እባብ! – በላይነህ አባተ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

እባብ ምራቅ ተፍቶ ዛሬ እንደሰበከው፣
አማራ በሱ ቤት ሁለት መልክ አለው፣

በቁሙ ነፍጠኛ ሲሞት ወረሞ ነው፡፡
ያልበሰለ ቀርጮ እባቡ ጮርቃ ነው፣
ለሬሳ ዘር ሰጥቶ ወንጀል ሊሸፍን ነው፡፡

ስኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያ፣

ድሮም ሸፍጥ ነበር ዛሬም ትል አፈራ፣
ጩጨው በዘር በዘር ሲከፍል እሬሳ!

ደሞ ተብለጥልጦ ትኩረትን ሊያስቀይስ፣

ባህርዳር ነጎደ ጅሎችን ሊያናክስ፡፡

የታለልክ አማራ በዚህ እንጭጭ እባብ

እሳት ሆኖ ይፍጅህ ያያቶችህ ጥበብ!

ብልቷን አውጥቶ ተሚያኝካት አገር፣
ሱስ ያዘኝ እያለ አሞኘህ እንደ ጅል፡፡

በዱላ ደቁኖ በመለስ ቀስሶ፣
ሊበር ይችላል ወይ እባብ እርግብ ሆኖ?

ይሁዳን ተሙሴ እያመሳሰሉ፣
እነ ፕሮፌሰር ስንቱን መንጋ አስካዱ፡፡

አምልኩ ቢባሉ አንድ አምላክ አንድ እግዜር፣
ጥሪ ተቀብለው ተጆሮ ጠቢ ዛር፣
እጅ ወደ ላይ ሰቅለው ገቡ እንደ ምርኮ ጦር፡፡

በእንብልብልህ ተጓዝ ሲል የረገመውን፣
እንዴት ሰው ያመልካል ያሳተውን ሄዋን?

አምላክ ቀናተኛው እውነትን የሚወድ፣
ምነው አይቆጣ ምነው አይናደድ፣
ከሙሴ ወንበር ላይ ይሁዳን ስትጎልት፡፡

እየዬን ተውና መውቀስ የከዳህን፣
ቀበቶህን አጥብቅ የክብር ምንጭህን፡፡

ልትቆርጥ ስትማልል ተጊንጥ ተዘንዶ ማር፣
በምላሱ ወግቶ በመርዝ ይገልሃል ፡፡

ዘንዶ ሰው ይሆናል ብሎ ያመነን ሰው፣
እንኳንስ እባቡ አምላክም አይምረው፡፡

ከሃያ ዓመት በላይ የጨፈጨፋቸው፣
መንበር መወጣጫ እርካብ ያረጋቸው፣
ከምድር ሥጋቸው ከሰማይ ነፍሳቸው፣
ከችሎት ገትሮ ፍርድ ቅጣት ያሰጠው፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን ፍርዱን እስቲያገኘው፣
ትሰማኝ ተሆነ ጅልና ዘልዛላው፣
ተእባብ ሥር እንደ አፈር ወድቀህ የሰገድከው፣
ዳግም እንዳታመልክ በዛሩ በቆሌው፣
ይሰላ እንደሆነ ራስህን ውቀረው፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

One Response to  እባብ! – በላይነህ አባተ

  1. በትክክል ይህ እባብ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ ካለዉ ነፍጠኛ ጋር ይመሳሰላል።

    Avatar for እባቡ ነፍጠኛ

    እባቡ ነፍጠኛ
    November 4, 2019 at 10:17 am
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.