በገሀድ 23ሺ የኮንዶሚኒየም ቤት ዝርፊያ ??? ተረኝነት !!!

1 min read

-ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ሁለት ቢሊየን ብር ተመድቧል
-ሀገር ውስጥ የሌሉም ለካሳ ቤት ደርሷቸዋል

ዋዜማ ራዲዮ- በአዲስ አበባ እና ዳርቻዎቿ በልማት ምክንያት ተነስተዋል ለተባሉ አርሶ አደር አባወራዎች : ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በሚስጥር በወጣ እጣ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ከተሰሩ የጋራ መኖርያ ቤቶች (ኮንደሚኒየሞች) 23 ሺዎቹ መሰጠታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ቤቶቹ ከተሰጣቸው ግለሰቦች አረጋግጣለች። በእጣ የተከፋፈሉት የጋራ መኖርያ ኮንደሚኒየሞች ኮዬ ፈጬ : ቱሉዲምቱ እና ካራ ቆሬ የሚገኙ ናቸው።
በዋናነት የተከፋፈሉት የጋራ መኖርያ ቤቶች ያሉት ኮዬ ፈጬ ሲሆን ካራ ቆሬ ከተገነቡት ውስጥ ደግሞ በረከት : ፋኑኤል : ወታደር ሰፈር እና ጀሞ የሚባሉ ሰፈሮች የተሰሩ የጋራ መኖርያ ቤቶች ተከፋፍለዋል።በባለ እድለኞች እየተኖረበት ካለው ከቱሉዲምቱ ሳይት ደግሞ በመጠባበቂያነት የተያዙ ቤቶችም እጣ እንደወጣባቸው ሰምተናል።

የእጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት የሚሊኒየም አዳራሹ ስነ ስርአት ተሰርዞ አሁን ላይ እጣ የማውጣት ስነ ስርአቱ በሚስጥር መከናወኑን ተገንዝበናል።ከሰሞኑም ቤቱ በእጣ የተሰጣቸው ግለሰቦች በየሳይቱ እየሄዱ የደረሳቸውን ብሎኮች እያዩ እንደሆነም ማረጋገጥ ችለናል።ባለ እጣዎቹም ባለ ስንት መኝታ ቤት? የት ሳይት? ቤት እንደደረቸሳውም አውቀዋል።

የልማት ተነሽ ለተባሉት ለአባወራዎች ባለሶስት መኝታ ቤት የደረሳቸው ሲሆን ለልጅና ልጅ ልጆቻቸው ደግሞ እንደ እድላቸው ባለ ሁለትና ባለ አንድ ደርሷቸዋል።
የጋራ መኖርያ ቤት ለተሰጣቸው አርሶ አደር : ልጅና የልጅ ልጆቻቸው የተሰጣቸውን ቤት ለመኖርያ ዝግጁ አድርገው እንዲያጠናቅቁ ለማድረግም ሁለት ቢሊየን ብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መድቧል። በዚህ ገንዘብ ራሱ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛ ቀጥሮ ቤቱን ያስጨርስ ወይስ ለቤቱ እድለኞች ገንዘቡ ተተምኖ እንዲሰጣቸው ይታሰብ አይታሰብ ግን ማወቅ አልቻልንም።

ሆኖም የቤቱ ክፍፍል ላይ አሁንም ከፍተኛ ችግሮች መከሰታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ከታማኝ ምንጮቿ መረዳት ችላለች።
በመጀመርያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለልማት ተነሽ አርሶ አደሮች በምትኩ የጋራ መኖርያ ቤት ይሰጥ ብሎ ባለፈው አመት ሲወስን ኮንደሚኒየም የሚሰጠው ለልማት ተነሽ አባወራ ብቻ እንዲሆን ነበር የደመደመው።

አሁን ግን ከካቢኔ ውሳኔው ውጭ ከልማት ተነሽ አርሶ አደሮች በተጨማሪ የትኛውም ያህል ቁጥር ያላቸው ልጆች ቢኖራቸው የጋራ መኖርያ ቤት ለልጆቻቸውም ተሰጥቷል ሲያልፍም  ለልጅ ልጆቻቸውም እንዲሰጥ ተደርጓል። በምን መነሻ ካቢኔው መጀመርያ የወሰነው ውሳኔ እንደተቀለበሰ ግን አልታወቀም።

በሌላ በኩል በካሳ መልክ የጋራ መኖርያ ቤት ለማግኘት የልማት ተነሽ የተባሉ አርሶ አደሮች የእርሻ ቦታቸው ላይ ይሰሩ በነበረበት ወቅት ግብር የከፈሉበት ደረሰኝ : ያለፉትን ጊዜያት የተደረጉ ምርጫዎችን በዚያው ቦታ ለመምረጣቸው ማረጋገጫ መረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም በነበሩበት አካባቢ ያሉ ኮሚቴዎች እንዲመሰክሩላቸውም ይጠበቃል። ሆኖም ከነዚህ መመዘኛዎች ውጭ በርካታ ሰዎች የጋራ መኖርያ ቤት ማግኘት ችለዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ይኖሩ የነበሩና አርሶአደርም የአርሶ አደር ልጅ ያልነበሩ ሰዎችም የጋራ መኖርያ ቤት ተሰጥቷቸዋል።

በካራ ቆሬ አካባቢ ብቻ ሰላሳ የጋራ መኖርያ ቤቶች ያለ አግባብ ተሰጥተዋል።በኮዬ ፈጬ ሳይት ከተሰሩ ቤቶች መካከልም ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ ለቆጣቢ እድለኞች በእጣ ወጥተው የነበሩ ቤቶችም አሁን ራሳቸው ቤቶቹ ተደርበው የልማት ተነሽ ለተባሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው በእጣ ደርሷቸዋል። በአስገራሚ ሁኔታም በአካል ሀገር ውስጥ የሌሉም ሰዎች እንዲሁ የጋራ መኖርያ ቤቶቹ ደርሷቸዋል።

ኮዬ ፈጩ ያሉት የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ከወጣባቸው በሁዋላ የኦሮሞ መብት ተከራካሪ ነን የሚሉ ግለሰቦች ባስነሱት አመጽ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ወሰን አከላለል ጥናት እስኪጠናቀቅ እንዳይተላለፍ መታገዱ ይታወሳል። ከ1997 አ.ም ጀምሮ ቤቶቹን የቆጠቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ቤቶቹን ለማግኘት እየተጠባበቁ ነበር።
ከሁለት ቀናት በፊት የኣአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሀያ ሺህ የጋራ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መዘጋጀቱን ምክትል ከንቲና ታከለ ዑማ ይፋ አድርገዋል። [ዋዜማ ራዲዮ]

7 Comments

 1. Kenezih asmesay leboch fiteh metebek mognenet new
  They are working only for the benefit of their people not for the benefit of the addis ababa residents
  Gena ekidachew bitay kezih yebelete zegnagn sira liseru yetezegaju nachew
  They pretend to be a born again Christian but …..
  Better expect from God
  Pray that’s all

  • Why should your ‘Addis Abebans’ be previleged over those farmers who lost their whole livelyhood? You don’t need to say it – we know. You mean the ‘Addis Abebans’ are 1st class citizens for whom 60% of the country’s national budget should be allocated. The Oromos on the periphery of the city, on the other hand, are just unwanted subjects, and can be freely expropriated and evicted from their ancestral homesteads at will. Right?

 2. These people who were awarded condos were not farmers who lost lands to development, they are Oromo politicians ODP CADRES and OLF members who were based in Eritrea which Abiy promised to give them housing condos in Addis Ababa if they come back to Ethiopia, they did come and no housing was readily available as promised , no housing provided per the deal so instead ABIY GAVE BLIND EYE letting them go at it on many bank robberies in the country just for the meantime to cover their hotel costs and hopefully now open businesses with the remaining money from the robberies to support themselves.

  They robbed all those Banks and they might continue to rob since they got no skills in business to generate income , very likely they rob Addis Ababa people businesses or residences.Hopefully they don’t rob anymore , somehow they be productive not Querro symphatizers.

  Who is going to give condo to those that got chased out with all their property looted then burnt down to the ground and even in some cases with their loved ones murdered just last month in Oromia , Harari , Dire DAWA ? NOONE. Noone is even documenting their identities SO they can claim to see if anything remained from their properties even after if it is burnt down , Right now Querro/ODP is putting their own fence around their properties .

  P.S. In the near past from Burayu , Sululta , Legetafo , Lafto ……people got displaced for green area and development.

  All these are signs of the times for Ethiopia

  • ለአሸባሪ ነፍጠኞች የምትቆረቆሩ ከሆነ፤ ሂዱና ባህር ዳር፣ ጎንደርና ደብረ ማርቆስ አካባቢ (ዙሪያ ገባዉን) ሚሊዮን ባለመቶ መቶ ፎቅ ኮንዶሚንየም ገንቡና ነፍጠኞቹን ከያሉበት ለቅማችሁ አስገቡ። ያኔ እምዬ ኢትዮጵያ ሰላም ታገኛለች።

   ማወቅ ያለባችሁ ነገር ኦሮምያ ዉስጥ የተሰራው ኮንዶምንየም የኦሮሞዎች ነዉ። ሕግ ላይ ተመስርቶ ብቻ ነዉ ልትኖሩበት የምትችሉት። ቆማጣ ሁሉ!

 3. 1)”…….. ሆኖም ከነዚህ መመዘኛዎች ውጭ በርካታ ሰዎች የጋራ መኖርያ ቤት ማግኘት ችለዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ይኖሩ የነበሩና አርሶአደርም የአርሶ አደር ልጅ ያልነበሩ ሰዎችም የጋራ መኖርያ ቤት ተሰጥቷቸዋል።……”

  OPDO yenefxenya shint yihin leOromo asiba fetsima kehone deg aregech. Gena yiqeral. Oromon keFinfinnee aglileh (le 150+ ametat)yet abak litiders neber???????!!!! Jib hulla.

  2)”…….ከ1997 አ.ም ጀምሮ ቤቶቹን የቆጠቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ቤቶቹን ለማግኘት እየተጠባበቁ ነበር።………”

  Atiwash, qebaxari. Oromon lemasaxat yematadergew neger yelem bayisakam. Inya yetemezegebnew be 1997 bihonim, meqoxeb yejemernew ke 2005 Yehabesha aqoxaxer jemiro new.

  3) Sijemer ciraq wayanewochna yenefxenya shintoch kilil teshagreh lemin genebah??????!!!! Genbito yafirsihna!!!!! Qoshasha jiboch. Ahunim gena waga tikeflaleh Oromo lay betecawetkew. Seeraa be seeraa yimelesal. Jiloch. Oromo yetinantina mesloshal.

 4. This news made so happy I am overjoyed as all Ethiopians should be jumping up in the air with joy. Mark my words within a few years from now Ethiopia will be self sufficient with food just because this farmers got the proper support and recognition , soon for the first time in a very long time foreign food aid will stop being needed to feed Ethiopians ,this is Medemer at it’s best.

 5. Abiy with Isayas and whoeverelse they got on their sides are extremely weak.
  Badme is for Tigrai people if they beg us peacefully we might consider it, otherwise Badme is for Tigrai.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.