብቻ ነው!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.