“የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን መደመር ትክክለኛ አማራጭ ነው” አቶ ሌንጮ ባቲ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አማካሪ

1 min read

አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን መደመር ትክክለኛ አማራጭ እንደሚሆን ተገለጸ።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አማካሪ አቶ ሌንጮ ባቲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የተበላሸውን የፖለቲካ የኢኮኖሚ ስርአት ለማስተካከል ብቸኛው አማራጭ ፌዴራሊዝም ሲሆን መደመር ደግሞ እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲመጣ የሚያደርግ አተያይ ነው።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በርካታ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶች ተፈጥረዋል የሚሉት አቶ ሌንጮ እነዚህን ስብራቶች ለመጠገን ደግሞ መደመር ትክክለኛ አማራጭ እንደሚሆን አመልክተዋል። መደመር “አህዳዊነትን የሚያመጣ ነው” በሚል በአንዳንድ አካላት የሚነሳው ሃሳብም መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢህአዴግ ውህደት ከፌዴራሊዝም ስርዓቱ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሚገልፁት አቶ ሌንጮ ፌዴራል የሚሆነው አስተዳደሩና አወቃቀሩ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲው አይደለም ይላሉ።

ግርታ የፈጠረው ቀደም ሲል መንግስትና ፓርቲ አንድ ስለሆኑ ነው እንጂ መንግስትና ፓርቲ ሲለያይ ፌዴራሊዝም የመንግስት ስራ፤ ርዕዮተ ዓለም ደግሞ የፓርቲ ጉዳይ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

አሜሪካንና ጀርመን ፌዴራል የሆኑ ግዛቶች ቢኖሯቸውም ፓርቲዎቹ ግን ፌዴራል አይደሉም ሲሉ የሚጠቅሱት አቶ ሌንጮ አስተዳደሩ ፌዴራል የሆነው ህዝቡ የራሱን ባህልና ቋንቋ ጥቅም ላይ እንዲያውል መሆኑን አመልክተው የኢህአዴግ መዋሃድ አህዳዊ ስርዓት ለማምጣት ነው በሚል ብዥታ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት በውል አለመገንዘብ፣ ወይም የአስተሳሰብና የእውቀት ጉድለት መሆኑን አመልክተዋል።

የኢህአዴግ አገዛዝ አጋር ድርጅቶችን ያገለለና እኩል ተሳታፊ ያላደረገ እንደነበር ያነሱት አቶ ሌንጮ ውህደቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን እኩል የሚያሳትፍና ውሳኔ ሰጪ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ ዘመን ጥቅምት 24/2012

ጌትነት ምህረቴ

12 Comments

 1. Ethiopia is a failed state in all measures, the country is being led towards a path leading to a cliff because federal leaders don’t care about the country .

  The federal political leaders care about only their own cliques (the Oromo extremists).
  The rest (except the brave Tigrai ) are being chewed up and spit out one by one like a used chewing gum just because they tried to Medemer. Medemer means being chewed up by Oromo extremists Querro only to be spit out like a used chewing gum when the Oromo extremist is done with you.

  To the whole country the Medemer pill got serious side effects, just to name a few

  1. Medemer may lead to the loss of social values to the majority of young generation .

  2. The economy collapsing beyond repair.

  3. The politics being none relevant to the reality of the people’s lives.

 2. የጃዋርና ፀረ ኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ህልም ሉዐላዊ ኦሮሚያን ፈጥሮ ኢትዮጵያን መቅበር ነው:: ህውሀት ደግሞ የጃዋርን ያልሰለጠነ መንጋ ጋልቦ ኢትዮጵያን እንደገና ለመዝረፍ ነው:: ይህ በገሀድ እየታየ ነው:: ህውሀትና ጃዋር አንድ ክንፍ ሆነዋል:: የኢትዮጵያውያን ምርጫ ከዐቢይ ጋር ተሰልፎ ፀረ ኢትዮጵያዊውን ሀይል መቅበር ብቻ ነው:: ኢትዮጵያውያን ይደመራሉ:: ፀረ ኢትዮጵያውያን ይቀነሳሉ:: ሪፍራፊ አይደመርም::ሌንጮ ባቲና ዲማ ነገዎ በኦነግ ጀምራቸው መልካም ኢትዮጵያውያን ስለሆናችሁ እንደ አንድ አማራ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ

  • በፌደራል ደንብ እኮ ኦሮሚያ ዛሬም ሉዐላዊ ናት። አሁንም እኮ አንቀጽ 39 በህገ መንግስቱ ላይ አለ። የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ቢያስከብር (ነጻ ሃገር መመስረትም ቢሆን) እንግዲህ ኦሮሞ በሙሉ ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑ ነው?? ብሄር ብሄረሰቦች ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ማስከበራቸው ፀረ ኢትዮጵያ የሚያደርጋቸው ከሆነ፣ ያንተ ኢትዮጵያ የሰብአዊ እና የዲሞክራሲ ፀር ነች ማለት ነው! ችግሩ ያለው ማን ጋ ነው ታዲያ?

   • ክልሎች የአስተዳደራዊ ወሰኖች ናቸው:: ሉዐላዊ ሀገሮች አይደሉም:: ፅንፈኛ ኦሮሞዎች ህልማችሁ ሸል ሆኖ ይቀራል:: የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ ፅንፈኞች እንደተለመደው ትቢያ ሆነው ይቀራሉ::የኦሮሚያ አስተዳደር የሚኖረው በአንድ ሉዐላዊ ኢትዮጵያ ሀገር ነው:: የህውሀት ኮንፌዴሬሽን የጃዋር ኢስላሚክ ኦሮሚያ በተባበረው የኢትዮጵያ ሀይል መስመር ይይዛል:: ወያኔ ቀንሶ አንድ የሚሆነው አዲሱ የብልፅግና ፓርቲ የአንድ ኢትዮጵያ ግንባታ መሰረትም ይሆናል:: ጫፍ ከጫፍ የኢትዮጵያውያን ማእበል ይሰበሰባል:: ፀረ ኢትዮጵያውያንን ያመክናል:: ጃዋር የውጪ ጠላት ቅጥረኛ ባንዳ ኦሮሞን አይወክልም:: የአሱ ያልሰለጠነው መንጋ በህግ አስከባሪዎች መስመር ይይዛል:: ከታሪክ የምንማረው የኢትዮጵያ ጠላቶች አዲስ አበባ ምቹ ከተማ አይደለችም::

    • “ክልሎች የአስተዳደራዊ ወሰኖች ናቸው”?? – ታዲያ እንደድሮው ለምን ጠቅላይ ግዛቶች አልተባሉም?? ጠቅላይ ግዛቶችስ የራሳቸው ህገ መንግስታት ያስፈልጋቸዋል?? ይህ ነው የናንተ የፌደራሊዝም አረዳድ?? መጀመሪያ የፌደራሊዝምንና የዲሞክራሲን ሀ ሁ ተማሩ! ከዚያ በኋላ እንነጋገር ይሆናል!
     Nazrawi< 'ሉአላዊ' የሚለው ቃል ለእንግሊዝኛው 'sovereign' ትርጉም እንደሆነ ብዬ ነው። ታዲያ ሌሎች ሰዎችን በአንተ ደረጃ ዝቅ አድርገህ አትገምት፣ እንደበግ የምትነዳው ወይም የሌሎችን ጩሄት እንደበቀቀን የምታስተጋባው አንተ ነህ። ህዝብን "እንደበግ መነዳት" ወይም 'መንጋ' ብለው የሚሳደቡ ከበግ የባሱ ደንቆሮዎች ናቸው! የሰውን ልጅ እንደከብት የምታንቋሽሹት እራሳችሁ ከብት ስለሆናችሁ ሌላውንም እንደራሳችሁ እያያችሁት ነው! You imagine others through your own self! You have no better self image other than a ruminating animal, and think that others are as dumb as you are! No, others have better self conciousness!

     • Now I am “clear about Federalism”–qiqiqiqi.Thank you, teacher. But whoever prefers to live alone can not እዘርፋለሁ፣ እደበድባለው፣ እገላለሁ ማለት ግን እንሰሳነት ይሆናልና ታቀብ፡፡ ሰው ሁን:: Teacher, do you agree or remain to engage in robbery, killing and …This is what the people request you and your cruel friends

   • Aba Challa
    ሉአላዊ አገር እንጂ ሉአላዊ ክልል አለ ሲባል ሰምተን አናውቅም፡፡ የፌዴራል መንግስት ባላቸው አገራት ሁሉ ክልሎች አስተዳደራዊ ወሰኖች ናቸው፡፡ በኛም አገር ክልሎች አውቶኖሚ ያላቸው አስተዳደራዊ ክልል እንጂ ሉአላዊ አይደሉም፡፡ ሲፈለግ ሊበተኑ ሲያሻ ደግሞ ሊዋሃዱ እንደሚችሉ እንደሆነ ህገመንግስቱ ከገለጸ ምኑ ነው ሉአላዊ ናቸው የምትለው፡፡
    ለማንኛውም እንዳልከው አንቀጽ 39 አገር እንዴት መበታተን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ይህን ተጠቀምህ በግልጽ እየተናገርክ ጓዝህን ይዘህ በህግ አግባብ መንጎድ ትችላለህ፡፡ ለመሄድ ስታስብ ግን ሂሳብ አወራርደህ እንጂ የቀረውን አሸብረህ፣ ዘርፈህ፣ ደብድበህና ገለህ መሆን የለበትም፡፡ ጠ/ሚር ጃዋር ያዘዙህን ብቻ እየሰማህ እንደበግ ከመነዳት ሃይማኖትና ህሊና ካለህ እንደሰው በማሰብ፤ የሰውነት ግዴታህን ተወጥተህ ከሆነ መብትህን እናከብራለን፡፡ እዘርፋለሁ፣ እደበድባለው፣ እገላለሁ ማለት ግን እንሰሳነት ይሆናልና ታቀብ፡፡ ሰው ሁን

    • ህሳብ ማወራረድ ከተባለማ፣ እስከዛሬ ለጨፈጫፋችኋቸው ሚሊዮን ኦሮሞዎች ጉማ ትከፍላላችሁ! ለመቶ አመታት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለረሃብ፣ እርዛትና ሞት ለተዳረጉት፣ እንዲሁም በእስራትና ግርፋት ለአካለ ጎዶሎነትና ህሊናዊ ቁስል ላደርሳችሁባቸው ሚሊዮኖች ካሳ ትከፍሉና፣ የዘረፋችሁትን መሬትና ንብረት መልሳችሁ ኦሮሚያን ትሰናበቱና መልካም ጎረበቶች እንሆናለን! ናጋቲ!

  • ለዚህ ሁሉ ችግር መሰረት የሆነችዉን ያንተን የነፍጠኞች ኢትዮጵያ መቅበር ማለት የአፍርቃ ቀንድን ችግር ላንዴና ለመጨራሻ ጊዜ ምፍታት ማለት ነዉ።

   • በመጀመሪያ አንተ ያልሰሰጠንከው ገልቱ ተቀበርና የሰለጠነች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትመሰረታለች:: ሀገር የሚመራው በሰከነና በሰለጠነ አእምሮና እውቀት ነው:: አሸባሪ መንጋ ልክ እደሌሎች አሸባሪዎች በህግ መስመር ይይዛል:: ነፍጠኛውን ደግሞ አመስግን ሰው ስላደረገህ ከእረኝነት አውጥቶ ላፕ ቶፕና ፌስቡክ ተጠቃሚ ስላደረገህ::

 3. “ቀደም ሲል መንግስትና ፓርቲ አንድ ስለሆኑ ነው …” ታዲያ መንግስትና ፓርቲን ለመለየት አሁን ያለውን አሰራር ከመቀየር ማን ከለከላችሁ? ያን መቀየር ከፓርቲ ዉህደት ጋር ምን አገናኘው? አሁንም በመንግስት ካዝና የፓርቲ ሥራና ፕሮፓጋንዳ እየሰራችሁ አይደል??

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.