የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ

1 min read
2

የኢ.ፌ.ዲ.ሪመከላከያ ሚኒስተር ዘመናዊ የሰራዊት ግንባታ ሂደት የሚጠይቀውን የዘመኑን የወታደራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እየሰራ ነው፤ በመሆኑም የሁሉንም ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ወጣቶችን ወደ ተቋሙ በማምጣት ተኪ የመከላከያ ሰራዊት ማፍራት ይፈለጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ብቃት ያላቸው ወጣቶችን ከህብረተሰቡ በፍቃደኝነት መልምሎ በወታደርነት ሙያ በማሰልጠን በልዩ ልዩ ሙያዎችመመደብ ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመመልመያ መስፈርቶች መሰረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

1. ፖለቲካዊ መስፈርት
1.1. የኢ.ፌ.ዲ.ሪን ህገ-መንግስትን የሚቀበሉ፤
1.2. ሀገሪቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በፅናት ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑ፤
1.3. ከማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አስተሳሰብ ወገናዊነት ነፃ የሆኑ፣የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆኖ ለማገልገል ሙሉ ፈቃደኛ የሆኑ፤
1.4. በኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት የሚያምኑ፤
1.5. ከአሁን በፊት በመከላከያ ፣ በፖሊስና የተለያዩ ድርጅቶች አባል ያልነበሩ፤
1.6. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሰው የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው፤
1.7. ዜግነት ኢትዮዽያዊ፤
1.8. በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያላቸውና ከተለያዩ አጉል ሱሶች የራቁ፤
1.9. በሚመለመሉበት አካባቢ ቢያንስ ከሁለት አመት በላይ በኗሪነት የታወቁ፤ ከላይ ለተጠቀሱት ፖለቲካዊ መስፈርቶች ከቀበሌ መስተዳድርና ከፖሊስ የፅሁፍ ማስረጃ መምጣት የሚችሉ፤

2.አካላዊ ብቃት

2.1. የተስተካከለ ቁመናና ሙሉ ጤነኛ የሆኑ፤
2.2. የተሟላ የሰውነት ህዋሶች ያላቸው፤
2.3. ቁመት ለወንድ 1.60 ሳ/ሜትር ፣ ለሴት 1.55 ሳ/ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
2.4.ክብደት ለወንድ ከ50-75 ኪሎ ግራም ፣ለሴት ከ45-66 ኪሎ ግራም የሆኑ፤
2.5. ዕድሜ ከ18-22 ዓመት የሆኑ፤

3.የፍቃደኝነት ሁኔታ

3.1. በውትድርና ሙያ መከላከያ በሚያሰማራው ቦታ ሁሉ በታማኝነት ለመስራት ፍቃደኛ የሆኑ፤
3.2. መከላከያ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆኑ፤
3.3. በመከላከያ ህግና ደንብ መሰረት ለ 7 አመት ውል የሚፈፅሙ፤
3.4. በመከላያ ህግና ደንብ መሠረት መብትና ግዴታቸውን አውቀውየሚሰሩ፤
3.5. ትዳር ያልመሰረቱና ልጅ ያልወለዱ፤
3.6. ፆታ አይለይም፤

4. የትምህርት ሁኔታ፤ የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቁእና የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ካርድ ማቅረብ የሚችሉ።

የምዝገባ ቦታና ጊዜ

☞ ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች ጦር ሃይሎች ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ሃይል ግቢ በብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ፥
☞ ለክልል ተመዝጋቢዎች በአካባቢያችሁ ባሉ የቀበሌ መስተዳድርና በወረዳ አስተዳደር ፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
☞ የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ይሆናል::
የኢፌዲሪመከላከያሚኒስቴር

2.ለዕጩ መኮንንነት ለሚመለመሉ የመልመያ መስፈርት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪመከላከያ ሚኒስቴር ዘመናዊ የሰራዊት ግንባታ ሂደት የሚጠይቀውን የወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሚያስችል የአመራር ብቃትና ክህሎትን ለማዳበር እየሰራ ይገኛል፤ ስለሆነም የሁሉንም ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ የሰው ሃይል ወደ ተቋሙ በማምጣት ተኪ አመራር ለማፍራት ጥረት እያደረገ ነው፤ ከዚህ በታች የተገለፁትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ወጣቶችን ከህብረተሰቡ በፍቃደኝነት በመመልመልበዕጩ መኮንንነት በሜ/ጀኔራል ሃየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ በረጅም ኮርስ በድግሪ መርሃ ግብር በወታደራዊ አመራርነት ሙያ ያሰለጥናል፤ በም/መ/አለቃነት ማዕረግ አስመርቆም በአመራርነት መመደብ ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመመልመያ መስፈርቶች መሰረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

ከህብረተሰብ ለዕጩ መኮንንነት ለሚመለመሉ የመግቢያ መስፈርት (Admission Criteria)
☞ ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ፤
☞ ዕድሜ ከ18 እስከ 24 አመት የሆናቸው፤
☞ የትዳር ሁኔታ ያላገቡ፤
☞ ልጅ ያልወለዱ፤
☞ ፆታ አይለይም፤
የትምህርት ደረጃ እና ተፈላጊ ብቃት
☞ 12ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁና የወቅቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤
☞ የድግሪ ምሩቅ ለሆኑ እውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተመረቁ፤
☞ የዲፕሎማ ምሩቅ ከሆኑ Level – 4 (Advanced Diploma) ሆኖ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የተመረቁ፤
Level – 3 ለሆኑ COC ሰርቲፊኬት ያላቸው፤
☞ በሁሉም የትምርትና ስልጠና ፕሮግራም ሴት ዕጩ መኮንኖች ይበረታታሉ።

ተፈላጊ ቁመት እና ክብደት

☞ ቁመት ለወንድ ከ1.60 ሴ.ሜ በላይ /ለሴት 1.55 ሴ.ሜ በላይ፤
☞ ከብደት ለወንድ ከ50 ኪ.ግ በላይ /ለሴት ከ 45 ኪ.ግ በላይ፤
ተፈላጊ ባህሪና አስተሳሰብ
☞ በውትድርና ሙያ ሀገራቸውን ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፤
☞ ለ3 ዓመት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በመኮንንነት ለ10 ዓመት ለማገልገል የኮንትራትውል የሚፈፅሙ፤
☞ በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የሚያመኑ፤
☞ የጤና ምርመራ ለማደረግ ፍቃደኛ የሆኑ እና የሚሰጠውን ትምህርትና ስልጠና ለመከታተል የተሟላ ጤንነትና ሰነ-ልቦናዊ ዝግጁነት ያላቸው፤
☞ ከሚኖርበት ቀበሌ የማንነት መታወቂያ ያላቸው፤
☞ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው ከወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ማሰረጃ ማቅረበ የሚችሉ፤
☞ ሙሉ ጤነኛ የሆኑና ከማንኛውም ሱስ ነፃ የሆኑ፤
☞ በአካባቢው ማህበረሰብ የተመሰገነ ባሀሪ እና ስነ-ምግባር ያላቸው፤
☞ ከአሁን በፊት የመከላከያ ወይም የፖሊስ ሰራዊት አባል ሆነው ያላገለገሉ፤
☞ የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ ወደ ወታደራዊ አካዳሚ ሲገቡ የ 11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ሰርተፍኬት መያዝ አለባቸው፤
☞ የዲግሪ ተመራቂዎች ኦሪጅናል ቴምፖራሪና ስቱዴንት ኮፒ (Student copy) መያዝ አለባቸው፤
☞ ለLevel ተመራቂዎች የትምህርት ማሰረጃና የ CoC ሰርተፍኬት መያዝ አለባቸው፤
☞ ወደ ወታደራዊ አካዳሚ ሲገቡ 4 (Passport size) ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ አለባቸው፤

የምዝገባ ቦታና ጊዜ

☞ ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች ጦር ሃይሎች ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ሃይል ግቢ በብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን፤
☞ ለክልል ተመዝጋቢዎች በክልል አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤትና በዞን አስተዳደር ፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
☞ የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ይሆናል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር

3. ለአየር ሃይል አብራሪነት እና ቴክኒሻንነት የሚመለመሉ

ኢትዮጵያ ሃገራችን ጀግኖች እና ብቁ ፓይለቶችን በማፍራት ከፍ ያለ ታሪክ ባቤት ነች:: እያፈራችም ትገኛለች፤ በአሁኑ ወቅትም አለም የደረሰበትን ሳይንስና የቴክኖሎጂ ደረጃ ለመድረስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ሃይል እውቅ ፓየለቶችን ለማፍራት እየሰራ ይገኛል፤ ስለሆነም በአብራሪነት ሙያና በአየር ሃይል ቴክኒሻንነት ብቃት ያላቸው ወጣቶችን ከህብረተሰቡ መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል:: ስለሆነም የጀግናው አየር ሃይላችን አባል ለመሆን የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የመልመያ መስፈርት መሰረት ለአየር ሃይል አብራሪነትና ቴክኒሻንነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

ተፈላጊ ችሎታ:- ለአየር ሃይል አብራሪነት እና ቴክኒሻንነት የሚመለመሉ ተ/ቁ የሚፈለገው የሙያ ዓይነት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ (የሙያ ማስረጃ)

ለአየር ሃይል አብራሪነት እና ቴክኒሻንነት

☞ በ2011 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውጤታቸው ዩንቨርሲቲ ማለፊያ ነጥብ ያላቸው፤
☞ በ2010 ዓ.ም 2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ውጤታቸው ዩንቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ የሆነ ለወንድ 354′ ለሴት 340′ ለታዳጊና ለአርብቶ አደር አካባቢ ለወንድ 340′ ለሴት 335 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያላቸው፤
☞ በ2008 እና 2009 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ በሂሳብ’ በፊዚክስ ና በእንግሊዘኛ B እና ካዛ በላይ ያላቸው፤
☞ የኮሌጅ /ዩንቨርሲቲ/ተማሪ የሆኑና ከሚማሩበት ተÌም የመጨረሻ ዓመት የውጤት ሪፖርቱን ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱበትን ኦርጅናል ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ የከፍተኛ ትምህርት ተÌም የመጀመሪያ ድግሪ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ያላቸው እና ዕድሜያቸው ከ 22 አመት ያልበለጠ፤
☞ የ2011 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ለመደበኛ ስልጠና የሚገቡ በትምህርት ሚኒስቴር ቴክኒክና ሙያ በሚያወጣው መስፈርት ሆኖ በእንግሊዝኛ ፣በሒሳብ ፣ በፊዚክስ ትምህርቶች C እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
☞ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አጠናቀው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑና የወቅቱ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤
☞ 10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በ2010 ዓ/ም እና በ2011 ዓ/ም ያጠናቀቁ’
☞ ተመልማዮች የአካል ብቃታቸውና እና ጤንነታቸው የተረጋገጠ ሆኖ የጤና ምርመራ ወስዶ ማለፍ የሚችሉ፤
☞ የአየር ሃይል ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የመግቢ ፈተና ወስዶ ማለፍ የሚችሉ፤
☞ 12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ተመልማዮች የ2010 ዓ/ም እና 2011 ዓ/ም እና ለሌቭል 4 የቴክኒክና ያ መግቢያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት ማሟላት የሚችሉ፤

ለአየር ሃይል አብራሪነትም ሆነ በቴክኒሻንነት የሚመዘገቡ ከዚህ በታች የተገለፁትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው

☞ ዕድሜ ከ18-22 ዓመት የሆኑ ቁመት 1.68 – 1.98 ሜትር የሆኑ፤
☞ ዜግነት ኢትዮጵያዊ፤
☞ ሙሉ ጤንነት ያለውና ስልጠናው የሚጠይቀውን የህክምና ምርመራ ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆኑ፤
☞ ከወንጀል ድርጊት ነፃ ለመሆናቸው ከትውልድ ቦታቸው/ከሚኖሩበት አካባቢ/ማስረጃ ማቀረብ የሚችሉ፤
☞ ከዚህ በፊት በማንኛውም በውትድርና /በፖሊስነት/ተቀጥረው ያልሰሩ፤
☞ በውትድርና ሙያ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፤
☞ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት የሚቀበሉ፤
☞ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑ፤
☞ ትዳር ያልመሰረቱ እና ልጅ ያልወለዱ፤
☞ ፆታ አይለይም፤
☞ ሴቶች ይበረታታሉ::
☞ የ 8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መልቀቂያ ካርድ’የሁለኛ ደረጃ መልቀቂያ /ማትሪክ/ ፈተና ውጤትና የፕሪፓራቶሪ ፈተና ውጤት ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ ተመዝጋቢዎች ወደ ምዝገባ ቦታ ሲመጡ 2/ሁለት/ ወቅታዊ ፎቶግራፍ እና ኦርጅናል የትምህርት ማሰረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዞ መምጣት ይጠበቅባቸዋል::
☞ የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ይሆናል::

የምዝገባ ቦታና ጊዜ
☞ ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች ጦር ሃይሎች ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ሃይል ግቢ ብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል ማደ/ማስ/ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን፤
☞ ለክልል ተመዝጋቢዎች በክልል አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤትና በዞን አስተዳደርና ፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
☞ የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ይሆናል::
የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር፤

4.ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመልመያ መስፈርት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪመከላከያ ሚኒስቴር ዘመናዊ የሰራዊት ግንባታ ሂደት የሚጠይቀውን የወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚያስችል ብቃትና ክህሎትን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ የሁሉንም ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ አዳዲስ ወጣት ሞያተኞችን በተለያዩ የሞያ ዘርፍ መልምሎ ወደ ተቋሙ ማምጣት ይፈልጋል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ልዩ ልዩ ሞያተኞችን ከህብረተሰቡ በፍቃደኝነት መልምሎ በማሰልጠን አስመርቆ በወታደርነት በተለያዩ ሞያዎች መመደብ ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመመልመያ መስፈርቶች መሰረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

4.1 ለሎጅስቲክ ስራዎች የሚመለመሉ

ተ/ቁ የሚፈለገው የሙያ ዓይነት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ (የሙያ ማስረጃ)

1 አውቶ መካኒክ ሙያ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ መካኒክ’በአውቶ ኤሌክትሪክ’በጀኔራል መካኒክ’በሌቭል 3፣ 4 እና 5 ተመርቀው የብቃት ማረጋጋጫ ሲኦሲ(COC) ሰርቲፊኬት ያላቸው፤
2 አውቶ ኤሌክትሪክ ሙያ
3 ጀነራል መካኒክ ሙያ
4 አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪግ ሙያ በአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፤ በመካኒካል ኢንጅነሪግ (በሞተር ቬሄክል፣በፖወር ትሬን) የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፤
5 የዳቦ ማሽንና የኤሌክተሪክ ምድጃዎች ጥገና ሙያተኛ በኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው’እና በሌቭል 3 ፣ 4 እና 5 ተመርቀው የብቃት ማረጋጋጫ ሲኦሲ(COC) ሰርቲፊኬት ያላቸው’
6 የመለዋወጫና መስሪያ ዕቃ ግ/ቤት ሙያ በሎጀስቲክስ ሰፕላይ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው እና’ ሌቭል 3 ፣ 4 እና 5 ያላቸው፤

4.2 ለተለያዩ ክፍሎች በፋይናንስ እና ለሰው ሃብት ስራዎች የሚመለመሉ

ተ/ቁ የሚፈለገው የሙያ ዓይነት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ (የሙያ ማስረጃ)

1 በፐርቸዚንግ ሳፕላይ ማኔጅመንት በአካውንቲንግ፤ በፐርቼዚንግ፤ በቢዝነስ አድሚኒስትሬረሽን፤ በሳፕላይ ማናጅመንት፤ በሰው ሃይል አስተዳደር እና በማናጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው፤ እንዲሁም ድፕሎማ ያላቸው፣ በሌቭል 1′ 2 ፣ 3 እና 4 ተመርቀው (COC) ሰርቲፊኬት ያላቸው፤
2 ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን ሙያ
3 በአካውንቲግና በፋይናንስ ሙያ
4 በሎጅስቲክና ሳፕላይ ማኔጅመንት፣በግዥና አቅርቦት እና በማኔጅመንት ሙያ
5 የሰው ሀብት ባለሙያ  በሰው ሃይል አስተዳደር በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤
☞ በሰው ሃይል አስተዳደር በድፕሎማ የተመረቁ’
☞ በሌቭል 3 እና 4 የተመረቁ፤
6 ሴክሬተሪ
7 ኤሌክትሪሻን በኤሌክትሪክ ሲቲ’በጀኔሬተር ኦፕሬተርነትና ጥገና’ በቧንቧ ጥገና በድፕሎማ የተመረቁ እና በሌቭል 3 እና 4 የተመረቁና COC ሰርቲፊኬት ያላቸው፤

8 ጀኔሬተር ኦፕሬተር ሙያ
9 ቧንቧ ሰራተኛ

4.3 ለሚድያና ለአይቲ ሙያዎች የሚመለመሉ

ተ/ቁ የሚፈለገው የሙያ ዓይነት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ (የሙያ ማስረጃ)

1 ሪፖርተር በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን በቋንቋና ስነ-ፅሁፍ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው፤

2 ለፅሁፍ ዝግጅት ሙያዎች  ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በስነ-ፅሁፍ ወይም በማስ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሆኖ በፅሁፍ ዝግጅት በቂ ልምድ ያላቸው፤
3 የሚዲያ ቴክኒክ ሙያዎች  ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነትና በአይሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፤
☞ በኤሌክትሪኒክስ የኮሌጅ ዲፕሎማ ኑሯቸው ቪድዮና ፎቶ ኤዲተር ፣ በካሜራ ማን ፣ በበአርካይቭ አያያዝ እና የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሙያ ያላቸው፤
4 የግራፊክስ ባለሙያ በሚዲያ ዌብ ዲዛይነር በመልቲ ሚዲያ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው፤
5 የፎቶ ግራፍ ሙያተኛ  በፎቶ ግራፍ ሙያ በድፕሎማ የተመረቁ ወይም በሌቭል 3 እና 4 የተመረቁና COC ሰርቲፊኬት ያላቸው፤

6 ለሙዚቃ ሙያዎች  ከታወቀ ኮሌጅ በኤሌክትሪኒክስ የኮሌጅ ድፕሎማና ከዚያ በላይ ያላቸው ወይም
☞ ከያሬድ ት/ቤት በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት ፣ በተዋዛዋዥነት ፣ በሙዚቃ መሳሪያ ጠጋኝነት እና በድምፃዊነት 10ኛ ክፍል አጠናቀው ከ3 ዓመት በላይ አገልግሎትና የስራ ልምድ ያላቸው፤
7 የአይቲ ባለሙያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅና በአይሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ወይም
በአይቲ በድፕሎማ የተመረቁ’ወይም በሌቭል 3 እና 4 የተመረቁና COC ሰርቲፊኬት ያላቸው

ዕድሜን በተመለከተ

ለሎጀስቲክ ሞያተኞች’ለሚድያና አይቲ ሞያተኞች’ለፋይናንስ ነክና ለሰው ሃብት ሞያተኞች
☞ ከደረጃ(Level) 1 እስከ 5 እና ድፕሎማ ያለው ከ18 ዓመት እስከ 24 ዓመት ድረስ
☞ ለዲግሪ ከ18 ዓመት እስከ 26 ዓመት ድረስ ይሆናል::

4.4 በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለኢንጅነሪንግ እና ለጤና ሙያዎች የሚመለመሉ ተ/ቁ የሚፈለገው የሙያ ዓይነት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና መመዘኛዎች (የሙያ ማስረጃ)

ለኢንጅነሪንግ እና ለጤና ሳይንስ ሙያዎች

የትምህርት መስፈርት:-
☞ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑ፤
☞ ለወንዶች’ለሴቶች እና ከታዳጊ ክልሎች ለሚመጡ አመልካቾች በ2011 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ውጤታቸው 140 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
☞ ለሁሉም አመልካቾች የ10ኛ ክፍል ውጤት በእንግሊዘኛ’በሂሳብ’በፊዚክስና በኬሚስትሪ C እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
☞ የዕድሜ ጣሪያው እንደተቀመጠ ሆኖ የመጀመሪያ ዲግሪ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተማሩ እና በእንጂነሪንግ ፊልዶች እንደ አዲስ መማር የሚፈልጉ፤
☞ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል እንዲሁም ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የመሰናዶ ትምህርት ውጤት ትራንስክሪብት ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በ2010 ወይም በ2011 ዓ.ም በቴክኒክና ሙያ Level 4 በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ የተመረቁ እና የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC)ሰርቲፊኬት ያላቸው፤

መመዘኛዎች:-
☞ ዕድሜ ከ18-22፤
☞ ህገ መንግስቱን የሚያምኑ፤
☞ ከወንጀል ድርጊት ነፃ ለመሆኑ ከፖሊስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
☞ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑ፤
☞ ትዳር ያልመሰረቱ እና ልጅ ያልወለዱ፤
☞ ወታደር ለመሆን ሙሉ ፈቃደኛ የሆኑ፤
☞ ሙሉ ጤነኛ የሆኑ“ ከተለያዩ አጉል ሱሶች የጸዱ፤
☞ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው እና በቀበሌው ከ2 ዓመት በላይ የኖሩ፤
☞ ዜግነት ኢትዮጵያዊ፤
☞ ፆታ አይለይም፤

በኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ስልጠና የሚሰጥባቸው የትኩረት መስኮች:-
i. ኤሮናቲካል ኢንጅነሪንግ፤
ii. አርማመንት ኢንጅነሪንግ፤
iii. ሞተር ቬይክል ኢንጂነሪንግ፤
iv. ፕሮዳክሽን ኢንጅነሪንግ፤
v. ሲቪልና ኮምባት ኢንጅነሪንግ፤
vi. ኮምፒውተርና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፤
vii. ኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ፤
viii. ኤሌክትሪካል ፓወር ኢንጂነሪንግ፤
ix. ሜታለርጂ እና ማቴሪያልስ ኢንጅነሪንግ፤
x. ኬሚካል ኢንጅነሪንግሲሆን፤
በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስልጠና የሚሰጥባቸው የትኩረት መስኮች:-
i. ፊዞትራፒ
ii. ነርስ
iii. ላብራቶሪ
iv. ኤችኦ/HO/
v. ፋርማሲ

የምዝገባ ቦታና ጊዜ

☞ ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች ጦር ሃይሎች ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ሃይል ግቢ ብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል ማደ/ማስ/ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን፤
☞ ለክልል ተመዝጋቢዎች በክልል አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤትና በዞን አስተዳደርና ፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
☞ የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ይሆናል::
የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር

በበለጠ በመከላከያ ድረ-ገፅ በመግባት ማየት ትችላላችሁ (www.fdremod.gov.et)