የጠቅላዩ (?) የድረሱልኝ ጩኸት (ዶ/ር መኮንን ብሩ)

1 min read

ሰሞኑን ብዙዎች ስለሀገርና ሕዝባቸዉ በመጨነቅ “አሁን ማድረግ ያለብን ምንድን ነዉ?” ሲሉ ይደመጣሉ። ትክክል ይመስሉኛል ,,,,, አዎን! አሁን ምን እናድርግ?…….ጥያቄዉ ግን በዚህ መቆም የሚችል አይመስለኝም። ምክንያቱም ከጠቅላዩ የዛሬዉ መግለጫ በስተጀርባ እኔን ጨምሮ ብዙዎች የሰሙት የድረሱልኝ ጩኸት “ለሰዉዬዉ ምን እናድርግላቸዉ?” የሚልን ጥያቄ ይዞ በመምጣት ዛሬ መልሱን መፈለግ የእኛ ዕዳ ሆኗል።

ዶ/ር አብይ አህመድን ያህል በፍቅር የሕዝብ ድጋፍ ሊያሰባስብ የቻለ መሬ በዘመኔ በየትኛዉም የመሬት ጠርዝ እንደነበር አላስታዉስም። በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ እንግሊዝ በጀርመን ልትወረር ስትልና በኃላም የእንግሊዝ ከተሞች የጀርመን አዉሮፕላኖች በሚጥሏቸዉ ቦንብ ሲደበደቡ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ቸርችል የነበራቸዉን ፍቅር በበለጠ የወያኔ በደል ለሃያ ሰባት ዓመታት ያንገሸገሸዉ ኢትዮጵያዊ ለዶ/ር አብይ ዘርግፎ ነበር። የዛሬ ሰባ አምስት ዓመታት ገደማ ቸርችል ሕዝባቸዉ ላይ የናዚ ቦንብ ሌት ተቀን እየዘነበ የሕዝባቸዉ መሪና ተስፋ መሆን ሲችሉ የእኛዉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ግን ላለፉት ጥቂት ወራት በጥቂት ወንጀለኞች ሴራ ተጠልፈዉ……ተጎሳቁለዉ ……ጥቁርቁር ብለዉ …….በሰዉ ልጅ እኩይ ባሕሪ አዝነዉ …….ተበሳጭተዉ …..ለወትሮዉ ደመቅመቅና ፈካ ብለዉ የምናያቸዉ ጎልማሳ የለበሱት ኮት ሳሞራ የለበሰዉ ይመስል ከትከሻቸዉ ላይ ሊወርድ ሲንሸራተት ተዘናግተዉ ለተመለከተ ሁሉ እኛ ብቻ ሳንሆን እሳቸዉም ቸርችልን እየፈለጉ መሆኑን በቀላሉ የሚረዳ ይመስለኛል። ስለዚህ ምናልባት ቸርችልን ልንሆንላቸዉ ባንችል ቸርችልን ማፋለጉ ሳይበጀን አይቀርም።

አቶ ታዬ ደንድኣ ከሁለት ቀናት በፊት የአንቦን ፀረ አብይ ሰልፍ አያይዘዉ እንደገለፁት፤ ጠማሪ ስዩም ተሾመም ያንን አስታኮ ሊያብራራ እንደሞከረዉ የጃዋር ቅጥረኛ ቄሮዎች (የኦሮሚያ ፖሊስ ጥቂት አባላትን ጨምሮ) የስዉር አደረጃጀትና እንቅስቃሴ ከጠቅላዩ ቸልተኛነት ጋር ተዳምሮ ነገሮችን በማወሳሰቡ ሰዉዬውን አስደንግጧቸዋል። ማስደንገጥ ብቻ ሳይሆን አስፈርቷቸዋል። በነገራችን ላይ ታዬ ደንደኣም ሶስት አራት የሚሆኑ በጥፋት መዋቅሩ ዉስጥ የነበሩ በማለት ከአምቦ ልሰልፍ ጋር በማያያዝ ነገሩን በጣም አሳንሶ ማየቱ ለምን እንደሆን ባላዉቅም የአምቦን ጨምሮ በርካታ የኦሮሚያና አማራ ከተሞች ዉስጥ በቄሮ ስም ኦዴፓ አደራጅቷቸዉ ከነበሩ በርካታ ተወርዋሪ አመፅ ቀስቃሾች ዉስጥ ቢያንስ ከሁለት መቶ በላይ ስልካቸዉን በተጠንቀቅ ይዘዉ የሚጠብቁ የጅዋር ምልምሎች አሉ። እንደ መረጃ ምንጬ አባባል ከዞንና ከወረዳ ባለስልጣናት ጀምሮ የፖሊስ አባላት የመከላከያ አባላት የፓርላማ አባላት በቆንፅላ ደረጃ በተለያየ ሀገር ያሉ አባላትን ያካትታል። እነኚህን አደገኛ የሚያደርጋቸዉ ጥቂቶቹ ከዶ/ር አብይ ጋር በጣም የቀረበ ግኑኝነት ያላቸዉ በመሆናቸዉ ነዉ። የዚህ ፁሑፍ አቅራቢ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣንና በጃዋር መዋቅር ዉስጥ ላይ ያሉ ጥቂት ተዋናዬችን ያዉቃል። ስለዚህ ይህን መረብ ለመበጣጠስ እኛ ኢትዮጵያዊያን ምን በማድረግ ሀገራችን እንታደግ የሚለዉ ነዉ አሁኑኑ መመለስ ያለበት ጥያቄ።

ምናልባት ሰዉየዉን መታደግ ጥሩ አማራጭ ላይሆን ይችላል…. የጃዋርን ሰንሰለት መበጣጠስ ግን አማራጭ አይኖረዉም።

2 Comments

 1. “ግጭቱን ስንመለከት…
  በእርስ በርስ ግጭት ተቧድነው ሰዎች”
  አንድ መንጋ ባልተዘጋጁ ግለሰቦች ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ግድያ … በዚህ መልክ መገለጹ፣ ሕዝብ በጠ/ሚ ላይ እምነት እንዲያጣ ያደርጋል።
  ጠቅላዩ፣ ስክሪን ላይ የሚያነቡትን ግሩም ስነ ጽሁፍ የራሳቸው ነው?
  ያምኑበታል?
  ይተገብሩታል?
  ብዙ ሰው የሚጠይቀው ጥያቄ ይመስለኛል።
  ከእንግዲህ የፈለጉትን ግሩም ንግግር ቢያደርጉ ሰው ከቁብ የሚቆጥርላቸው አይመስለኝም። ሰው የሚፈልገው ከጭካኔ ግድያ የሚታደገው መንግስት እንጂ እንደ ሃሳዊ ፓስተር ባዶ ሰላምና እርቅ የሚሰብክ አይደለም።
  ክቡር ጠ/ሚ
  የጨፍጫፊዎቹ ጦር የታወቀ ነው። ከርሶ ብሄር የተውጣጣ መንጋ ነው። ኣዛዡም የታወቀ አሸባሪ ነው። ሰለባዎች አንድ ቡድን ሳይሆን ግለሰቦችና የእምነት ተቋማት ናቸው።
  ፍላጎትን በኃይል መፈጸም ወይም ማስፈጸም የትግል ስልት ሊሆን ይችላል ፣ ፍላጎቴን ካልፈጸማችሁ ንጹሓን ሰዎችን እገድላለው፣ ወይም የእምነት ተቋማትን አጋያለሁ የሚል አጋሰስ ግን አሸባሪ ነው። እንደ አሸባሪም መስተናገድ ይኖርበታል። የጸረ ሽብር ህጉ ፣ ምናልባትም ለመጀመሪያ ግዜ መተግበር ያለበት አሁን ነው። መንግስትዎ ፣ በሰላም የሚንቀሳቀሰውን ፣ ባልደራስን በሚያሳድድበት ኃይሉ ፣ ይህን የለየለት የሽብር ቡድን ቢያሳድድና ህግ ፊት ሲያቀርብ ቢታይ ኖሮ ምንኛ በተከበሩ ነበር።
  ይህ ያቀበጡት ቄሮ የሚሰራውን ሥራ እየታዘብን ነው። ስብሰባ ሲበትን፣ መንገድ ሲዘጋ፣ ባንዲራ ሲቀድ፣ ሰው ሲደበድብ፣ ሲዝት፣ ሲፎክር የጸጥታ አስከባሪው ዝም ብሎ ይመለከታል፣ መንግስትም እንዳላየ ችላ ሲል ታዝበናል። ዛሬ እርሶ ላይ መድረሱ ሊገርሞት አይገባም። ነገ ቤተ መንግስት ድረስ ሆ ብሎ ገብቶ ማጅራቶን አንቆ እንደሚደፋዎት አይጠራጠሩ።
  ስለዚህ ከቻሉ፣ አፋጣኝና የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ይውሰዱ።
  ካልቻሉ ወይም አቅሙ ከሌሎት ምስክኑን ህዝብ ያሳውቁትና ቄሮን ከነአዛዡ ልክ ያስገባው።
  በተረፈ ቸርችና የመንግስት ቢሮ ለየቅል ነው። የቄሳርን ለቄሳር ይላል ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.